ለስሙ የሚገባ ክብርን ለእግዚአብሔር አምጡ፤ ቍርባንን ይዛችሁ በአደባባዩ ግቡ፤ በቅድስናውም ስፍራ ለእግዚአብሔር ስገዱ።
ኢሳይያስ 52:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጽዮን ሆይ፥ ተነሺ፥ ተነሺ፤ ጽዮን ሆይ፥ ኀይልሽን ልበሺ፤ አንቺም ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ያልተገረዘና ርኩስ ከእንግዲህ ወዲህ ወደ አንቺ አያልፍምና ክብርሽን ልበሺ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጽዮን ሆይ፤ ተነሺ፤ ተነሺ፤ ኀይልን ልበሺ፤ ቅድስቲቱ ከተማ፤ ኢየሩሳሌም ሆይ! የክብር ልብስሽን ልበሺ፤ ያልተገረዘ የረከሰም ከእንግዲህ ወደ አንቺ አይገባም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጽዮን ሆይ፥ ተነሺ፥ ተነሺ፥ ኃይልሽን ልበሺ፤ ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ያልተገረዘና ርኩስ ከእንግዲህ ወዲህ አይገባብሽምና ጌጠኛ ልብስሽን ልበሺ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጽዮን ሆይ! ተነሺ፤ ንቂ! ኀይልሽን እንደ ልብስ ልበሺ! ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ! የተዋበ ልብስሽን ልበሺ፤ ከእንግዲህ ወዲህ ያልተገረዙና በሥርዓት ያልነጹ ሰዎች ወደ ቅጥርሽ ውስጥ አይገቡም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጽዮን ሆይ፥ ተነሺ፥ ተነሺ፥ ኃይልሽን ልበሺ፥ ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ያልተገረዘና ርኩስ ከእንግዲህ ወዲህ አይገባብሽምና ጌጠኛ ልብስሽን ልበሺ። |
ለስሙ የሚገባ ክብርን ለእግዚአብሔር አምጡ፤ ቍርባንን ይዛችሁ በአደባባዩ ግቡ፤ በቅድስናውም ስፍራ ለእግዚአብሔር ስገዱ።
የሕዝቡም አለቆች በኢየሩሳሌም ተቀመጡ፤ ከቀሩትም ሕዝብ ከዐሥሩ ክፍል አንዱ በቅድስቲቱ ከተማ በኢየሩሳሌም፥ ዘጠኙም በሌሎች ከተሞች ይቀመጡ ዘንድ ዕጣ ተጣጣሉ።
ፍርድ መልቶባት የነበረ የታመነችይቱ የጽዮን ከተማ እንዴት ጋለሞታ ሆነች! ጽድቅ አድሮባት ነበር፤ አሁን ግን ወንበዴዎችና ነፍሰ ገዳዮች አሉባት።
ፈራጆችሽንም እንደ ቀድሞ፥ አማካሪዎችሽንም እንደ መጀመሪያ ጊዜ አስነሣለሁ፤ ከዚያም በኋላ የጽድቅ ከተማ፥ የታመነችም ጽዮን ርእሰ ከተማ ተብለሽ ትጠሪያለሽ።
በዚያም ንጹሕ መንገድ ይሆናል፤ እርሱም የተቀደሰ መንገድ ይባላል፤ በዚያም ንጹሓን ያልሆኑ አያልፉበትም፤ ርኩስ መንገድም በዚያ አይኖርም፤ የተበተኑትም በእርሱ ይሄዳሉ፤ አይሳሳቱምም።
በቅድስት ከተማ ስም የተጠራችሁ፥ ስሙም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በሚባል በእስራኤል አምላክ የምትደገፉ፥ ይህን ስሙ።
ዐይንሽን አንሥተሽ በዙሪያሽ ተመልከቺ፤ እነዚህ ሁሉ ተሰብስበው ወደ አንቺ ይመጣሉ። እኔ ሕያው ነኝና እነዚህን ሁሉ እንደ ጌጥ ትለብሻቸዋለሽ፤ እንደ ሙሽራም ትጐናጸፊአቸዋለሽ ይላል እግዚአብሔር።
ከእግዚአብሔር እጅ የቍጣውን ጽዋ የጠጣሽ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ተነሺ፤ ተነሺ፤ ቁሚ፤ የሚያንገደግድሽን የቍጣውን ጽዋ ጠጥተሻልና፥ ጨልጠሽውማልና።
በእግዚአብሔርም እጅግ ደስ ይላቸዋል። ነፍሴም በእግዚአብሔር ሐሤት ታደርጋለች። ሽልማትን እንደ ለበሰ ሙሽራ፥ በጌጥ ሽልማቷም እንዳጌጠች ሙሽራ፥ የማዳንን ልብስ አልብሶኛልና፥ የደስታንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛልና።
እግዚአብሔር ለክብሩ የተከላቸው የጽድቅ ዛፎች እንዲባሉ ለጽዮን አልቃሾች አደርግላቸው ዘንድ፥ በአመድም ፋንታ አክሊልን፥ በልቅሶም ፋንታ የደስታን ዘይት፥ በኀዘንም መንፈስ ፋንታ የምስጋናን መጐናጸፊያ እሰጣቸው ዘንድ ልኮኛል።
የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ምርኮአቸውን በመለስሁ ጊዜ በይሁዳ ሀገር በከተሞችዋ፦ የጽድቅ ማደሪያ ሆይ! የቅድስና ተራራ ሆይ! እግዚአብሔር ይባርክህ የሚል ነገርን እንደ ገና ይናገራሉ።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በእስራኤል ልጆች መካከል ከአሉት ሁሉ በልቡና በሥጋው ያልተገረዘ የባዕድ ልጅ እንግዳ ሁሉ ወደ መቅደሴ አይግባ።
“እኔም በተቀደሰ ተራራዬ በጽዮን የምቀመጥ አምላካችሁ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ፤ ያን ጊዜም ኢየሩሳሌም የተቀደሰች ከተማ ትሆናለች፥ እንግዶችም ከእንግዲህ ወዲህ አያልፉባትም።
እነሆ፥ የምስራችን የሚያመጣ ሰላምንም የሚያወራ ሰው እግር በተራሮች ላይ ነው! ይሁዳ ሆይ፥ አጥፊው ፈጽሞ ጠፍቶአልና፥ ከእንግዲህም ወዲህ በአንተ ዘንድ አያልፍምና ዓመት በዓሎችህን አድርግ፥ ስእለቶችህን ክፈል።
አሁን ግን፥ ዘሩባቤል ሆይ፥ በርታ፥ ይላል እግዚአብሔር፣ ታላቁም ካህን የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢያሱ ሆይ፥ በርታ፥ እናንተም የአገሩ ሕዝብ ሆይ፥ በርቱና ሥሩ፥ ይላል እግዚአብሔር፣ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
እርሱም መልሶ በፊቱ የቆሙትን፦ እድፋሙን ልብስ ከእርሱ ላይ አውልቁ አላቸው። እርሱንም፦ እነሆ፥ አበሳህን ከአንተ አርቄአለሁ፥ ጥሩ ልብስም አለብስሃለሁ አለው።
አባቱም አገልጋዮቹን እንዲህ አላቸው፦ ‘ያማሩ ልብሶችን ቶሎ አምጡና አልብሱት፤ ለጣቱም ቀለበት፥ ለእግሩም ጫማ አድርጉለት፤’