አቤቱ ይህ ለአንተ አግባብ አይደለም፤ ይህን ነገር አታድርግ፤ ጻድቃንን ከኃጥኣን ጋር አታጥፋ፤ ምድርን ሁሉ የምትገዛ ይህን ፍርድ ታደርግ ዘንድ ለአንተ አግባብ አይደለም።”
ኤርምያስ 12:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ! ከአንተ ጋር በተምዋገትሁ ጊዜ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ነገር ግን ከአንተ ጋር ስለ ፍርድ ልናገር። የኀጢአተኞች መንገድ ስለ ምን ይቀናል? በደልንስ የሚያደርጉ ሁሉ ስለ ምን ደስ ይላቸዋል? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ጕዳዬን በፊትህ ሳቀርብ፣ አንተ ጻድቅ መሆንህን እያወቅሁ ነው። የክፉዎች መንገድ ለምን ይሰምራል? የከዳተኞችስ ኑሮ ለምን ይሳካል? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ! ከአንተ ጋር በተምዋገትሁ ጊዜ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ነገር ግን ከአንተ ጋር ስለ ፍርድ ልናገር። የኃጢአተኞች መንገድ ስለምን ይቃናል? በደልንስ ለሚበድሉ ሁሉ ስለምን ደኅንነት ይሆናል? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! ከአንተ ጋር በምከራከርበት ጊዜ ሁሉ አንተ ትክክለኛ ነህ፤ አሁን ግን ስለ ትክክለኛ ፍርድ ጥያቄ አለኝ፤ የኃጢአተኛ ሕይወት የተቃና የሚሆንበት ምክንያት ምንድን ነው? አታላዮችስ ሁሉ ነገር የሚሳካላቸው ስለምንድን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤቱ፥ ከአንተ ጋር በተምዋገትሁ ጊዜ አንተ ጻድቅ ነህ፥ ነገር ግን ከአንተ ጋር ስለ ፍርድ ልናገር። የኃጢአተኞች መንገድ ስለምን ይቃናል? በደልንስ ለሚያደርጉ ሁሉ ስለምን ደኅንነት ይሆናል? |
አቤቱ ይህ ለአንተ አግባብ አይደለም፤ ይህን ነገር አታድርግ፤ ጻድቃንን ከኃጥኣን ጋር አታጥፋ፤ ምድርን ሁሉ የምትገዛ ይህን ፍርድ ታደርግ ዘንድ ለአንተ አግባብ አይደለም።”
አቤቱ የእስራኤል አምላክ ሆይ፥ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ዛሬም እንደ ሆነው እኛ አምልጠን ቀርተናል፤ እነሆ በፊትህ በበደላችን አለን፤ ስለዚህ በፊትህ ሊቆም የሚችል የለም።”
ከፀሓይ በታች በምድር የሚደረግ ከንቱ ነገር አለ፥ በኃጥኣን የሚደረገው ሥራ የሚደርስባቸው ጻድቃን አሉ፥ ለጻድቃንም የሚደረገው ሥራ የሚደርስላቸው ኃጥኣን አሉ፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው አልሁ።
አላወቅህም፤ አላስተዋልህም፤ ጆሮህን ከጥንት አልከፈትሁልህም፤ አንተ ፈጽሞ ወንጀለኛ እንደ ሆንህ፥ ከማኅፀንም ጀምረህ ተላላፊ ተብለህ እንደ ተጠራህ ዐውቄአለሁና።
ኵላሊትንና ልብን የምትፈትን፥ በቅንም የምትፈርድ እግዚአብሔር ሆይ! ክርክሬን ገልጬልሃለሁና ከእነርሱ ፍረድልኝ።
ወንድሞችህና የአባትህ ቤት እነርሱ ጭምር ክደውሃልና፥ ጮኸውም በስተኋላህ ተሰበሰቡ፤ በመልካምም ቢናገሩህ አትመናቸው።
ሁሉም አመንዝሮች፥ የዐመጸኞች ጉባኤ ናቸውና ሕዝቤን እተዋቸው ዘንድ ከእነርሱም እለይ ዘንድ በምድረ በዳ ማደሪያን ማን በሰጠኝ?
ጻዴ። ቃሉን አማርሬአለሁና እግዚአብሔር ጻድቅ ነው። እናንተ አሕዛብ ሁሉ እባካችሁ ስሙ፤ መከራዬንም ተመልከቱ፤ ደናግሎችና ጐልማሶች ተማርከው ሄደዋልና።
“እናንተ ግን፦ የጌታ መንገድ የቀናች አይደለችም ትላላችሁ። የእስራኤል ቤት ሆይ! እንግዲህ ስሙ፤ በውኑ መንገዴ የቀናች አይደለችምን? ይልቅስ የእናንተ መንገድ ያልቀናች አይደለችምን?
እግዚአብሔር በውስጥዋ ጻድቅ ነው፣ ክፋትን አያደርግም፣ ፍርዱን በየማለዳው ወደ ብርሃን ያወጣል፥ ሳያወጣውም አይቀርም፣ ዓመፀኛው ግን እፍረትን አያውቅም።
እግዚአብሔርን በቃላችሁ አታክታችኋል። እናንተም፦ ያታከትነው በምንድር ነው? ብላችኋል። ክፉን የሚያደርግ ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ መልካም ነው፥ እርሱም በእነርሱ ደስ ይለዋል፣ ወይስ፦ የፍርድ አምላክ ወዴት አለ? በማለታችሁ ነው።
እግዚአብሔር በሥራው እውነተኛ ነው፤ መንገዱም ሁሉ የቀና ነው፤ እግዚአብሔር የታመነ ነው፤ ክፋትም የለበትም፤ እግዚአብሔር ጻድቅና ቸር ነው።