ኢሳይያስ 51:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለወገኑ የሚፈርድ አምላክሽ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ የሚያንገደግድሽን ጽዋ የቍጣዬንም ጽዋ ከእጅሽ ወስጃለሁ፤ ደግመሽም ከእንግዲህ ወዲህ አትጠጪውም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሕዝቡን የሚታደግ አምላክሽ፣ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ ከእጅሽ፣ ያንገደገደሽን ጽዋ ወስጃለሁ፤ ያን ጽዋ፣ የቍጣዬን ዋንጫ፣ ዳግም አትጠጪውም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ ወገኑ የሚምዋገት አምላክሽ ጌታሽ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የሚያንገደግድን ጽዋ የቁጣዬንም ዋንጫ ከእጅሽ ወስጃለሁ፤ ደግመሽም ከእንግዲህ ወዲህ አትጠጪውም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሕዝቡን አቤቱታ የሚመለከተው አምላካችሁ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እንደ ሰከረ ሰው የሚያንገዳግደውን የመከራ ጽዋ ከእጃችሁ ወስጄአለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያ ኀይለኛ ቊጣዬን ከትልቁ ዋንጫ አትጠጡም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ወገኑ የሚምዋገት አምላክሽ ጌታሽ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ የሚያንገደግድን ጽዋ የቍጣዬንም ዋንጫ ከእጅሽ ወስጃለሁ፥ ደግመሽም ከእንግዲህ ወዲህ አትጠጪውም። |
ሕዝቤ ሆይ፥ ገዥዎቻችሁ ያስጨንቁአችኋል፤ አስጨናቂዎች ሴቶችም በላያችሁ ይሠለጥኑባችኋል። ሕዝቤ ሆይ፥ የሚያመሰግኑአችሁ ያስቱአችኋል፤ የምትሄዱበትንም መንገድ ያጠፋሉ።
እግዚአብሔር ግን እንዲህ ይላል፥ “በኀያላን የተማረኩ ይወሰዳሉ፤ የጨካኞችም ብዝበዛ ያመልጣል፤ እኔም ፍርድሽን እፈርድልሻለሁ፤ ልጆችሽንም አድናለሁ።
ከእግዚአብሔር እጅ የቍጣውን ጽዋ የጠጣሽ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ተነሺ፤ ተነሺ፤ ቁሚ፤ የሚያንገደግድሽን የቍጣውን ጽዋ ጠጥተሻልና፥ ጨልጠሽውማልና።
እግዚአብሔር፥ “ከእንግዲህ ወዲህ በእርግጥ ለጠላቶችሽ መብል ይሆን ዘንድ እህልሽን አልሰጥም፥ መጻተኞችም የደከምሽበትን ወይንሽን አይጠጡም፤” ብሎ በጌትነቱና በክንዱ ኀይል ምሎአል።
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይለኛል፥ “ያልተበረዘ የዚህን ቍጣ የወይን ጠጅ ጽዋ ከእጄ ውሰድ፤ አንተን የምሰድድባቸውን አሕዛብን ሁሉ አጠጣቸው።
የሚቤዢአቸው ብርቱ ነው፤ ስሙም ሁሉን የሚገዛ እግዚአብሔር ነው፤ ምድርን ያሳርፍ ዘንድ፥ በባቢሎንም የሚኖሩትን ያውክ ዘንድ ጠላቶቹን ወቀሳ ይወቅሳቸዋል።
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እነሆ የሚገፋሽን እፈርድበታለሁ፤ በቀልሽንም እበቀልልሻለሁ፤ ባሕርዋንም ድርቅ አደርገዋለሁ፤ ምንጭዋንም አደርቃለሁ።
ፊቴንም ከእነርሱ ከእንግዲህ ወዲህ አልመልስም፤ መዓቴን በእስራኤል ቤት ላይ አፍስሻለሁና፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
አሕዛብን ሁሉ እሰበስባቸዋለሁ፤ ወደ ኢዮሳፍጥም ሸለቆ አወርዳቸዋለሁ፤ በአሕዛብም መካከል በተበተኑበትና ምድሬን በተካፈሉበት በዚያ ስለ ወገኖች ስለ ርስቴ ስለ እስራኤል እወቅሳቸዋለሁ።
በቅዱሱ ተራራዬ ላይ እንደ ጠጣህ እንዲሁ አሕዛብ ሁሉ ወይንን ይጠጣሉ፤ አዎን፥ ይጠጣሉ፥ ይጨልጡማል፤ እንዳልነበሩም ይሆናሉ።
በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት ሠርቻለሁና እስኪምዋገትልኝ ድረስ፥ ፍርድን ለእኔ እስኪያደርግ ድረስ ቍጣውን እታገሣለሁ። ወደ ብርሃን ያወጣኛል፥ ጽድቅንም አያለሁ።
እነሆ፥ ኢየሩሳሌምን በዙሪያዋ ላሉት ለአሕዛብ ሁሉ የመንገድገድ ዋንጫ አደርጋታለሁ፣ ደግሞም ኢየሩሳሌም ስትከበብ በይሁዳ ላይ እንዲሁ ይሆናል።
ኢየሱስ ግን መልሶ “የምትለምኑትን አታውቁም። እኔ ልጠጣው ያለውን ጽዋ ልትጠጡ እኔም የምጠመቀውን ጥምቀት ልትጠመቁ ትችላላችሁን?” አለ። “እንችላለን” አሉት።
ዳዊትም ናባል እንደ ሞተ በሰማ ጊዜ፥ “ከናባል እጅ የስድቤን ፍርድ የፈረደልኝ፥ ባሪያውንም ከክፉዎች እጅ የጠበቀ እግዚአብሔር ይመስገን፤ እግዚአብሔርም የናባልን ክፋት በራሱ ላይ መለሰ” አለ። ዳዊትም ያገባት ዘንድ አቤግያን እንዲያነጋግሩለት ላከ።