ሁሉም ዕውራን እንደ ሆኑ ኑና እዩ፤ ሁሉ ያለ ዕውቀት ናቸው፤ ሁሉም ዲዳ የሆኑ ውሾች ናቸው፤ ይጮኹም ዘንድ አይችሉም፤ በመኝታቸውም ሕልምን ያልማሉ፤ ማንቀላፋትንም ይወድዳሉ።
ኤርምያስ 14:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም፥ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ወዮ! እነሆ ነቢያት፦ እውነትንና ሰላምን በዚህ ስፍራ እሰጣችኋለሁ እንጂ ሰይፍን አታዩም፤ ራብም አያገኛችሁም ይሉአቸዋል” አልሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔም፣ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ወዮ! ነቢያቱ ‘ሰይፍ አታዩም፤ ራብም አያገኛችሁም፤ ነገር ግን በዚህ ስፍራ ዘለቄታ ያለው እውነተኛ ሰላም እሰጣችኋለሁ’ ይላል ይሏቸዋል” አልሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም፦ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ወዮ! እነሆ፥ ነቢያት፦ ‘ዘላቂ ሰላም በዚህ ስፍራ እሰጣችኋለሁ እንጂ ሰይፍን አታዩም፥ ራብም አያገኛችሁም’ ይሉአቸዋል” አልሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔም እንዲህ አልኩ፦ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ነቢያቱ ‘ጦርነት ሆነ ራብ አይኖርም’ እያሉ ለሕዝቡ ይናገራሉ፤ ‘በምድራችን ዘላቂ ሰላም ብቻ እንደሚሰፍን እግዚአብሔር ተናግሮአል’ ይላሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም፦ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወዮ! እነሆ፥ ነቢያት፦ በእውነት ሰላምን በዚህ ስፍራ እሰጣችኋለሁ እንጂ ሰይፍን አታዩም፥ ራብም አያገኛችሁም ይሉአቸዋል አልሁ። |
ሁሉም ዕውራን እንደ ሆኑ ኑና እዩ፤ ሁሉ ያለ ዕውቀት ናቸው፤ ሁሉም ዲዳ የሆኑ ውሾች ናቸው፤ ይጮኹም ዘንድ አይችሉም፤ በመኝታቸውም ሕልምን ያልማሉ፤ ማንቀላፋትንም ይወድዳሉ።
አንተም ጳስኮር ሆይ! በቤትህም የሚኖሩት ሁሉ ተማርካችሁ ትሄዳላችሁ፤ አንተም በሐሰት ትንቢት የተናገርህላቸው ወዳጆችህ ሁሉ ወደ ባቢሎን ትገባላችሁ፤ በዚያም ትሞታላችሁ፤ በዚያም ትቀበራላችሁ።”
የእግዚአብሔርን ቃል ለሚያቃልሉ ሰላም ይሆንላችኋል፥ በፍላጎታቸውና በልቡናቸው ክፋት ለሚሄዱም ሁሉ፦ ክፉ ነገር አያገኛችሁም” ይላሉ።
የባቢሎን ንጉሥ በእናንተና በዚህች ሀገር አይመጣባችሁም ብለው ትንቢት ይናገሩላችሁ የነበሩ ነቢያቶቻችሁ ወዴት አሉ?
እኔም፥ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ወዮ! አንተ ሰይፍ እስከ ሰውነታቸው ድረስ እስክትደርስ ሰላም ይሆንላችኋል” ብለህ ይህን ሕዝብና ኢየሩሳሌምን እጅግ አታለልህ አልሁ።
የይሁዳም ወገኖች በእግዚአብሔር ዋሹ፤ እንዲህም አሉ፥ “እንደዚህ አይደለም፤ ክፉ ነገርም አይመጣብንም ሰይፍንና ራብንም አናይም፤
ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፥ ካህናትም በእጃቸው ያጨበጭባሉ፥ ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ነገር ይወድዳሉ፤ በፍጻሜውስ ምን ታደርጋላችሁ?
እኔም ያልመለስሁትን የጻድቁን ልብ ወደ ዐመፃ መልሳችኋልና፥ በሕይወትም ይኖር ዘንድ ከክፉ መንገድ እንዳይመለስ የኀጢአተኛውን እጅ አበርትታችኋልና፤
አለቆችዋ በጉቦ ይፈርዳሉ፥ ካህናቶችዋም በዋጋ ያስተምራሉ፥ ነቢያቶችዋም በገንዘብ ያምዋርታሉ፥ ከዚህም ጋር፦ እግዚአብሔር በመካከላችን አይደለምን? ክፉ ነገር ምንም አይመጣብንም እያሉ በእግዚአብሔር ይታመናሉ።
ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት ደግሞ በሕዝቡ መካከል ነበሩ፤ እንዲሁም በመካከላችሁ ደግሞ ሐሰተኞች አስተማሪዎች ይሆናሉ፤ እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው የሚፈጥንን ጥፋት በራሳቸው ላይ እየሳቡ የሚያጠፋ ኑፋቄን አሹልከው ያገባሉ፤