አንተ እንዲህ ትላቸዋለህ፦ አባቶቻችሁ እኔን ስለ ተዉ ነው፥ ይላል እግዚአብሔር፤ ሌሎችንም አማልክት ተከተሉ፤ አመለኩአቸውም፤ ሰገዱላቸውም፤ እነርሱም ትተውኛል፤ ሕጌንም አልጠበቁም፤
እንዲህ ትላቸዋለህ፤ ‘አባቶቻችሁ እኔን ስለ ተዉኝ ነው’ ይላል እግዚአብሔር፤ ‘ሌሎችን አማልክት በመከተል፣ ስላገለገሏቸውና ስላመለኳቸው ነው፤ ትተውኝ ኰበለሉ፤ ሕጌንም አልጠበቁም።
አንተም እንዲህ ትላቸዋለህ፦ ‘አባቶቻችሁ እኔን ስለ ተው ነው፥ ይላል ጌታ፥ ሌሎችንም አማልክት ተከተሉ አገለገሉአቸውም ሰገዱላቸውም፥ እነርሱም ትተውኛል፥ ሕጌንም አልጠበቁም፤
በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር እንዲህ ይላችኋል በላቸው፦ ‘የቀድሞ አባቶቻችሁ ከእኔ ተለይተው የሐሰት አማልክትን በማምለክ አገለገሉ፤ እኔን ተዉኝ፤ ሕጌንም አልፈጸሙም።
አንተ እንዲህ ትላቸዋለህ፦ አባቶቻችሁ እኔን ስለ ተው ነው፥ ይላል እግዚአብሔር፥ ሌሎችንም አማልክት ተከተሉ አመለኩአቸውም ሰገዱላቸውም፥ እነርሱም ትተውኛል፥ ሕጌንም አልጠበቁም፥
መልሰውም፦ ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት አባቶቻቸውን ያወጣውን አምላካቸውን እግዚአብሔርን ትተው ሌሎችን አማልክት ስለ ተከተሉ፥ ስለ ሰገዱላቸውም፥ ስለ አመለኩአቸውም፥ ስለዚህ እግዚአብሔር ይህን ክፉ ነገር ሁሉ አመጣባቸው ይላሉ።” ያንጊዜም ሰሎሞን የፈርዖንን ልጅ ከዳዊት ከተማ አውጥቶ በዚያ ወራት ለራሱ በሠራው ቤት አስገባት።
መልሰውም፦ ከግብፅ ምድር ያወጣቸውን ያባቶቻቸውን አምላክ እግዚአብሔርን ትተው ሌሎችን አማልክት ስለ ተከተሉ፥ ስለ ሰገዱላቸውም፥ ስለ አመለኩአቸውም፥ ስለ አገለገሏቸውም፥ ስለዚህ ይህን ክፉ ነገር ሁሉ አመጣባቸው” ይላሉ።
በልብሽም፦ እንዲህ ያለ ነገር ስለ ምን ደረሰብኝ? ብትዪ፥ ከኀጢአትሽ ብዛት የተነሣ ልብስሽ በስተኋላሽ ተገፎአል፤ ተረከዝሽም ተገልጦአል።
ካህናቱም፦ እግዚአብሔር ወዴት አለ? አላሉም፤ ሕጌን የተማሩትም አላወቁኝም፤ ጠባቂዎችም ዐመፁብኝ፤ ነቢያትም በበዐል ትንቢት ተናገሩ፤ የማይጠቅማቸውንም ነገር ተከተሉ።
እነርሱም፦ የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ትተው ለሌሎች አማልክት ስለ ሰገዱ፥ ስለ አመለኳቸውም ነው ብለው ይመልሳሉ።”
ይህም የሆነው ያስቈጡኝ ዘንድ ስላደረጉት ክፋት፥ እነርሱና አባቶቻቸው ለማያውቁአቸው ለሌሎች አማልክት ያጥኑ ዘንድ፥ ያመልኳቸውም ዘንድ ስለሄዱ ነው።
በወደዱአቸውና በአመለኳቸው፥ በተከተሉአቸውና በፈለጓቸው፥ በሰገዱላቸውም በፀሐይና በጨረቃ፥ በከዋክብትም፥ በሰማይም ሠራዊት ሁሉ ፊት ይዘረጓቸዋል፤ አያለቅሱላቸውም፤ አይቀብሯቸውምም፤ በምድርም ፊት ላይ እንደ ጕድፍ ይሆናሉ።
ነገር ግን የልባቸውን ምኞትና አባቶቻቸው ያስተማሩአቸውን ጣዖት ተከትለዋል፤
አባቶቻችን ኀጢአትን ሠሩ፤ ዛሬም የሉም፤ እኛም በደላቸውን ተሸከምን።
ጣዖት በሚያመልኩበት ልባቸውና በኀጢአታቸው እንደ ልባቸው ቢሄዱ መንገዳቸውን በራሳቸው ላይ እመልሳለሁ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “የእግዚአብሔርን ሕግ አፍርሰዋልና፥ ትእዛዙንም አልጠበቁምና፥ አባቶቻቸውም የተከተሉት ከንቱ ነገር አስቶአቸዋልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የይሁዳ ኀጢአት መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስላቸውም።
ከአባቶቻችሁ ዘመን ጀምሮ ከሥርዓቴ ፈቀቅ ብላችኋል፥ እርስዋንም አልጠበቃችሁም። ወደ እኔ ተመለሱ፥ እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። እናንተ ግን፦ የምንመለሰው በምንድር ነው? ብላችኋል።
የአሕዛብን ፈቃድ ያደረጋችሁበት በመዳራትና በሥጋ ምኞትም በስካርም በዘፈንም ያለ ልክም በመጠጣት ነውርም ባለበት በጣዖት ማምለክ የተመላለሳችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃልና።
የእስራኤልም ልጆች በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረጉ፤ በዓሊምንም አመለኩ።