Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 52:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “በከ​ንቱ ተሸ​ጣ​ችሁ ነበር፤ ያለ ወር​ቅም እቤ​ዣ​ች​ኋ​ለሁ።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ያለ ዋጋ ተሸጣችሁ ነበር፤ ያለ ገንዘብ ትቤዣላችሁ።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ጌታ እንዲህ ይላል፦ በከንቱ ተሽጣችሁ ነበር፥ ያለ ገንዘብም ትቤዣላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 እግዚአብሔር ሕዝቡን እንዲህ ይላል፦ “ለባርነት ያለ ዋጋ ተሸጣችሁ ነበር፤ የምትዋጁትም ዋጋ ሳይከፈል ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በከንቱ ተሽጣችሁ ነበር፥ ያለ ገንዘብም ትቤዣላችሁ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 52:3
13 Referencias Cruzadas  

የጢ​ሮስ ሴቶች ልጆች እጅ መን​ሻን ይዘው ይሰ​ግ​ዱ​ለ​ታል። የም​ድር ባለ​ጠ​ጎች አሕ​ዛብ ሁሉ በፊ​ትሽ ይማ​ለ​ላሉ።


ለሐ​ሴ​ቦን ንጉሥ ሴት ልጅ ሁሉ ክብ​ርዋ ነው፤ በወ​ርቀ ዘቦ ልብስ የተ​ጐ​ና​ጸ​ፈ​ችና የተ​ሸ​ፋ​ፈ​ነች ናት።


ምር​ኮ​ኞ​ችሽ በእ​ው​ነ​ትና በም​ጽ​ዋት ይድ​ናሉ።


እኔ ቂሮ​ስን በጽ​ድቅ አስ​ነ​ሥ​ቼ​ዋ​ለሁ፤ መን​ገ​ዱ​ንም ሁሉ አቀ​ና​ለሁ፤ እርሱ ከተ​ማ​ዬን ይሠ​ራል፤ በዋ​ጋም ወይም በጉቦ ሳይ​ሆን ምር​ኮ​ኞ​ችን ያወ​ጣል፥ ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እና​ታ​ች​ሁን የፈ​ታ​ሁ​በት የፍ​ችዋ ደብ​ዳቤ የት አለ? ወይስ እና​ን​ተን የሸ​ጥሁ ከአ​በ​ዳ​ሪ​ዎች ለማን ነው? እነሆ፥ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችሁ ተሸ​ጣ​ች​ኋል፤ ስለ በደ​ላ​ች​ሁም እና​ታ​ችሁ ተፈ​ት​ታ​ለች።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “የተ​ቤ​ዣ​ቸው፥ የተ​ቀ​ደሰ ሕዝብ” ብለው ይጠ​ሩ​አ​ቸ​ዋል፤ አን​ቺም፥ “የተ​ተ​ወች ያይ​ደ​ለች የተ​ወ​ደ​ደች ቅድ​ስት ከተማ” ትባ​ያ​ለሽ።


የም​በ​ቀ​ል​በት ቀን ደር​ሶ​ባ​ቸ​ዋ​ልና፥ የም​ቤ​ዥ​በ​ትም ዐመት ደር​ሶ​አ​ልና።


በዳ​ር​ቻህ ሁሉ ስላለ ኀጢ​አ​ትህ ሁሉ ፋንታ ባለ​ጠ​ግ​ነ​ት​ህ​ንና መዝ​ገ​ብ​ህን ለመ​በ​ዝ​በዝ በከ​ንቱ እሰ​ጣ​ለሁ።


በየ​መ​ን​ገዱ ራስ የም​ን​ዝ​ር​ና​ሽን ስፍራ ሠር​ተ​ሻል፤ በየ​አ​ደ​ባ​ባ​ዩም ከፍ ያለ​ውን ቦታ​ሽን አድ​ር​ገ​ሻል። ዋጋ​ዋን እን​ደ​ም​ት​ሰ​በ​ስብ እንደ ጋለ​ሞ​ታም አል​ሆ​ን​ሽም።


የም​ድረ በዳ ዛፍም ፍሬ​ውን ይሰ​ጣል፤ ምድ​ርም ቡቃ​ያ​ዋን ትሰ​ጣ​ለች፤ በም​ድ​ራ​ቸ​ውም በሰ​ላም ታም​ነው ይኖ​ራሉ፤ የቀ​ን​በ​ራ​ቸ​ው​ንም ማነቆ በሰ​በ​ርሁ ጊዜ፥ ከሚ​ገ​ዙ​አ​ቸ​ውም እጅ ባዳ​ን​ኋ​ቸው ጊዜ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ያው​ቃሉ።


በዚህ ዘመን ሁሉ ግን ባይ​ቤዥ በኢ​ዮ​ቤ​ልዩ ዓመት እርሱ ከል​ጆቹ ጋር ይውጣ።


ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ ኑሮአችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥ ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos