ወደ ግብዣ ቤትም ከመሄድ ወደ ልቅሶ ቤት መሄድ ይሻላል፤ እርሱ የሰው ሁሉ ፍጻሜ ነውና፥ ሕያውም የሆነ ይህን መልካም ነገር በልቡ ያኖረዋል።
ኤርምያስ 12:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋም ለፍጹም ጥፋት ሆናለች፤ ስለ እኔም ምድር ሁሉ ባድማ ሆናለች፤ በልቡም የሚያኖራት የለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በፊቴ ባድማ፣ ደረቅና ወና ይሆናል፤ መላዪቱም ምድር ጠፍ ትሆናለች፤ ስለ እርሷ የሚገድደው የለምና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባድማ አድርገውታል፥ ፈርሶም ወደ እኔ ያለቅሳል፤ ምድር ሁሉ ባድማ ሆናለች በልቡም የሚያስባት ማንም የለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምድረ በዳም ስላደረጉአት በፊቴ ባድማ ሆናለች፤ አገሪቱ በሙሉ ወደ በረሓነት ተለውጣለች፤ ስለ እርስዋም የሚገደው አንድ እንኳ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባድማ አድርገውታል፥ ፈርሶም ወደ እኔ ያለቅሳል፥ ምድር ሁሉ ባድማ ሆናለች በልቡም የሚያስባት የለም። |
ወደ ግብዣ ቤትም ከመሄድ ወደ ልቅሶ ቤት መሄድ ይሻላል፤ እርሱ የሰው ሁሉ ፍጻሜ ነውና፥ ሕያውም የሆነ ይህን መልካም ነገር በልቡ ያኖረዋል።
ስለዚህ የቍጣውን መዓትና የሰልፉን ጽናት አመጣባቸው፤ በዙሪያቸው አቃጠላቸው፤ እነርሱ ግን አላወቁም፤ በልባቸውም አላስተዋሉም።
ጻድቅ ሰው እንደጠፋ አያችሁ፤ ይህንም በልባችሁ አላሰባችሁም፤ ጻድቃን ሰዎች ይወገዳሉ፤ ጻድቅም ከክፋት ፊት እንደ ተወገደ ማንም አያስተውልም።
የወሬ ድምፅ ተሰማ፤ እነሆም የይሁዳን ከተሞች ባድማና የሰገኖ ማደሪያ ያደርጋቸው ዘንድ ከሰሜን ምድር ታላቅ መነዋወጥ መጥቶአል።
ያዕቆብን በልተውታልና፥ አጥፍተውትማልና፥ ማደሪያውንም አፍርሰዋልና በማያውቁህ አሕዛብ፥ ስምህንም በማይጠሩ ትውልድ ላይ መዓትህን አፍስስ።
ይህችንም ከተማ ለጥፋትና ለማፍዋጫ አደርጋታለሁ፤ በእርስዋም የሚያልፍ ሁሉ ስለ ተደረገባት መቅሠፍት ሁሉ ይደነግጣል፤ ያፍዋጫልም።
ዝሙታቸው ምድርን ሞልትዋልና፥ ከመርገም ፊት የተነሣ ምድር አልቅሳለች፤ የምድረ በዳ ማሰሪያው ሁሉ ደርቆአል፤ ሥራቸውና ድካማቸው ከንቱ ሆነ።
ስለዚህ ምድር ታለቅሳለች፤ በላይም ሰማይ ይጠቍራል፤ ተናግሬአለሁና፤ አልጸጸትም ወደፊት እሮጣለሁ፤ ከእርስዋም አልመለስም።
በተራሮቹ ላይ አልቅሱ፤ በምድረ በዳም ጎዳና ላይ እዘኑ፤ ሰው ጠፍትዋልና፤ የሚመላለስም የለምና ሙሾውንም አሙሹ፤ የሰማይ ወፍ ድምፅንም እስከ ከብት ድምፅ ድረስ አይሰሙም፤ ደንግጠውም ተማርከው ሄዱ።
ኢየሩሳሌምንም የፍርስራሽ ክምር፥ የቀበሮም ማደሪያ አደርጋታለሁ፤ የይሁዳንም ከተሞች ሰው እንዳይቀመጥባቸው አጠፋቸዋለሁ።
በውኑ ስለዚህ ነገር በመቅሠፍት አልጐበኝምን? ይላል እግዚአብሔር፤ ነፍሴስ እንደዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አትበቀልምን?
ለምድሩ ሕዝብ ሁሉ ለካህናትም እንዲህ ብለህ ተናገራቸው፦ በዚህ በሰባው ዓመት በአምስተኛውና በሰባተኛው ወር በጾማችሁና ባለቀሳችሁ ጊዜ፥ በውኑ ለእኔ ጾም ጾማችሁልኝ?
ለስሜ ክብር ትሰጡ ዘንድ ባትሰሙ፥ በልባችሁም ባታደርጉት፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ እርግማን እሰድዳባችኋለሁ፥ በረከታችሁንም እረግማታለሁ፣ አሁንም በልባችሁ አላደረጋችሁትምና እኔ ረግሜአታለሁ።