እርሱም፥ “እኔ ደግሞ እንዳንተ ነቢይ ነኝ፤ መልአክም፦ እንጀራ ይበላ ዘንድ ውኃም ይጠጣ ዘንድ ከአንተ ጋር ወደ ቤትህ መልሰው ብሎ በእግዚአብሔር ቃል ተናገረኝ” አለው። ዋሽቶም ተናገረው።
ኤርምያስ 28:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሐናንያም በሕዝቡ ሁሉ ፊት፥ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እንግዲህ በሁለት ዓመት ውስጥ የባቢሎንን ንጉሥ የናቡከደነፆርን ቀንበር ከአሕዛብ ሁሉ አንገት እሰብራለሁ” አለ። ነቢዩ ኤርምያስም መንገዱን ሄደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሐናንያም በሕዝቡም ፊት፣ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ የባቢሎንን ንጉሥ የናቡከደነፆርን ቀንበር ከሕዝቡ ሁሉ ጫንቃ ላይ ልክ እንደዚህ እሰብራለሁ’ ” አለ። በዚህ ጊዜ፣ ነቢዩ ኤርምያስ ትቶት መንገዱን ቀጠለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሐናንያም በሕዝብ ሁሉ ፊት እንዲህ ብሎ ተናገረ፦ “ጌታ እንዲህ ይላል፦ በሁለት ዓመት ውስጥ እንዲሁ የባቢሎንን ንጉሥ የናቡከደነፆርን ቀንበር ከአሕዛብ ሁሉ አንገት እሰብራለሁ።” ነቢዩም ኤርምያስ መንገዱን ሄደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሕዝቡም ሁሉ ፊት ሲናገር፦ “በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ የባቢሎንን ንጉሥ ናቡከደነፆርን የአገዛዝ ቀንበር ከሕዝቡ ጫንቃ ላይ አውርዶ እንደዚህ የሚሰባብረው መሆኑን እግዚአብሔር ተናግሮአል” አለ፤ ከዚያም በኋላ እኔ ከዚያ ተነሥቼ ሄድኩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሐናንያም በሕዝብ ሁሉ ፊት፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እንዲሁ በሁለት ዓመት ውስጥ የባቢሎንን ንጉሥ የናቡከደነፆርን ቀንበር ከአሕዛብ ሁሉ አንገት እሰብራለሁ አለ። ነቢዩም ኤርምያስ መንገዱን ሄደ። |
እርሱም፥ “እኔ ደግሞ እንዳንተ ነቢይ ነኝ፤ መልአክም፦ እንጀራ ይበላ ዘንድ ውኃም ይጠጣ ዘንድ ከአንተ ጋር ወደ ቤትህ መልሰው ብሎ በእግዚአብሔር ቃል ተናገረኝ” አለው። ዋሽቶም ተናገረው።
የእስራኤልም ንጉሥ ነቢያቱን አራት መቶ የሚያህሉትን ሰዎች ሰበሰበ፤ የእስራኤል ንጉሥም፥ “ወደ ሬማት ዘገለዓድ ለሰልፍ ልሂድን? ወይስ ልቅር?” አላቸው። እነርሱም፥ “እግዚአብሔር በንጉሥ እጅ አሳልፎ ይሰጣታልና ውጣ” አሉት።
የካህናን ልጅ ሴዴቅያስም የብረት ቀንዶች ሠርቶ፦ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ሶርያውያንን እስክታጠፋቸው ድረስ በእነዚህ ትወጋለህ” አለ።
እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፥ “ነቢያቱ በስሜ የሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤ አላክኋቸውም፤ አላዘዝኋቸውም፤ አልተናገርኋቸውም፤ የሐሰቱን ራእይ፥ ምዋርትንም፥ ከንቱንም ነገር፥ በልባቸውም የፈጠሩትን ይተነብዩላችኋል።”
የእግዚአብሔርን ቃል ለሚያቃልሉ ሰላም ይሆንላችኋል፥ በፍላጎታቸውና በልቡናቸው ክፋት ለሚሄዱም ሁሉ፦ ክፉ ነገር አያገኛችሁም” ይላሉ።
ነቢዩም ኤርምያስ ሐሰተኛውን ሐናንያን፥ “ሐናንያ ሆይ ስማ፤ እግዚአብሔር አልላከህም፤ ነገር ግን ይህ ሕዝብ በሐሰት እንዲታመን አድርገሃል።
እኔም ሳልናገር፦ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎአል ስትሉ፥ ከንቱ ምዋርትን የተናገራችሁ፥ የሐሰት ራእይንም ያያችሁ አይደላችሁምን?”