ሁሉም እያንዳንዱ በፊቱ የነበረውን ሰው ገደለ፤ ደጋግመውም ገደሉ። ከዚህም በኋላ ሶርያውያን ሸሹ፤ እስራኤልም አሳደዱአቸው፤ የሶርያ ንጉሥ ወልደ አዴርም በፈጣን ፈረስ አመለጠ።
ኤርምያስ 15:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናቴ ሆይ! ለምድር ሁሉ የክርክርና የጥል ሰው የሆንሁትን እኔን ወልደሽኛልና ወዮልኝ! ለማንም አልጠቀምሁም፤ ማንም እኔን አልጠቀመኝም፤ ከሚረግሙኝም የተነሣ ኀይሌ አለቀ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወይኔ እናቴ! ለምድር ሁሉ፣ የጭቅጭቅና የክርክር ሰው የሆንሁትን ምነው ወለድሽ! ለማንም አላበደርሁም፤ ከማንም አልተበደርሁም፤ ነገር ግን ሰው ሁሉ ይረግመኛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናቴ ሆይ፥ ወዮልኝ! ለምድር ሁሉ የሙግትና የጥል ሰው የሆንሁትን ወለድሽኝ፤ ለማንም አላበደርሁም፥ ማንም ለእኔ አላበደረም፥ ነገር ግን ሁሉ ይረግመኛል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናቴ ሆይ፥ ወዮልኝ! ለምን ወለድሽኝ? ዕድል ፈንታዬ ከአገሪቱ ሕዝብ ሁሉ ጋር መከራከርና መነታረክ ሆኗል፤ እኔ ገንዘብ ለማንም አላበደርኩም ወይም ከማንም አልተበደርኩም፤ ሆኖም ሰው ሁሉ ይረግመኛል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናቴ ሆይ፥ ወዮልኝ! ለምድር ሁሉ የክርክርና የጥል ሰው የሆንሁትን ወለድሽኝ፥ ለማንም አላበደርሁም፥ ማንም ለእኔ አላበደረም፥ ነገር ግን ሁሉ ይረግመኛል። |
ሁሉም እያንዳንዱ በፊቱ የነበረውን ሰው ገደለ፤ ደጋግመውም ገደሉ። ከዚህም በኋላ ሶርያውያን ሸሹ፤ እስራኤልም አሳደዱአቸው፤ የሶርያ ንጉሥ ወልደ አዴርም በፈጣን ፈረስ አመለጠ።
የእስራኤልም ንጉሥ ኢዮሣፍጥን፥ “እግዚአብሔርን የምንጠይቅበት የይምላ ልጅ ሚክያስ የሚባል አንድ ሰው አለ፤ ነገር ግን ክፉ እንጂ መልካም አይናገርልኝምና እጠላዋለሁ” አለው። የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥም፥ “ንጉሥ እንዲህ አይበል” አለ።
አቤቱ፥ የሚሹህ ሁሉ በአንተ ሐሤት ያድርጉ፥ ደስም ይበላቸው፤ ሁልጊዜ ማዳንህን የሚወድዱ፥ “ዘወትር እግዚአብሔር ታላቅ ነው” ይበሉ።
ወንድምህ ከአንተ ጋር ይኖር ዘንድ ከእርሱ ምንም ወለድ ወይም ትርፍ አትውሰድ፤ ነገር ግን አምላክህን ፍራ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝና።
እኔ ግን እላችኋለሁ፤ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፤ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፤ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፤ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።
ስምዖንም ባረካቸው፤ እናቱን ማርያምንም እንዲህ አላት፤ “እነሆ፥ ይህ ሕፃን ከእስራኤል መካከል ለብዙዎች ለመውደቃቸውና ለመነሣታቸው፥ ለሚቃወሙትም ምልክት ይሆን ዘንድ የተሠየመ ነው፤
ሰዎች ስለ ሰው ልጅ ቢጠሉአችሁ፥ ከሰው ለይተው ቢአሳድዱአችሁ፥ ቢሰድቡአችሁ፥ ክፉ ስምም ቢአወጡላችሁ ብፁዓን ናችሁ።
ነገር ግን በዚህ ነገር በየስፍራው ሁሉ እንዲጣሉ በእኛ ዘንድ ታውቋልና የአንተን ዐሳብ ደግሞ ከአንተ እንሰማ ዘንድ እንወድዳለን።”