ኤርምያስ 13:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስሙ፤ አድምጡ፤ እግዚአብሔር ተናግሮአልና አትታበዩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ተናግሯልና፣ ስሙ፤ ልብ በሉ፤ ትዕቢተኛም አትሁኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስሙ፥ አድምጡም፤ ጌታ ተናግሮአልና አትታበዩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ተናግሮአልና፤ ትዕቢታችሁን አስወግዳችሁ ስሙት፤ በጥንቃቄም አድምጡት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስሙ፥ አድምጡ፥ እግዚአብሔር ተናግሮአልና አትታበዩ። |
እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናግሮአልና፥ “ሰማይ ስማ፤ ምድርም አድምጪ፤ ልጆችን ወለድሁ፤ አሳደግሁም፤ እነርሱም ዐመፁብኝ።
ነገር ግን ይህን ቃል ሁሉ በጆሮአችሁ እናገር ዘንድ በእውነቱ እግዚአብሔር ወደ እናንተ ልኮኛልና ብትገድሉኝ ንጹሕ ደምን በራሳችሁና በዚች ከተማ፥ በሚኖሩባትም ላይ እንድታመጡ በርግጥ ዕወቁ።”
እናንተ ሽማግሌዎች! ይህን ስሙ፤ በምድርም የምትኖሩ ሁሉ አድምጡ። ይህ በዘመናችሁ ወይስ በአባቶቻችሁ ዘመን ሆኖ ነበርን?