እናንተ በእኔ ላይ ክፉ መከራችሁ፤ እግዚአብሔር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እንዲመገብ ለማድረግ ለእኔ መልካም መከረ።
ኢሳይያስ 37:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “እኔ ጥንት የሠራሁትን አልሰማህምን? እኔ በቀድሞ ዘመን እንዳደረግሁት፥ አሁንም አሕዛብን በምሽጎቻቸው፥ በጽኑ ከተሞቻቸው የሚኖሩትንም ያጠፉ ዘንድ አዘዝሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ይህን ቀድሞ እንደ ወሰንሁት፣ አልሰማህምን? ጥንትም እንዳቀድሁት አሁን ግን እንዲፈጸም አደረግሁት፤ ይህም የተመሸጉትን ከተሞች አንተ የድንጋይ ክምር ማድረግህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህን እኔ ጥንቱን እንደ ሠራሁት፥ ቀድሞውንም እንዳደረግሁት አልሰማህምን? እሁንም የተመሸጉትን ከተሞች የፍርስራሽ ክምር እስኪሆኑ ድረስ እንድታፈርስ አደረግኩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ከብዙ ጊዜ በፊት ይህን ሁሉ የወሰንኩት እኔ ራሴ መሆኔን አልሰማህምን? ዕቅዱን አውጥቼ አሁን ለፍጻሜ ያደረስኩት እኔ ነኝ፤ የተመሸጉ ከተሞችን የፍርስራሽ ክምር እንድታደርጋቸው ኀይልን የሰጠሁህ እኔ ነኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ጥንቱን እንደ ሠራሁት፥ ቀድሞውንም እንዳደረግሁት አልሰማህምን? እሁንም የተመሸጉትን ከተሞች የፍርስራሽ ክምር እስኪሆኑ ድረስ እንድታፈርስ አደረግሁህ። |
እናንተ በእኔ ላይ ክፉ መከራችሁ፤ እግዚአብሔር ግን ዛሬ እንደ ሆነው ብዙ ሕዝብ እንዲመገብ ለማድረግ ለእኔ መልካም መከረ።
“በውኑ መጥረቢያ በሚቈርጥበት ሰው ላይ ይነሣልን? ወይስ መጋዝ በሚስበው ሰው ላይ ይጓደዳልን? ይህም ዘንግ በሚመቱበት ላይ እንደ መነሣት፥ በትርም ዕንጨት አይደለሁም እንደ ማለት ነው።”
በአሮጌው ኵሬ ላለው ውኃ በሁለቱ ቅጥር መካከል መከማቻ ሠራችሁ፤ ይህን ያደረገውን ግን አልተመለከታችሁም፤ ቀድሞ የሠራውንም አላያችሁም።
አላወቃችሁምን? ወይስ አልሰማችሁምን? ከጥንትስ አልተወራላችሁምን? ወይስ ምድር ከተመሠረተች ጀምሮ አላስተዋላችሁምን?
አሁንም አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘለዓለም አምላክ፥ የምድርንም ዳርቻ የፈጠረ አምላክ ነው፤ አይራብም፤ አይጠማም፤ አይደክምም፤ ማስተዋሉም አይመረመርም።
ብርሃንን ፈጠርሁ፤ ጨለማውንም ፈጠርሁ፤ ሰላምንም አደርጋለሁ፤ ክፋትንም አመጣለሁ፤ እነዚህን ሁሉ ያደረግሁ እግዚአብሔር እኔ ነኝ።
ወይስ በከተማ ውስጥ መለከት ሲነፋ ሕዝቡ አይደነግጡምን? ወይስ እግዚአብሔር ያላዘዘው ክፉ ነገር በከተማ ላይ ይመጣልን?
እርሱንም በተወሰነው በእግዚአብሔር ምክርና በቀደመው ዕውቀቱ እናንተ አሳልፋችሁ በኃጥኣን እጅ ሰጣችሁት፤ ሰቅላችሁም ገደላችሁት።
ከብዙ ጊዜ በፊት ለዚህ ፍርድ የተጻፉ አንዳንዶች ሰዎች ሾልከው ገብተዋልና፤ ኀጢአተኞች ሆነው የአምላካችንን ጸጋ በሴሰኝነት ይለውጣሉ፤ ብቻውን ንጉሣችንንና ጌታችንንም የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ይክዳሉ።