La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢሳይያስ 33:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እርሱ ከፍ ባለ በጽ​ኑዕ ዓለት ዋሻ ይኖ​ራል፤ እን​ጀ​ራም ይሰ​ጠ​ዋል፤ ውኃ​ውም የታ​መ​ነች ትሆ​ና​ለች።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ይህ ሰው በከፍታ ላይ ይኖራል፤ የተራራም ምሽግ መጠጊያው ይሆናል፤ እንጀራ ይሰጠዋል፣ ውሃውም አይቋረጥበትም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እርሱ ከፍ ባለ ሥፍራ ይቀመጣል፤ ጠንካራ አምባ መጠጊያው ይሆናል፤ እንጀራም ይሰጠዋል፥ ውኃውም የማታቋርጥ ትሆናለች።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በከፍተኛ ቦታ ላይ ይኖራሉ። ከለላቸውም እንደ ቋጥኝ ምሽግ ይሆናል ምግባቸውንም በጊዜው ያገኛሉ፤ የሚጠጡትንም ውሃ አያጡም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እርሱ ከፍ ባለ ሥፍራ ይቀመጣል፥ ጠንካራ አምባ መጠጊያው ይሆናል፥ እንጀራም ይሰጠዋል፥ ውኃውም የታመነች ትሆናለች።

Ver Capítulo



ኢሳይያስ 33:16
27 Referencias Cruzadas  

ከዚህ በኋላ ኤል​ያስ ተነ​ሥቶ፥ እነሆ፥ በራሱ አጠ​ገብ የተ​ጋ​ገረ እን​ጎ​ቻና በማ​ሰሮ ውኃ አገኘ። በላም፤ ጠጣም፤ ተመ​ል​ሶም ተኛ።


ርኅ​ሩኅ፥ ይቅር ባይና ቸር ሰው ነገ​ሩን በፍ​ርድ ይፈ​ጽ​ማል።


አቤቱ፥ በአ​ንተ ታም​ኛ​ለ​ሁና ጠብ​ቀኝ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በል​ባ​ቸው የዋ​ሃን ለሆኑ ቅርብ ነው፥ በመ​ን​ፈስ ትሑ​ታን የሆ​ኑ​ት​ንም ያድ​ና​ቸ​ዋል።


አጥ​ን​ቶች ሁሉ እን​ዲህ ይሉ​ሃል፦ “አቤቱ፥ እንደ አንተ ማን ነው? ድሃ​ውን ከሚ​ቀ​ማው እጅ ድሃ​ው​ንና ችግ​ረ​ኛ​ው​ንም ከሚ​ነ​ጥ​ቀው እጅ ታድ​ነ​ዋ​ለህ።”


ከቍ​ጣህ ፊት የተ​ነሣ ለሥ​ጋዬ ድኅ​ነት የለ​ውም፤ ከኀ​ጢ​አ​ቴም ፊት የተ​ነሣ ለአ​ጥ​ን​ቶቼ ሰላም የላ​ቸ​ውም።


ረዳቴ ሆነ​ኽ​ል​ኛ​ልና፥ በክ​ን​ፎ​ች​ህም ጥላ እታ​መ​ና​ለሁ።


በል​ዑል ረድ​ኤት የሚ​ያ​ድር፥ በሰ​ማይ አም​ላክ ጥላ ውስጥ የሚ​ቀ​መጥ፥


ያን​ጊዜ በመ​ል​ካም ሽም​ግ​ልና ይበ​ዛሉ፤ ዕረ​ፍት ያላ​ቸ​ውም ሆነው ይኖ​ራሉ።


የሚሰማኝ ግን በተስፋ ይኖራል፥ ከክፉም ሁሉ ያለ ድንጋጤ ያርፋል።”


በየውሃት የሚሄድ ተማምኖ ይኖራል፤ መንገዱን የሚያጣምም ግን ይታወቃል።


የእግዚአብሔር ስም ታላቅ ኀይል ነው፤ ጻድቃንም እርሱን በመከተል ከፍ ከፍ ይላሉ።


ለተ​ዋ​ረዱ ሰዎች ከተ​ሞች ረዳት ሆነ​ሃ​ልና፥ በች​ግ​ራ​ቸው የተ​ጨ​ነ​ቁ​ትን በደ​ስታ ጋረ​ድ​ሃ​ቸው፤ ከክ​ፉ​ዎች ሰዎ​ችም አዳ​ን​ሃ​ቸው፤ ለተ​ጠ​ሙት ጥላ ሆን​ሃ​ቸው፤ ለተ​ገ​ፉ​ትም ሕይ​ወት ሆን​ሃ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የጭ​ን​ቀ​ትን እን​ጀ​ራና የመ​ከ​ራን ውኃ ይሰ​ጥ​ሃል። የሚ​ያ​ሳ​ስ​ቱ​ህም እን​ግ​ዲህ ወደ አንተ አይ​ቀ​ር​ቡም፤ ዐይ​ኖ​ችህ ግን የሚ​ያ​ሳ​ስ​ቱ​ህን ያያሉ፤


ሕዝ​ቤም በሰ​ላም ከተማ ይኖ​ራል። ተዘ​ል​ሎም በው​ስ​ጥዋ ያድ​ራል፤ በብ​ል​ጽ​ግ​ናም ያር​ፋል።


የሚ​ራ​ራ​ላ​ቸ​ውም ያጽ​ና​ና​ቸ​ዋ​ልና፥ በውኃ ምን​ጮ​ችም በኩል ይመ​ራ​ቸ​ዋ​ልና አይ​ራ​ቡም፤ አይ​ጠ​ሙም፤ የፀ​ሐይ ትኩ​ሳ​ትም አይ​ጐ​ዳ​ቸ​ውም።


በዚ​ያን ጊዜ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትታ​መ​ና​ለህ፤ በም​ድ​ርም በረ​ከት ላይ ያወ​ጣ​ሃል፤ የአ​ባ​ትህ የያ​ዕ​ቆ​ብ​ንም ርስት ይመ​ግ​ብ​ሃል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፍ እን​ደ​ዚህ ተና​ግ​ሮ​አ​ልና።


ንጉ​ሡም ሴዴ​ቅ​ያስ አዘዘ፤ ኤር​ም​ያ​ስ​ንም በግ​ዞት ቤቱ ቅጥር ግቢ አኖ​ሩት፤ እን​ጀ​ራም ሁሉ ከከ​ተማ እስ​ኪ​ጠፋ ድረስ ዕለት ዕለት አንድ አንድ እን​ጀራ ከውጪ ጋጋ​ሪ​ዎች እያ​መጡ ይሰ​ጡት ነበር። እን​ዲ​ሁም ኤር​ም​ያስ በግ​ዞት ቤት ቅጥር ግቢ ተቀ​ምጦ ነበር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጽ​ዮን ሆኖ ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ ይጮ​ኻል፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሆኖ ቃሉን ይሰ​ጣል፤ ሰማ​ይና ምድ​ርም ይና​ወ​ጣሉ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ለሕ​ዝቡ ይራ​ራል፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ያጸ​ናል።


ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌ ነው፣ እግሮቼን እንደ ዋላ እግሮች ያደርጋል፣ በከፍታዎችም ላይ ያስሄደኛል።


የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን፤


እስ​ራ​ኤል ሆይ ብፁዕ ነህ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዳነ ሕዝብ እንደ አንተ ማን​ነው? እርሱ ያጸ​ን​ሃል፤ ይረ​ዳ​ሃ​ልም፤ ትም​ክ​ሕ​ትህ በሰ​ይ​ፍህ ነው፤ ጠላ​ቶ​ችህ ውሸ​ታ​ሞች ናቸው፤ አን​ተም በአ​ን​ገ​ታ​ቸው ላይ ትጫ​ና​ለህ።”