Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢዮብ 12:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ያ​ስ​ቈ​ጡ​ትን ሰዎች፥ እርሱ የሚ​መ​ረ​ም​ራ​ቸው አይ​ደ​ለ​ምን?

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 የቀማኞች ድንኳን አይታወክም፤ አምላካቸውን በእጃቸው ይዘው እየዞሩም፣ እግዚአብሔርንም እያስቈጡ በሰላም ይኖራሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 የቀማኞች ድንኳን በደኅንነት ይኖራል፥ እግዚአብሔርንም የሚያስቈጡ ተዝናንተው ተቀምጠዋል፥ እግዚአብሔር ሁሉን በእጃቸው አምጥቶላቸዋል።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ኀይላቸውን እንደ አምላክ አድርገው የሚቈጥሩ ሌቦችና እግዚአብሔርን የካዱ ሰዎች እንኳ በሰላም ይኖራሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 የቀማኞች ድንኳን በደኅንነት ይኖራል፥ እግዚአብሔርንም የሚያስቈጡ ተዘልለው ተቀምጠዋል፥ እግዚአብሔር ሁሉን በእጃቸው አምጥቶላቸዋል።

Ver Capítulo Copiar




ኢዮብ 12:6
17 Referencias Cruzadas  

እርሱ በተ​ወ​ሰ​ነው ዕድሜ በሌ​ሎች እን​ዲ​ወ​ድቅ፥ ቤቱም በኃ​ጥ​ኣን እን​ዲ​ፈ​ርስ ተዘ​ጋ​ጅቶአል። ነገር ግን ማንም ክፉ ሆኖ ንጹሕ እን​ደ​ሚ​ሆን አይ​መን።


“አሁን ግን እን​ስ​ሶ​ችን ጠይቅ፥ ያስ​ተ​ም​ሩ​ህ​ማል፤ የሰ​ማ​ይ​ንም ወፎች ጠይቅ፥ ይነ​ግ​ሩ​ህ​ማል።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በቍጣ ትመ​ልስ ዘንድ፤ እን​ደ​ዚ​ህስ ያለ ነገር ከአ​ፍህ ታወጣ ዘንድ፤


ነገር ግን ቤታ​ቸ​ውን በመ​ል​ካም ነገር ሞላ፤ የኃ​ጥ​ኣን ምክር ከእ​ርሱ የራ​ቀች ናት።


በታ​መ​መም ጊዜ መዳ​ንን ተስፋ አያ​ደ​ር​ግም። ነገር ግን እርሱ በሕ​ማሙ ይሞ​ታል።


በኃ​ጥ​ኣን እጅ ተሰ​ጥ​ተ​ዋ​ልና፤ የም​ድር ፈራ​ጆ​ችን ፊት ይሸ​ፍ​ናል፤ እርሱ ካል​ሆነ ማን ነው?


ፍላ​ጻ​ውን ላከ፥ በተ​ና​ቸ​ውም፤ መብ​ረ​ቆ​ችን አበዛ አወ​ካ​ቸ​ውም።


አቤቱ፥ በመ​ዓ​ትህ አት​ቅ​ሠ​ፈኝ፥ በመ​ቅ​ሠ​ፍ​ት​ህም አት​ገ​ሥ​ጸኝ።


ጠላት በቅ​ዱ​ሳ​ንህ ላይ እንደ ከፋ መጠን፥ ሁል​ጊዜ በት​ዕ​ቢ​ታ​ቸው ላይ እጅ​ህን አንሣ።


አቤቱ! ከአ​ንተ ጋር በተ​ም​ዋ​ገ​ትሁ ጊዜ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ነገር ግን ከአ​ንተ ጋር ስለ ፍርድ ልና​ገር። የኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች መን​ገድ ስለ ምን ይቀ​ናል? በደ​ል​ንስ የሚ​ያ​ደ​ርጉ ሁሉ ስለ ምን ደስ ይላ​ቸ​ዋል?


ቀፎ ወፎ​ችን እን​ደ​ሚ​ሞላ፥ እን​ዲሁ ቤታ​ቸው ሽን​ገ​ላን ሞል​ታ​ለች፤ በዚ​ህም ከብ​ረ​ዋል ባለ​ጸ​ጎ​ችም ሆነ​ዋል።


ፍር​ድን አጣ​መሙ ለድ​ሃ​አ​ደ​ጎች ፍር​ድን አል​ፈ​ረ​ዱም፤ ለመ​በ​ለ​ቷም አል​ተ​ሟ​ገ​ቱም።


የዚያን ጊዜም እንደ ነፋስ አልፎ ይሄዳል፥ ይበድልማል፣ ኃይሉንም አምላክ ያደርገዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos