ኢሳይያስ 8:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ታችም ወደ ምድር ትመለከታላችሁ፤ ድቅድቅ ጨለማንም ታያላችሁ፤ ታላቅ መከራንም ትቀበላላችሁ፤ ትጨነቃላችሁ፤ ትቸገራላችሁም፤ በፊታችሁም ጨለማ ይሆናል፤ አታዩምም፤ በመከራም ያለ ጊዜው እስኪደርስ አይድንም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ወደ ምድር ይመለከታሉ፣ የሚያዩትም ጭንቀት፣ ጨለማና የሚያስፈራም ጭጋግ ብቻ ነው፤ ወደ ድቅድቅ ጨለማም ይጣላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ወደ ምድር ይመለከታሉ፤ የሚያዩትም ጭንቀት፤ ጨለማና የሚያስፈራም ጭጋግ ብቻ ነው፤ ወደ ድቅድቅ ጨለማም ይጣላሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያ በኋላ ወደ ምድር ሲመለከቱ ሊያዩ የሚችሉት ጭንቀት ጨለማና ጭፍግግ ያለ አስፈሪ ሁኔታን ነው፤ ወደ ድቅድቅ ጨለማም ይጣላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ምድርም ይመለከታሉ፥ እነሆም፥ መከራና ጨለማ የሚያስጨንቅም ጭጋግ አለ፥ ወደ ድቅድቅም ጨለማ ይሰደዳሉ። |
ተባትና እንስት አንበሳ፥ እፉኝትም፥ ነዘር እባብም፥ በሚወጡባት በመከራና በጭንቀት ምድር በኩል ብልጽግናቸውን በአህዮች ጫንቃ ላይ፥ መዛግብቶቻቸውንም በግመሎች ሻኛ ላይ እየጫኑ ወደማይጠቅሙአቸው ሕዝብ ይሄዳሉ።
እነሆ፥ እሳት የምታነድዱ፥ የእሳትንም ነበልባል ከፍ ያደረጋችሁ ሁላችሁ፥ በእሳታችሁ ብርሃንና ባነደዳችሁት ነበልባል ሂዱ፤ ስለ እኔ ይህ ይሆንባችኋል፤ በኀዘንም ትተኛላችሁ።
ስለዚህ ፍርድ ከእነርሱ ዘንድ ርቆአል፤ ጽድቅም አላገኛቸውም፤ ብርሃንን ሲጠባበቁ ብርሃናቸው ጨለማ ሆነባቸው፤ ብርሃንንም ሲጠባበቁ በጨለማ ሄዱ፤
እነሆ፥ ጨለማ ምድርን፥ ድቅድቅ ጨለማም አሕዛብን ይሸፍናል፤ ነገር ግን በአንቺ ላይ እግዚአብሔር ይገለጣል፤ ክብሩም በአንቺ ላይ ይታያል፤
የዚህም ጊዜው እስከሚደርስ የተቸገረው ሁሉ አያመልጥም፤ በመጀመሪያው ዘመን የዛብሎንንና የንፍታሌምን ምድር አቃለለ፤ በኋለኛው ዘመን ግን በዮርዳኖስ ማዶ በባሕር መንገድ ያለውን የአሕዛብን ገሊላ ያከብራል።
ሳይጨልምባችሁ፥ ጨለማም ባለባቸው ተራሮች እግሮቻችሁ ሳይሰነካከሉ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ክብርን ስጡ፤ በዚያም የሞት ጥላ አለና በጨለማውም ውስጥ ያኖራችኋልና ብርሃንን ተስፋ ታደርጋላችሁ።
ስለዚህ መንገዳቸው ድጥና ጨለማ ትሆንባቸዋለች፤ እነርሱም ፍግምግም ብለው ይወድቁባታል፤ እኔም በምጐበኛቸው ዓመት ክፉ ነገርን አመጣባቸዋለሁና፥” ይላል እግዚአብሔር።