ኢሳይያስ 8:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከይሁዳ ወንድ ሰውን ሁሉ ያጠፋል፤ ኀያላኑንም ይጨርሳል፤ ሰፈሩም በሰፊው ምድርና በሀገሮቻቸው ሁሉ ይሞላል፤” እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነውና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እየጠራረገ ወደ ይሁዳ ይወርዳል፤ እያጥለቀለቀ ያልፋል፤ እስከ ዐንገትም ይደርሳል፤ ዐማኑኤል ሆይ! የተዘረጉ ክንፎቹ ምድርህን ከዳር እስከ ዳር ይሸፍናሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እየጠራረገ ወደ ይሁዳ ይወርዳል፤ እያጥለቀለቀ ያልፋል፤ እስከ ዐንገትም ይደርሳል፤ አማኑኤል ሆይ፤ የተዘረጉ ክንፎቹ ምድርህን ከዳር እስከ ዳር ይሸፍናሉ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በኀይል እየጐረፈም ወደ ይሁዳ ምድር ይገባል፤ ሁሉን ነገር አጥለቅልቆ ከመሸፈን አልፎ ሙላቱ እስከ አንገት ይደርሳል፤” ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው፤ እርሱም ዶሮ ጫጩቶችዋን በክንፎችዋ ሰውራ እንደምትጠብቅ ምድሪቱን ይጠብቃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እየጎረፈም ወደ ይሁዳ ይገባል፥ እያጥለቀለቀም ያልፋል፥ እስከ አንገትም ይደርሳል፥ አማኑኤል ሆይ፥ የክንፉ መዘርጋት የአገርህን ስፋት ትሞላለች። |
ቍጣዬን በኀጢአተኛ ሕዝብ ላይ እልካለሁ፤ ይማርኳቸውና ይበዘብዙአቸው ዘንድ፥ ከተሞችንም ይረግጡአቸውና እንደ ትቢያ ያደርጓቸው ዘንድ ሕዝቤን አዝዛለሁ።
እስትንፋሱም አሕዛብን ስለ ከንቱ ስሕተታቸው ሊከፋፍላቸው በሸለቆ እንደሚያጥለቀልቅ፥ እስከ አንገትም እንደሚደርስና እንደሚከፋፍል ውኃ ይጐርፋል፤ ስሕተታቸውም ይከተላቸዋል፤ ይወስዳቸዋልም።
በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ ወንዞችም አያሰጥሙህም፤ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም፤ ነበልባሉም አይፈጅህም።
ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅንም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።
እግዚአብሔርም ኤፍሬም ከይሁዳ ከተለየበት ቀን ጀምሮ ያልመጣውን ዘመን በአንተና በሕዝብህ በአባትህም ቤት ላይ ያመጣል፤ እርሱም የአሦር ንጉሥ መምጣት ነው።”
ምክርን ብትመክሩም እግዚአብሔር ምክራችሁን ይለውጣል፤ የተናገራችሁትም ነገር አይሆንላችሁም። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነውና።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እነሆ ውኃ ከሰሜን ይነሣል፥ የሚያጥለቀልቅም ፈሳሽ ይሆናል፤ በሀገሪቱና በመላዋ ሁሉ፥ በከተማዪቱና በሚኖሩባትም ላይ ይጐርፋል፤ ሰዎቹም ይጮኻሉ፤ በምድርም የሚኖሩ ሁሉ ያለቅሳሉ።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ታላቅ ክንፍ፥ ረጅምም ጽፍር ያለው፥ ላባንም የተሞላ፥ መልከ ዝንጉርጉር የሆነ ታላቅ ንስር ወደ ሊባኖስ መጣ፤ የዝግባንም ጫፍ ወሰደ።
“ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ሰው እንደሌለባቸው ከተሞች ባድማ ከተማ ባደረግሁሽ ጊዜ፥ ቀላዩንም ባወጣሁብሽ ጊዜ፥ ብዙ ውኆችም በከደኑሽ ጊዜ፥
“እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል፤” የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፤ ትርጓሜውም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው፤” የሚል ነው።