ኤርምያስ 12:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ለሕዝቤ ለእስራኤል ያወረስሁትን ርስት ለሚነኩት ክፉዎች ጎረቤቶች ሁሉ እንዲህ ይላልና፥ “እነሆ ከምድራቸው እነቅላቸዋለሁ፤ የይሁዳንም ቤት ከመካከላቸው እነቅለዋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ለሕዝቤ ለእስራኤል የሰጠሁትን ርስት የሚይዙትን ክፉ ጎረቤቶቼን ሁሉ ከምድራቸው እነቅላቸዋለሁ፤ የይሁዳንም ቤት ከመካከላቸው እነቅላለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ለሕዝቤ ለእስራኤል ያወረስሁትን ርስት ለሚነኩት ክፉዎች ጎረቤቶች ሁሉ እንዲህ ይላልና፦ “እነሆ፥ ከምድራቸው እነቅላቸዋለሁ፥ የይሁዳንም ቤት ከመካከላቸው እነቅለዋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ለሕዝቤ ለእስራኤል የሰጠኋቸውን ምድር ስላጠፉት ስለ እስራኤል ጐረቤቶችም የምናገረው ነገር አለኝ፤ እነዚያን ክፉ ሕዝቦች ከየአገራቸው ነቃቅዬ እወስዳቸዋለሁ፤ የይሁዳንም ሕዝብ ከመካከላቸው መንጥቄ አወጣቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ለሕዝቤ ለእስራኤል ያወረስሁትን ርስት ለሚነኩት ክፉዎች ጐረቤቶች ሁሉ እንዲህ ይላልና፦ እነሆ፥ ከምድራቸው እነቅላቸዋለሁ፥ የይሁዳንም ቤት ከመካከላቸው እነቅለዋለሁ። |
እስራኤል ለእግዚአብሔር ቅዱስ ነበረ፤ የቡቃያው በኵራትም ነበረ፤ የበሉት እንደ በደለኞች ይቈጠራሉ፤ ክፉም ነገር ያገኛቸዋል፤ ይላል እግዚአብሔር።”
እነሆ ልኬ የሰሜንን ወገኖች ሁሉ፤ ባሪያዬንም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆርን እወስዳለሁ፤ በዚችም ምድርና በሚቀመጡባትም ሰዎች ላይ፥ በዙሪያዋም ባሉ በእነዚህ አሕዛብ ሁሉ ላይ አመጣቸዋለሁ፤ ፈጽሜም አጠፋቸዋለሁ፤ ለጥፋትና ለፉጨት ለዘለዓለምም ዕፍረት ባድማ አደርጋቸዋለሁ።
በዚያም ዘመን የይሁዳ ቤት ወደ እስራኤል ቤት ይሄዳል፤ በአንድም ሆነው ከሰሜን ምድር ርስት አድርጌ ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠኋት ምድር ይመጣሉ።
እነሆ በቍጣዬና በመዓቴ፥ በታላቅም መቅሠፍቴ እነርሱን ካሳደድሁባት ሀገር ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ፤ ወደዚህም ስፍራ እመልሳቸዋለሁ፤ ተዘልለውም እንዲኖሩ አደርጋለሁ፤
ስለ ሞአብ፤ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ናባው ጠፍታለችና ወዮላት! ቂርያታይም አፍራለች፤ ተይዛማለች፤ መጠጊያዋም አፍራለች፤ ደንግጣማለች።
ስለ አሞን ልጆች እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ሚልኮም ጋድን ይወርስ ዘንድ ሕዝቡም በከተሞቹ ላይ ይቀመጥ ዘንድ ለእስራኤል ልጆች የሉትምን? ወይስ ወራሽ የለውምን?
ስለ ኤዶምያስ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በውኑ በቴማን ጥበብ የለምን? ከብልሃተኞችስ ምክር ጠፍቶአልን? ጥበባቸውስ አልቆአልን?
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የእስራኤልን ቤት ከተበተኑባቸው አሕዛብ ዘንድ እሰበስባቸዋለሁ፤ በአሕዛብና በሕዝብ ፊትም እቀደስባቸዋለሁ፤ ለባሪያዬ ለያዕቆብም በሰጠኋት ምድራቸው ይቀመጣሉ።
ተዘልለውም ይቀመጡባታል፤ ቤቶችንም ይሠራሉ፤ ወይኑንም ይተክላሉ፤ በዙሪያቸውም በአሉ በሚንቋቸው ሁሉ ላይ ፍርድን በአደረግሁ ጊዜ ተዘልለው ይቀመጣሉ፤ እኔም እግዚአብሔር አምላካቸው፥ የአባቶቻቸውም አምላክ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
ከአሕዛብም መካከል አወጣችኋለሁ፤ ከየሀገሩም ሁሉ እሰበስባችኋለሁ፤ ወደ ገዛ ምድራችሁም እመልሳችኋለሁ።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያሳድዱአትና ይበዘብዙአት ዘንድ በልባቸው ሁሉ ደስታና በነፍሳቸው ንቀት ምድሬን ርስት አድርገው ለራሳቸው በሰጡ በቀሩት አሕዛብና በኤዶምያስ ሁሉ ላይ በቅንአቴ እሳት ተናግሬአለሁ፤
አንተም እንዲህ ትላቸዋለህ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ የእስራኤልን ልጆች ከገቡባቸው ከአሕዛብ መካከል እወስዳለሁ፤ ከስፍራም ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ፤ ወደ እስራኤልም ምድር አመጣቸዋለሁ፤
የይሁዳ ልጆችና የእስራኤል ልጆች በአንድነት ይሰበሰባሉ፤ ለእነርሱም አንድ አለቃ ይሾማሉ፤ ከምድሪቱም ይወጣሉ፤ የኢይዝራኤል ቀን ታላቅ ይሆናልና።
እግዚአብሔርም በጎ ያደርግልህ ዘንድ፥ ያበዛህም ዘንድ ደስ ይለው እንደ ነበረ፥ እንዲሁ እግዚአብሔር ሲያጠፋህ፥ ሲያፈርስህም ደስ ይለዋል፤ ትወርሳትም ዘንድ ከምትገባባት ምድር ትነቀላለህ ።
እግዚአብሔርም ኀጢአትህን ይቅር ይልሃል ይራራልህማል፤ እግዚአብሔርም አንተን ከበተነበት ከአሕዛብ ሁሉ መካከል መልሶ ይሰበስብሃል።