Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 126:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በኀ​ያል እጅ እን​ዳሉ ፍላ​ጾች፥ የተ​ጣሉ ሰዎች ልጆች እን​ዲሁ ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እግዚአብሔር ሆይ፤ በኔጌብ እንዳሉ ጅረቶች፣ ምርኳችንን መልስ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 አቤቱ፥ በደቡብ እንዳሉ ፈሳሾች ምርኮአችንን መልስ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እግዚአብሔር ሆይ! ዝናብ ለደቡብ በረሓ ወንዝ ውሃን እንደሚሰጥ የተማረከብን ሀብታችንን መልስልን።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 126:4
9 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤትን ካል​ሠራ፥ ቤትን የሚ​ሠሩ በከ​ንቱ ይደ​ክ​ማሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከተ​ማን ካል​ጠ​በቀ፥ የሚ​ጠ​ብቁ በከ​ንቱ ይተ​ጋሉ።


የባ​ሪ​ያ​ህን ነፍስ ደስ አሰ​ኛት፥ ነፍ​ሴን ወደ አንተ አነ​ሣ​ለ​ሁና።


በዚ​ያን ጊዜ አን​ካ​ሳ​ዎች እንደ ሚዳቋ ይዘ​ል​ላሉ፤ የዲ​ዳ​ዎ​ችም ምላስ ርቱዕ ይሆ​ናል፤ በም​ድረ በዳ ውኃ፥ በተ​ጠማ መሬ​ትም ፈሳሽ ይፈ​ል​ቃ​ልና።


በተ​ራ​ሮች ላይ ወን​ዞ​ችን፥ በሸ​ለ​ቆ​ችም መካ​ከል ምን​ጮ​ችን እከ​ፍ​ታ​ለሁ፤ ምድረ በዳ​ውን ለውኃ መቆ​ሚያ፥ የተ​ጠ​ማ​ች​ው​ንም ምድር ለውኃ መፍ​ለ​ቂያ አደ​ር​ጋ​ለሁ።


እነሆ፥ አዲስ ነገ​ርን አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ እር​ሱም አሁን ይበ​ቅ​ላል፤ እና​ን​ተም አታ​ው​ቁ​ትም፤ በም​ድረ በዳም መን​ገ​ድን፥ በበ​ረ​ሃም ወን​ዞ​ችን አደ​ር​ጋ​ለሁ።


እገ​ለ​ጥ​ላ​ች​ኋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ምር​ኮ​አ​ች​ሁ​ንም እመ​ል​ሳ​ለሁ፤ ከአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ዘንድ እና​ን​ተ​ንም ከበ​ተ​ን​ሁ​በት ስፍራ ሁሉ እሰ​በ​ስ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እና​ን​ተ​ንም ለም​ርኮ ወዳ​ፈ​ለ​ስ​ሁ​በት ስፍራ እመ​ል​ሳ​ች​ኋ​ለሁ።


እነሆ! የሕ​ዝ​ቤን የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንና የይ​ሁ​ዳን ምርኮ የም​መ​ል​ስ​በት ዘመን ይመ​ጣ​ልና፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ወደ ሰጠ​ኋት ምድር እመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ይገ​ዙ​አ​ታል።”


የይ​ሁዳ ልጆ​ችና የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በአ​ን​ድ​ነት ይሰ​በ​ሰ​ባሉ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም አንድ አለቃ ይሾ​ማሉ፤ ከም​ድ​ሪ​ቱም ይወ​ጣሉ፤ የኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል ቀን ታላቅ ይሆ​ና​ልና።


ከላይ የሚ​ወ​ር​ደው ውኃ ቆመ፤ እስከ ቀር​ያ​ት​ያ​ርም አው​ራጃ እጅግ ርቆ እንደ ግድ​ግዳ ቆመ፤ ወደ ዓረባ ባሕር ወደ ጨው ባሕር የሚ​ወ​ር​ደው ውኃም ፈጽሞ ደረቀ፤ ሕዝ​ቡም በኢ​ያ​ሪኮ ፊት ለፊት ቆሙ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos