ኢሳይያስ 49:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንቺም በልብሽ፦ የወላድ መካን ሆኛለሁና፥ እኔም መበለት ነኝና እነዚህን ማን ወለደልኝ? እነዚህንስ ማን አሳደጋቸው? እነሆ፥ ብቻዬን ቀርቼ ነበር፤ እነዚህስ ከወዴት መጡ?” ትያለሽ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በልብሽም እንዲህ ትያለሽ፣ ‘እነዚህን የወለደልኝ ማን ነው? እኔ ሐዘንተኛና መካን፣ የተሰደድሁና የተጠላሁ ነበርሁ፤ እነዚህን ማን አሳደጋቸው? ብቻዬን ቀርቼ ነበር፤ ታዲያ፣ እነዚህ ከየት መጡ?’ ” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንቺም በልብሽ፦ “የወላድ መካን ሆኛለሁና፥ እኔም ብቻዬን ተሰድጄአለሁ፥ ተቅበዝብዤአለሁ፥ እነዚህን ማን ወለደልኝ? እነዚህንስ ማን አሳደጋቸው? እነሆ፥ ብቻዬን ቀርቼ ነበር፤ እነዚህስ ወዴት ነበሩ?” ትያለሽ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ አንቺም በልብሽ እንዲህ ትያለሽ፦ ‘እነዚህን ልጆች ማን ወለደልኝ? ብዙ ልጆቼን አጥቼና የወላድ መኻን ሆኜ ነበር፤ ተሰድጄ፥ ተቀባይነትም አጥቼ ነበር፤ ታዲያ እነዚህን ልጆች ያሳደጋቸው ማነው? እኔ ብቻዬን ቀርቼ ነበር፤ እንግዲህ እነዚህ ልጆች ከወዴት መጡ?’ ” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንቺም በልብሽ፦ የወላድ መካን ሆኛለሁና፥ እኔም ብቻዬን ተሰድጄአለሁና ተቅበዝብዤአለሁምና እነዚህን ማን ወለደልኝ? እነዚህንስ ማን አሳደጋቸው? እነሆ፥ ብቻዬን ቀርቼ ነበር፥ እነዚህስ ወዴት ነበሩ? ትያለሽ። |
በዚያም የተሰማራው መንጋ እንደ ተተወ መንጋ ይሆናል፤ ምድሩም ለብዙ ዘመን መሰማሪያ ይሆናል፤ በዚያም መንጋው ይሰማራል፤ ያርፋልም።
ነገር ግን ልጆቻቸው የእጄን ሥራ ባዩ ጊዜ ስለ እኔ ስሜን ይቀድሳሉ፤ የያዕቆብንም ቅዱስ ይቀድሳሉ፤ የእስራኤልንም አምላክ ይፈራሉ።
ከእንግዲህ ወዲህ፥ “የተተወች” አትባዪም፤ ምድርሽም ከእንግዲህ ወዲህ፥ “ውድማ” አትባልም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በአንቺ ደስ ብሎታልና፥ ምድርሽም ባል ታገባለችና አንቺ፥ “ደስታዬ የሚኖርባት” ትባያለሽ፤ ምድርሽም፥ “ባል ያገባች” ትባላለች።
በሰይፍ ስለት ይወድቃሉ፤ በአሕዛብም ሁሉ ይማረካሉ፤ የአሕዛብ ጊዜያቸው እስኪፈጸም ድረስ አሕዛብ ኢየሩሳሌምን ይረግጡአታል።
አንተ የዱር ወይራ፥ አንተን ስንኳ ከበቀልህበት ቈርጦ ባልበቀልህበት በመልካሙ ዘይት ስፍራ ከተከለህ፥ ይልቁን ጥንቱን ዘይት የነበሩትን እነዚያን በበቀሉበት ስፍራ እንዴት አብልጦ ሊተክላቸው አይችልም?