Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኤርምያስ 13:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ስለዚህም የልብስሽን ዘርፍ በፊትሽ እገልጣለሁ እፍረትሽም ይታያል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 “ኀፍረትሽ እንዲገለጥ፣ ልብስሽን ፊትሽ ድረስ እገልባለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 እግዚአብሔር ራሱ ልብሳችሁን ገፎ ኀፍረተ ሥጋችሁ እንዲጋለጥ ያደርጋል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ስለ​ዚ​ህም የል​ብ​ስ​ሽን ዘርፍ በስ​ተ​ኋ​ላሽ ወደ ፊትሽ እገ​ል​ጣ​ለሁ እፍ​ረ​ት​ሽም ይታ​ያል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ስለዚህም የልብስሽን ዘርፍ በፊትሽ እገልጣለሁ እፍረትሽም ይታያል።

Ver Capítulo Copiar




ኤርምያስ 13:26
9 Referencias Cruzadas  

እርሷም እህልንና ወይን ጠጅን ዘይትንም የሰጠኋት፥ ለበኣልም ያደረጉትን ብርና ወርቅ ያበዛሁላት እኔ እንደሆንኩ አላወቀችም።


ሔት። ኢየሩሳሌም እጅግ ኃጢአት ሠርታለች፥ ስለዚህ ረክሳለች፥ ያከብሩአት የነበሩ ሁሉ ኀፍረተ ሥጋዋን አይተዋታልና አቃለሉአት፥ እርሷም እየጮኸች ታለቅሳለች ወደ ኋላም ዘወር አለች።


እነርሱም በጥል ይቀርቡሻል፥ የድካምሽን ፍሬ ሁሉ ይወስዳሉ፥ ዕራቁትሽንና ዕርቃንሽን አድርገውም ይተዉሻል፥ የዝሙትሽ ዕራቁትነት፥ ሴሰኝነትሽና ግልሙትናሽ ይገለጣል።


ስለዚህ እነሆ እኔ ደስ የተሰኘሽባቸውን ወዳጆችሽን ሁሉ፥ የወደድሻቸውን ሁሉ ከጠላሻቸው ሁሉ ጋር እሰበስባቸዋለሁ፤ ሁሉንም ከየአቅጣጫው በአንቺ ላይ እሰበስባቸዋለሁ፥ ራቁትነትሽን ሁሉ እንዲያዩ በፊታቸው ዕርቃንሽን እገልጣለሁ።


በልብሽም፦ ‘እነዚህ ነገሮች ስለምን ደረሱብኝ?’ ብትዪ፥ ከኃጢአትሽ ብዛት የተነሣ የልብስሽ ዘርፍ ተገልጦአል ተረከዝሽም ተገፍፎአል።


እኔ ግን ዔሳውን ዐራቈትሁት፥ የመሸሸጊያውንም ስፍራዎች ገለጥሁ፥ እርሱም ለመሸሸግ አይችልም፤ ዘሩም ወንድሞቹም ጎረቤቶቹም ጠፍተዋል እርሱም የለም።


እነሆ፥ በአንቺ ላይ ነኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ፥ ልብስሽን እስከ ፊትሽ እገልጣለሁ፤ ኅፍረተ ሥጋሽን ለአሕዛብ፥ ነውርሽንም ለመንግሥታት አሳያለሁ።


ኀፍረተ ሥጋሽ ይገለጣል እፍረትሽም ይታያል፤ እኔ እበቀላለሁ፥ ለማንም አልራራም።


እንዲሁም አሁን ውሽሞችዋ እያዩ ነውርዋን እገልጣለሁ፤ ከእጄም ማንም አያድናትም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios