ኤርምያስ 12:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 ጌታ ለሕዝቤ ለእስራኤል ያወረስሁትን ርስት ለሚነኩት ክፉዎች ጎረቤቶች ሁሉ እንዲህ ይላልና፦ “እነሆ፥ ከምድራቸው እነቅላቸዋለሁ፥ የይሁዳንም ቤት ከመካከላቸው እነቅለዋለሁ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ለሕዝቤ ለእስራኤል የሰጠሁትን ርስት የሚይዙትን ክፉ ጎረቤቶቼን ሁሉ ከምድራቸው እነቅላቸዋለሁ፤ የይሁዳንም ቤት ከመካከላቸው እነቅላለሁ፤ Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ለሕዝቤ ለእስራኤል የሰጠኋቸውን ምድር ስላጠፉት ስለ እስራኤል ጐረቤቶችም የምናገረው ነገር አለኝ፤ እነዚያን ክፉ ሕዝቦች ከየአገራቸው ነቃቅዬ እወስዳቸዋለሁ፤ የይሁዳንም ሕዝብ ከመካከላቸው መንጥቄ አወጣቸዋለሁ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 እግዚአብሔር ለሕዝቤ ለእስራኤል ያወረስሁትን ርስት ለሚነኩት ክፉዎች ጎረቤቶች ሁሉ እንዲህ ይላልና፥ “እነሆ ከምድራቸው እነቅላቸዋለሁ፤ የይሁዳንም ቤት ከመካከላቸው እነቅለዋለሁ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 እግዚአብሔር ለሕዝቤ ለእስራኤል ያወረስሁትን ርስት ለሚነኩት ክፉዎች ጐረቤቶች ሁሉ እንዲህ ይላልና፦ እነሆ፥ ከምድራቸው እነቅላቸዋለሁ፥ የይሁዳንም ቤት ከመካከላቸው እነቅለዋለሁ። Ver Capítulo |