ኢሳይያስ 43:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆ፥ አዲስ ነገርን አደርጋለሁ፤ እርሱም አሁን ይበቅላል፤ እናንተም አታውቁትም፤ በምድረ በዳም መንገድን፥ በበረሃም ወንዞችን አደርጋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆ፤ አዲስ ነገር አደርጋለሁ! እርሱም አሁን ይበቅላል፤ አታስተውሉትምን? በምድረ በዳም መንገድ አዘጋጃለሁ፤ በበረሓም ምንጭ አፈልቃለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ፥ አዲስ ነገርን አደርጋለሁ፤ እርሱም አሁን ይበቅላል፥ ይህን እናንተም አታውቁም? በምድረ በዳም መንገድን በበረሃም ወንዞችን እዘረጋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይልቅስ የማደርገውን አዲስ ነገር ተመልከቱ፤ እርሱም በመፈጸም ላይ ስለ ሆነ ልታዩት ትችላላችሁ፤ በበረሓ መንገድን አወጣለሁ፤ በምድረ በዳም ወንዞችን አፈልቃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆ፥ አዲስ ነገርን አደርጋለሁ፥ እርሱም አሁን ይበቅላል፥ እናንተም አታውቁትምን? በምድረ በዳም መንገድን በበረሃም ወንዞችን አደርጋለሁ። |
እነሆ፥ እኔ በዚያ በኮሬብ በዓለት ላይ በፊትህ እቆማለሁ፤ ዓለቱንም ትመታለህ፤ ሕዝቡም ይጠጣ ዘንድ ከእርሱ ውኃ ይወጣል” አለው። ሙሴም በእስራኤል ልጆች ፊት እንዲሁ አደረገ።
በታላቅም እልቂት ቀን ግንቦች በወደቁ ጊዜ፥ በረዥሙ ተራራ ሁሉ ከፍ ባለውም ኮረብታ ሁሉ ላይ፥ ወንዞችና የውኃ ፈሳሾች ይሆናሉ።
ሰውም ቃሉን ይሰውራል፤ በውኃ እንደሚጠልቅም ይሰወራል፤ ክብሩም በደረቅ ምድር እንደሚፈስስ ውኃ በጽዮን ይገለጣል።
የእግዚአብሔር ስም ለእናንተ ታላቅ ነው፤ ሀገራችሁም የሰፉ ወንዞችና ታላቅ የመስኖ ስፍራ ይሆናል፤ በዚህች መንገድ አትሄድም፤ መርከቦችም አይሄዱም።
በተራሮች ላይ ወንዞችን፥ በሸለቆችም መካከል ምንጮችን እከፍታለሁ፤ ምድረ በዳውን ለውኃ መቆሚያ፥ የተጠማችውንም ምድር ለውኃ መፍለቂያ አደርጋለሁ።
እነሆ የቀድሞው ነገር ተፈጸመ፤ አዲስ ነገርንም እናገራለሁ፤ አስቀድሞም ሳይነገር እርሱን አስታውቃችኋለሁ።”
ስለዚህ፥ አንተ፥ “ጣዖቴ ይህን አድርጎአል፤ የተቀረጸው ምስሌና ቀልጦ የተሠራው ምስሌም ይህን አዘዙኝ” እንዳትል፥ የሚሆነውን ከመሆኑ በፊት ነገርሁህ፤ አስረዳሁህም፤
የሚራራላቸውም ያጽናናቸዋልና፥ በውኃ ምንጮችም በኩል ይመራቸዋልና አይራቡም፤ አይጠሙም፤ የፀሐይ ትኩሳትም አይጐዳቸውም።
ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ደስ አሰኝሻለሁ፤ ባድማሽንም ሁሉ ደስ አሰኛለሁ፤ ምድረ በዳሽንም እንደ ዔድን፥ በረሃዎችሽንም እንደ እግዚአብሔር ገነት አደርጋለሁ። ደስታና ተድላ እምነትና የዝማሬ ድምፅ በውስጧ ይገኝባታል።
ስለዚህ እነሆ፥ “የእስራኤልን ሕዝብ ከግብፅ ምድር ያወጣ ሕያው እግዚአብሔርን! ዳግመኛ የማይባልበት ዘመን ይመጣል፥” ይላል እግዚአብሔር፤
አንቺ ከዳተኛ ልጅ ሆይ! እስከ መቼ ትቅበዘበዣለሽ? እግዚአብሔር በምድር ላይ አዲስ ነገር ፈጥሮአልና ሰው ወደ ድኅነት ይመጣል።”
እያለቀሱ ሄዱ፤ እኔም በማጽናናት አመጣቸዋለሁ፤ በወንዝ ዳር በቅን መንገድ አስሄዳቸዋለሁ፤ በእርሱም አይሰናከሉም፤ እኔ ለእስራኤል አባት ነኝና፥ ኤፍሬምም በኵሬ ነውና።”
የሚናደፍ እባብና ጊንጥ፥ ጥማትም ባለባት፥ ውኃም በሌለባት፥ በታላቂቱና በምታስፈራው ምድረ በዳ የመራህን፥ ከጭንጫ ድንጋይም ጣፋጭ ውኃን ያወጣልህን፥