Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 56:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ሁሉም ዕው​ራን እንደ ሆኑ ኑና እዩ፤ ሁሉ ያለ ዕው​ቀት ናቸው፤ ሁሉም ዲዳ የሆኑ ውሾች ናቸው፤ ይጮ​ኹም ዘንድ አይ​ች​ሉም፤ በመ​ኝ​ታ​ቸ​ውም ሕል​ምን ያል​ማሉ፤ ማን​ቀ​ላ​ፋ​ት​ንም ይወ​ድ​ዳሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 የእስራኤል ጠባቂዎች ዕውሮች ናቸው፤ ዕውቀት የላቸውም፤ ሁሉም ድምፅ የለሽ ውሾች ናቸው፤ መጮኽ አይችሉም፤ ተጋድመው ያልማሉ፤ እንቅልፍ ይወድዳሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ጉበኞቹ ዕውሮች ናቸው፥ ሁሉም እውቀት የላቸውም፤ ሁሉም ዲዳ የሆኑ ውሾች ናቸው፤ መጮኽ አይችሉም፤ ሕልምን ያልማሉ፤ ይተኛሉ፤ እንቅልፍ ይወድዳሉ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 “የእስራኤል ጠባቂዎች ዕውሮች ናቸው፤ ሁሉም ዕውቀት የላቸውም፤ እነርሱም፥ እንደሚያንቀላፉ፥ እንደሚጋደሙ፥ እንደሚያልሙና መጮኽ እንደማይችሉ ውሾች ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ጕበኞቹ ዕውሮች ናቸው፥ ሁሉ ያለ እውቀት ናቸው፥ ሁሉም ዲዳ የሆኑ ውሾች ናቸው ይጮኹም ዘንድ አይችሉም፥ ሕልምን ያልማሉ፥ ይተኛሉ፥ ማንቀላፋትም ይወድዳሉ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 56:10
24 Referencias Cruzadas  

ከው​ሾች ተጠ​በቁ፤ ከክፉ አድ​ራ​ጊ​ዎ​ችም ተጠ​በቁ፤ ሥጋ​ቸ​ውን ብቻ በመ​ቍ​ረጥ ተገ​ዝ​ረ​ናል ከሚ​ሉም ተጠ​በቁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ን​ቅ​ልፍ መን​ፈ​ስን አፍ​ስ​ሶ​ባ​ቸ​ዋል፤ ዐይ​ኖ​ቻ​ቸ​ውን፥ የነ​ቢ​ያ​ት​ንም ዐይን፥ የተ​ሰ​ወ​ረ​ው​ንም የሚ​ያዩ የአ​ለ​ቆ​ቻ​ቸ​ውን ዐይን ጨፍ​ኖ​ባ​ቸ​ዋል።


ተዉአቸው፤ ዕውሮችን የሚመሩ ዕውሮች ናቸው፤ ዕውርም ዕውርን ቢመራው ሁለቱም ወደ ጉድጓድ ይወድቃሉ፤” አለ።


የአሦር ንጉሥ ሆይ፥ እረኞችህ አንቀላፍተዋል፣ መኳንንቶችህም ዐርፈዋል፣ ሕዝብህም በተራሮች ላይ ተበትኖአል፥ የሚሰበስበውም የለም።


ጕበ​ኛው ግን ጦር ሲመጣ ቢያይ፥ መለ​ከ​ቱ​ንም ባይ​ነፋ፥ ሕዝ​ቡ​ንም ባያ​ስ​ጠ​ነ​ቅቅ፥ ጦርም መጥቶ አንድ ሰው ከእ​ነ​ርሱ ቢወ​ስድ፥ እርሱ በኀ​ጢ​አቱ ተወ​ስ​ዶ​አል፤ ደሙን ግን ከጕ​በ​ኛው እጅ እፈ​ል​ጋ​ለሁ።


በኀ​ይ​ልህ ጩኽ፤ አት​ቈ​ጥብ፤ ድም​ፅ​ህን እንደ መለ​ከት አንሣ፤ ለሕ​ዝቤ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን፥ ለያ​ዕ​ቆብ ቤትም በደ​ላ​ቸ​ውን ንገር።


ሕዝቤ አእ​ምሮ እን​ደ​ሌ​ላ​ቸው ይመ​ስ​ላሉ፤ አን​ተም አእ​ም​ሮህ ተለ​ይ​ቶ​ሃ​ልና እኔ ካህን እን​ዳ​ት​ሆ​ነኝ እተ​ው​ሃ​ለሁ፤ የአ​ም​ላ​ክ​ህ​ንም ሕግ ረስ​ተ​ሃ​ልና እኔ ደግሞ ልጆ​ች​ህን እረ​ሳ​ለሁ።


እነ​ር​ሱም ስለ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ትን​ቢት የሚ​ና​ገሩ፥ የሰ​ላ​ም​ንም ራእይ የሚ​ያ​ዩ​ላት የእ​ስ​ራ​ኤል ነቢ​ያት ናቸው፤ ሰላ​ምም የለም፥” ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እነሆ፥ የሚ​ጠ​ብ​ቁሽ ሰዎች ድምፅ ከፍ ከፍ ይላ​ልና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጽዮ​ንን ይቅር ባላት ጊዜ ዐይን በዐ​ይን ይተ​ያ​ያ​ሉና በአ​ን​ድ​ነት በቃ​ላ​ቸው ደስ ይላ​ቸ​ዋል።


ደከሙ፤ ደነ​ገ​ጡም፤ ሰከ​ሩም፤ በወ​ይን አይ​ይ​ደ​ለም፤ በጠ​ጅም አይ​ደ​ለም።


ኖን። እነ​ርሱ ታው​ረው በመ​ን​ገድ ላይ ተቅ​በ​ዘ​በዙ፤ ልብ​ሳ​ቸ​ውም እን​ዳ​ይ​ዳ​ሰስ በደም ረክ​ሰ​ዋል።


ነገር ግን እስከ ንጉሡ እስከ ኢዮ​አስ እስከ ሃያ ሦስ​ተ​ኛው ዓመት ድረስ ከመ​ቅ​ደሱ ውስጥ የተ​ና​ዱ​ትን ካህ​ናቱ አል​ጠ​ገ​ኑ​ትም ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios