የሴዴቅያስንም ልጆች በፊቱ ገደሉአቸው፤ የሴዴቅያስንም ዐይኖች አወጡ፤ በሰንሰለትም አሰሩት፤ ወደ ባቢሎንም ወሰዱት።
ኤርምያስ 38:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሚስቶችህንና ልጆችህንም ሁሉ ወደ ከለዳውያን ያወጣሉ፤ አንተም በባቢሎን ንጉሥ እጅ ትያዛለህ እንጂ ከእጃቸው አታመልጥም፤ ይህችም ከተማ በእሳት ትቃጠላለች።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሚስቶችህና ልጆችህ ሁሉ ተወስደው ለባቢሎናውያን ይሰጣሉ፤ አንተም ራስህ በባቢሎን ንጉሥ ትያዛለህ እንጂ ከእጃቸው አታመልጥም፤ ይህችም ከተማ በእሳት ትቃጠላለች።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሚስቶችህንና ልጆችህንም ሁሉ ወደ ከለዳውያን ያወጣሉ፤ አንተም በባቢሎን ንጉሥ እጅ ትያዛለህ እንጂ ከእጃቸው አታመልጥም፤ ይህችም ከተማ በእሳት ትቃጠላለች።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በተጨማሪም እንዲህ አልኩት፦ “ሚስቶችህና ልጆችህ ሁሉ ወደ ባቢሎናውያን ይወሰዳሉ፤ አንተም በባቢሎን ንጉሥ ተይዘህ እስረኛ ትሆናለህ፤ ከእነርሱ እጅ ከቶ አታመልጥም፤ ይህችም ከተማ በእሳት ተቃጥላ ትወድማለች።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሚስቶችህንና ልጆችህንም ሁሉ ወደ ከለዳውያን ያወጣሉ፥ አንተም በባቢሎን ንጉሥ እጅ ትያዛለህ እንጂ ከእጃቸው አታመልጥም፥ ይህችም ከተማ በእሳት ትቃጠላለች። |
የሴዴቅያስንም ልጆች በፊቱ ገደሉአቸው፤ የሴዴቅያስንም ዐይኖች አወጡ፤ በሰንሰለትም አሰሩት፤ ወደ ባቢሎንም ወሰዱት።
ለመልካም ሳይሆን ለክፉ ፊቴን በዚህች ከተማ ላይ አድርጌአለሁና፤ ለባቢሎን ንጉሥ እጅ ትሰጣለች፤ እርሱም በእሳት ያቃጥላታል።”
የይሁዳም ንጉሥ ሴዴቅያስ በእውነት በባቢሎን ንጉሥ እጅ አልፎ ይሰጣል፤ አፍ ለአፍም ይናገረዋል፤ ዐይን ለዐይንም ይተያያሉ እንጂ ከከለዳውያን እጅ አያመልጥም፤
አንተም በርግጥ ትያዛለህ፤ በእጁም አልፈህ ትሰጣለህ እንጂ ከእጁ አታመልጥም፤ ዐይንህም የባቢሎንን ንጉሥ ዐይን ታያለች፤ እርሱም ከአንተ ጋር አፍ ለአፍ ይናገራል፤ ወደ ባቢሎንም ትገባለህ።
ወደ ባቢሎን ንጉሥ አለቆች ባትወጣ ግን፥ ይች ከተማ በከለዳውያን እጅ ትሰጣለች፤ በእሳትም ያቃጥሉአታል፤ አንተም ከእጃቸው አታመልጥም” አለው።
የከለዳውያንም ሠራዊት ተከታተላቸው፤ ሴዴቅያስንም በኢያሪኮ ሜዳ አገኙት፤ ይዘውም በሐማት ምድር ወዳለችው ወደ ዴብላታ ወደ ባቢሎን ንጉሥ ወደ ናቡከደነፆር አመጡት፤ እርሱም ፍርድን በእርሱ ላይ ተናገረ።
የባቢሎንም ንጉሥ የሴዴቅያስን ልጆች በዐይኑ ፊት በዴብላታ ገደላቸው፤ የባቢሎንም ንጉሥ የይሁዳን ታላላቆች ሁሉ ገደለ።
እስማኤልም በመሴፋ የነበረውን የሕዝቡን ቅሬታ ሁሉ፥ የንጉሡን ሴቶች ልጆች፥ የአዛዦች አለቃ ናቡዛርዳን ለአኪቃም ልጅ ለጎዶልያስ የሰጠውን በመሴፋ የቀሩትን ሕዝብ ሁሉ መለሰ፤ የናታንያም ልጅ እስማኤል ወደ አሞን ልጆች ይሄድ ዘንድ ተነሣ።
እጄን በዚች ምድር በሚኖሩ ላይ እዘረጋለሁና ቤቶቻቸዉ፥ እርሻዎቻቸውም፥ ሴቶቻቸውም በአንድነት ለሌሎች ይሰጣሉ፥ ይላል እግዚአብሔር፤
ነቢዩም ቢታለል፥ ቃልንም ቢናገር፥ ያን ነቢይ ያታለልሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፥ እጄንም በእርሱ ላይ እዘረጋለሁ፤ ከሕዝቤም ከእስራኤል መካከል አጠፋዋለሁ።
እርሱ ግን በእርሱ ላይ ሸፈተ፤ ፈረሶችንና ብዙንም ሕዝብ ይሰጡት ዘንድ መልእክተኞችን ወደ ግብፅ ላከ። በውኑ ይከናወንለት ይሆን? ይህንስ ያደረገ ያመልጣልን? ቃል ኪዳንንስ ያፈረሰ ያመልጣልን?
ያየሁትም ራእይ ከተማዪቱን ለማጥፋት በመጣሁ ጊዜ እንደ አየሁት ራእይ ነበረ፤ ራእዩም በኮቦር ወንዝ እንደአየሁት ራእይ ነበረ፤ እኔም በግምባሬ ተደፋሁ።