Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 15:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ጌታ እንዲህ አለ፦ በእውነት ለመልካም ነገር አጸናሃለሁ፤ በእውነት በመከራና በጭንቅ ጊዜ ጠላትህ እንዲለምንህ አደርገዋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “በርግጥ ለበጎ ዐላማ እታደግሃለሁ፤ በመከራና በጭንቅ ጊዜም፣ ጠላቶችህ ደጅ እንዲጠኑህ በእውነት አደርጋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “በእርግጥ ለመልካም ዓላማ እታደግሃለሁ፤ በችግርና በመከራ ጊዜ ጠላቶችህ አንተን እንዲለማመጡ አደርጋለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 አቤቱ! በመ​ከ​ራ​ቸ​ውና በጭ​ን​ቃ​ቸው ጊዜ በጠ​ላ​ቶ​ቻ​ቸው ዘንድ ስለ እነ​ርሱ በጎ ነገር በአ​ንተ ፊት የቆ​ምሁ ባል​ሆን ይህ ለእ​ነ​ርሱ መከ​ና​ወን ይሁን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ በእውነት ለደኅንነትህ አጸናሃለሁ፥ በእውነት በመከራና በጭንቅ ጊዜ ጠላትህ እንዲለምንህ አደርገዋለሁ።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 15:11
15 Referencias Cruzadas  

የሰው አካሄድ ጌታን ደስ ያሰኘው እንደሆነ፥ በእርሱና በጠላቶቹ መካከል ስንኳ ሰላምን ያደርጋል።


በማረኩአቸውም ሁሉ ፊት ሞገስን ሰጣቸው።


ንጉሡም ሴዴቅያስ፦ “እባክህ፥ ወደ አምላካችን ወደ ጌታ ስለ እኛ ጸልይ” ብሎ የሰሌምያን ልጅ ዮካልንና ካህኑን የመዕሤያን ልጅ ሶፎንያስን ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ ላከ።


ኃጢአተኛ መቶ ጊዜ ክፉን ቢሠራ ዘመኑም ረጅም ቢሆን፥ እግዚአብሔርን ለሚፈሩት በፊቱም ለሚፈሩት መልካም እንደሚሆን አውቃለሁ፥


ነቢዩንም ኤርምያስን እንዲህ አሉት፦ “በዐይኖችህ እንደምታየን ከብዙ ጥቂት ተርፈናልና ልመናችን እባክህ፥ በፊትህ ትድረስ፥ ስለ እኛና ስለዚህ ትሩፍ ሁሉ ለጌታ ለአምላክህ ጸልይ፥


“የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ይወጋናልና ስለ እኛ፥ እባክህ፥ ጌታን ጠይቅ፤ ምናልባትም ጌታ ለእኛ እንደ ተአምራቱ ሁሉ አድርጐ ከእኛ እንዲመለስ ያደርገዋልና።”


የንጉሥ ልብ እንደ ውኃ ፈሳሾች በጌታ እጅ ነው፥ ወደ ወደደውም ያዘነብለዋል።


በጠራሁህ ቀን በፍጥነት አድምጠኝ፥ ነፍሴን በኃይልህ አጸናሃት።


እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳሀለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።


ንጉሡ ሴዴቅያስ ልኮ አስመጣው፥ ንጉሡም በቤቱ፦ “በውኑ ከጌታ ዘንድ የሆነ ቃል አለን?” ብሎ በድብቅ ጠየቀው። ኤርምያስም፦ “አዎን አለ” ብሎ መለሰ። ከዚያም በኋላ፦ “በባቢሎን ንጉሥ እጅ ተላልፈህ ትሰጣለህ” አለ።


ንጉሡም ሴዴቅያስ ልኮ በጌታ ቤት ወደነበረው ወደ ሦስተኛው መግቢያ ወደ እርሱ ነቢዩን ኤርምያስን አስመጣው፤ ንጉሡም ኤርምያስን፦ “እኔ አንዲት ነገር እጠይቅሃለሁ፤ ምንም አትሸሽገኝ” አለው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios