ኢሳይያስ 63:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምበቀልበት ቀን ደርሶባቸዋልና፥ የምቤዥበትም ዐመት ደርሶአልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የበቀል ቀን በልቤ አለ፤ የምቤዥበትም ዓመት ደርሷል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምበቀልበት ቀን በልቤ ነውና፥ የምቤዥበትም ዓመት ደርሶአልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምበቀልበትን ጊዜ ወስኜአለሁ፤ ሕዝቤን የምታደግበትም ጊዜ ደርሶአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የምበቀልበት ቀን በልቤ ነውና፥ የምቤዥበትም ዓመት ደርሶአልና። |
ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ለእስራኤል ኀያላን ወዮላቸው! በጠላቶች ላይ ቍጣዬ አይበርድም፤ ጠላቶችንም እበቀላለሁ።
እነሆ፥ ምድሪቱን ባድማ ሊያደርግ፥ ኀጢአተኞችዋንም ከእርስዋ ዘንድ ሊያጠፋ በመዓትና በጽኑ ቍጣ ተሞልቶ የእግዚአብሔር ቀን ይመጣል።
እናንተ አእምሮ የሌላችሁ፥ ልቡናችሁን አረጋጉ፤ ጽኑ፤ አትፍሩ፤ እነሆ፥ አምላካችን ፍርድን ይመልሳል፤ ይበቀላልም፤ እርሱም መጥቶ ያድነናል።
ኀፍረትሽ ይገለጣል፤ ውርደትሽም ይታያል፤ ጽድቅ ከአንቺ ይወሰዳል፤ እንዲሁም በአንቺ ፋንታ ሰውን አሳልፌ አልሰጥም።
የተወደደችውን የእግዚአብሔርንም ዓመት የተመረጠች ብዬ እጠራት ዘንድ፥ አምላካችንም የሚበቀልበትን ቀን እናገር ዘንድ፥ የሚያለቅሱትንም ሁሉ አጽናና ዘንድ፥
እጆችዋ ደክመዋልና ክበቡአት፤ ግንቧ ወድቋል፤ ቅጥርዋም ፈርሶአል፤ የእግዚአብሔርም በቀል ነውና ተበቀሏት፤ እንደ ሠራችውም ሥሩባት።
ከባቢሎን መካከል ሽሹ፤ እያንዳንዳችሁም ነፍሳችሁን አድኑ፤ በበደልዋ አትጥፉ፤ የእግዚአብሔር በቀል ጊዜ ነውና፥ እርሱም ብድራቷን ይከፍላታልና።
በሕዝቤ በእስራኤል እጅ ኤዶምያስን እበቀላለሁ፤ እንደ ቍጣዬና እንደ መዓቴም መጠን በኤዶምያስ ያደርጋሉ፤ በቀሌንም ያውቃሉ፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ታላቁ ካህን ኢያሱ ሆይ፥ ስማ፣ በፊትህም የሚቀመጡት ባልንጀሮች ለምልክት የሚሆኑ ሰዎች ናቸውና ይስሙ፣ እነሆ፥ እኔ ባሪያዬን ቍጥቋጥ አወጣለሁ።
በዚያም ሰዓት ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ከከተማይቱም ዐሥረኛው እጅ ወደቀ፤ በመናወጥም ሰባት ሺህ ሰዎች ተገደሉ፤ የቀሩትንም ፍርሃት ያዛቸው፤ ለሰማዩም አምላክ ክብር ሰጡ።