ኢሳይያስ 49:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)21 አንቺም በልብሽ፦ “የወላድ መካን ሆኛለሁና፥ እኔም ብቻዬን ተሰድጄአለሁ፥ ተቅበዝብዤአለሁ፥ እነዚህን ማን ወለደልኝ? እነዚህንስ ማን አሳደጋቸው? እነሆ፥ ብቻዬን ቀርቼ ነበር፤ እነዚህስ ወዴት ነበሩ?” ትያለሽ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም21 በልብሽም እንዲህ ትያለሽ፣ ‘እነዚህን የወለደልኝ ማን ነው? እኔ ሐዘንተኛና መካን፣ የተሰደድሁና የተጠላሁ ነበርሁ፤ እነዚህን ማን አሳደጋቸው? ብቻዬን ቀርቼ ነበር፤ ታዲያ፣ እነዚህ ከየት መጡ?’ ” Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም21 ከዚህ በኋላ አንቺም በልብሽ እንዲህ ትያለሽ፦ ‘እነዚህን ልጆች ማን ወለደልኝ? ብዙ ልጆቼን አጥቼና የወላድ መኻን ሆኜ ነበር፤ ተሰድጄ፥ ተቀባይነትም አጥቼ ነበር፤ ታዲያ እነዚህን ልጆች ያሳደጋቸው ማነው? እኔ ብቻዬን ቀርቼ ነበር፤ እንግዲህ እነዚህ ልጆች ከወዴት መጡ?’ ” Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)21 አንቺም በልብሽ፦ የወላድ መካን ሆኛለሁና፥ እኔም መበለት ነኝና እነዚህን ማን ወለደልኝ? እነዚህንስ ማን አሳደጋቸው? እነሆ፥ ብቻዬን ቀርቼ ነበር፤ እነዚህስ ከወዴት መጡ?” ትያለሽ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)21 አንቺም በልብሽ፦ የወላድ መካን ሆኛለሁና፥ እኔም ብቻዬን ተሰድጄአለሁና ተቅበዝብዤአለሁምና እነዚህን ማን ወለደልኝ? እነዚህንስ ማን አሳደጋቸው? እነሆ፥ ብቻዬን ቀርቼ ነበር፥ እነዚህስ ወዴት ነበሩ? ትያለሽ። Ver Capítulo |