ኀፍረትሽ ይገለጣል፤ ውርደትሽም ይታያል፤ ጽድቅ ከአንቺ ይወሰዳል፤ እንዲሁም በአንቺ ፋንታ ሰውን አሳልፌ አልሰጥም።
ኤርምያስ 13:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህም የልብስሽን ዘርፍ በስተኋላሽ ወደ ፊትሽ እገልጣለሁ እፍረትሽም ይታያል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ኀፍረትሽ እንዲገለጥ፣ ልብስሽን ፊትሽ ድረስ እገልባለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም የልብስሽን ዘርፍ በፊትሽ እገልጣለሁ እፍረትሽም ይታያል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ራሱ ልብሳችሁን ገፎ ኀፍረተ ሥጋችሁ እንዲጋለጥ ያደርጋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህም የልብስሽን ዘርፍ በፊትሽ እገልጣለሁ እፍረትሽም ይታያል። |
ኀፍረትሽ ይገለጣል፤ ውርደትሽም ይታያል፤ ጽድቅ ከአንቺ ይወሰዳል፤ እንዲሁም በአንቺ ፋንታ ሰውን አሳልፌ አልሰጥም።
በልብሽም፦ እንዲህ ያለ ነገር ስለ ምን ደረሰብኝ? ብትዪ፥ ከኀጢአትሽ ብዛት የተነሣ ልብስሽ በስተኋላሽ ተገፎአል፤ ተረከዝሽም ተገልጦአል።
እኔ ግን ዔሳውን አራቆትሁት፤ የተሸሸጉትንም ስፍራዎች ገለጥሁ፤ ይሸሸግም ዘንድ አይችልም፤ ዘሩም፤ ወንድሞቹም፤ ጎረቤቶቹም ጠፍተዋል፥ እርሱም የለም።
ሔት። ኢየሩሳሌም እጅግ ኀጢአት ሠርታለች፤ ስለዚህ ረክሳለች፤ በተጨነቀችበት ቦታ ያከብሩአት የነበሩ ሁሉ ውርደቷን አይተዋልና አቃለሉአት፤ እርስዋም እየጮኸች ታለቅሳለች፤ ወደ ኋላዋም ዘወር አለች።
ስለዚህ እነሆ እኔ ከአንቺ ጋር አንድ የሆኑ ውሽሞችሽን በአንቺ ላይ እሰበስባቸዋለሁ፤ የምትወጃቸውንም ከምትጠያቸው ጋር በአንቺ ላይ እሰበስባቸዋለሁ፤ ይከቡሻል፤ በእነርሱም ዘንድ ጕስቍልናሽን እገልጥብሻለሁ፤ ሁሉም ኀፍረትሽን ያዩብሻል።
እነርሱም በጥል ያደርጉብሻል፤ የደከምሽበትንም ሁሉ ይወስዳሉ፤ ዕራቁትሽንና ዕርቃንሽን አድርገውም ይተዉሻል፤ የግልሙትናሽንም ነውር፥ ሴሰኝነትሽንና ግልሙትናሽንም ሁሉ ይገልጣሉ።
እርስዋም፥ “ወዳጆች የሰጡኝ ዋጋዬ ይህ ነው” ያለችውን ሁሉ ወይንዋንና በለስዋን አጠፋለሁ፤ ምስክርም ይሆኑ ዘንድ አኖራቸዋለሁ፤ የምድረ በዳም አራዊትና የሰማይ ወፎች፥ የምድር ተንቀሳቃሾችም ይበሉታል።
እነሆ፥ በአንቺ ላይ ነኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ ልብስሽን በፊትሽ እገልጣለሁ፣ ኅፍረተ ሥጋሽንም ለአሕዛብ፥ ነውርሽንም ለመንግሥታት አሳያለሁ።