La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 15:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አቤቱ! በመ​ከ​ራ​ቸ​ውና በጭ​ን​ቃ​ቸው ጊዜ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ዘንድ ስለ እነ​ርሱ በጎ ነገር በአ​ንተ ፊት የቆ​ምሁ ባል​ሆን ይህ ለእ​ነ​ርሱ መከ​ና​ወን ይሁን።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “በርግጥ ለበጎ ዐላማ እታደግሃለሁ፤ በመከራና በጭንቅ ጊዜም፣ ጠላቶችህ ደጅ እንዲጠኑህ በእውነት አደርጋለሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታ እንዲህ አለ፦ በእውነት ለመልካም ነገር አጸናሃለሁ፤ በእውነት በመከራና በጭንቅ ጊዜ ጠላትህ እንዲለምንህ አደርገዋለሁ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “በእርግጥ ለመልካም ዓላማ እታደግሃለሁ፤ በችግርና በመከራ ጊዜ ጠላቶችህ አንተን እንዲለማመጡ አደርጋለሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ በእውነት ለደኅንነትህ አጸናሃለሁ፥ በእውነት በመከራና በጭንቅ ጊዜ ጠላትህ እንዲለምንህ አደርገዋለሁ።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 15:11
15 Referencias Cruzadas  

ፍለ​ጋ​ዬ​ንና መን​ገ​ዴን አንተ ትመ​ረ​ም​ራ​ለህ፤ መን​ገ​ዶ​ቼን ሁሉ አስ​ቀ​ድ​መህ ዐወ​ቅህ፥


ቅንነትን የሚሹ ሰላምን ያገኛሉ።


የንጉሥ ልብ እንደ ውኃ ፈሳሽ በእግዚአብሔር እጅ ነው፤ ወደ ወደደውም ይመልሳታል፥ በዚያም ትቈያለች።


የበ​ደለ ከጥ​ንት ጀምሮ ከዚ​ያም በፊት ኀጢ​አ​ትን አድ​ር​ጓል፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለሚ​ፈ​ሩት በፊ​ቱም ለሚ​ፈ​ሩት ደኅ​ን​ነት እን​ዲ​ሆን አው​ቃ​ለ​ሁና፤


እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና አት​ፍራ፤ እኔ አም​ላ​ክህ ነኝና አት​ደ​ን​ግጥ፤ አበ​ረ​ታ​ሃ​ለሁ፤ እረ​ዳ​ህ​ማ​ለሁ፤ በጽ​ድ​ቄም ቀኝ ደግፌ እይ​ዝ​ሃ​ለሁ።


“የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ይወ​ጋን ዘንድ መጥ​ቶ​አ​ልና ከእኛ ይመ​ለስ ዘንድ፥ ምና​ል​ባ​ትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኛ ጋር እንደ ተአ​ም​ራቱ ሁሉ ያደ​ርግ እንደ ሆነ ስለ እኛ፥ እባ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጠይቅ።”


ንጉ​ሡም ሴዴ​ቅ​ያስ ልኮ አስ​መ​ጣው፥ ንጉ​ሡም በቤቱ፥ “በውኑ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ የሆነ ቃል አለን?” ብሎ በቈ​ይታ ጠየ​ቀው። ኤር​ም​ያ​ስም፥ “አዎን አለ፤ ደግ​ሞም በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ እጅ አል​ፈህ ትሰ​ጣ​ለህ” አለው።


ንጉ​ሡም ሴዴ​ቅ​ያስ፥ “ወደ አም​ላ​ካ​ችን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ እኛ ጸልይ” ብሎ የሰ​ሌ​ም​ያን ልጅ ዮካ​ል​ንና ካህ​ኑን የማ​ሴ​ውን ልጅ ሶፎ​ን​ያ​ስን ወደ ነቢዩ ወደ ኤር​ም​ያስ ላከ።


ንጉ​ሡም ሴዴ​ቅ​ያስ ልኮ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወደ ነበ​ረው ወደ ሦስ​ተ​ኛው መግ​ቢያ ወደ እርሱ ነቢ​ዩን ኤር​ም​ያ​ስን አስ​መ​ጣው፤ ንጉ​ሡም ኤር​ም​ያ​ስን፥ “አን​ዲት ነገር እጠ​ይ​ቅ​ሃ​ለሁ፤ ምንም አት​ሸ​ሽ​ገኝ” አለው።


እን​ዲ​ህም አሉት፥ “እባ​ክህ ልመ​ና​ችን በፊ​ትህ ትድ​ረስ፤ ስለ እኛ፥ ስለ እነ​ዚ​ህም ቅሬ​ታ​ዎች ሁሉ ወደ አም​ላ​ክህ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጸል​ይ​ልን፤ ዐይ​ኖ​ችህ እንደ አዩን ከብዙ ጥቂት ቀር​ተ​ና​ልና።