ኢሳይያስ 30:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የግብፅ ርዳታ ከንቱና ባዶ ነው፤ ስለዚህ፥ “ምክራችሁ ከንቱ ነው” ብለህ ንገራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ርዳታዋም ፈጽሞ ዋጋ ቢስ ወደ ሆነው ወደ ግብጽ ይሄዳሉ። ስለዚህ ስሟን፣ ረዓብ፣ ምንም የማትጠቅም ብዬ እጠራታለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የግብጽ እርዳታ ከንቱና ምንም ነው፤ ስለዚህ ስሙን፦ “በቤት የሚቀመጥ ረዓብ” ብዬ ጠርቼዋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከግብጽ የሚጠበቀው ርዳታ ከንቱ ነው፤ ስለዚህ ለግብጽ ‘መርዝ የሌለው እባብ’ የሚል የፌዝ ስም አውጥቼላታለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የግብጽ እርዳታ ከንቱና ምና ምን ነው፥ ስለዚህ ስሙን፦ በቤት የሚቀመጥ ረዓብ ብዬ ጠርቼዋለሁ። |
የዘመኖቻችንም ዕድሜ ሰባ ዓመት ነው፥ ቢበዛም ሰማንያ ዓመት ነው፤ ከእነዚህ ቢበዛ ግን ድካምና መከራ ነው፤ የዋህነት ከእኛ አልፋለችና፥ እኛም ተገሥጸናልና።
ሙሴም ለሕዝቡ፥ “አትፍሩ፤ ዛሬ የምታዩአቸውን ግብፃውያንን ለዘለዓለም አታዩአቸውምና ቁሙ፤ ዛሬ ለእናንተ የሚያደርጋትን የእግዚአብሔርን ማዳን እዩ።
በዚያም ቀን በዚች ደሴት የሚቀመጡ፦ እነሆ፥ ለርዳታ ወደ እነርሱ የሸሸንበት ተስፋችን ይህ ነበረ፤ ከአሦር ንጉሥ ራሳቸውን ያላዳኑ እኛን እንዴት ያድኑናል?” ይላሉ።
የእስራኤል ቅዱስ፥ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፥ “ብትጸጸትና ብታለቅስ ትድናለህ፤ የት እንዳለህም ታውቃለህ፤ በከንቱ ታምነሃልና፤ ኀይላችሁም ከንቱ ይሆናል፤ እናንተ ግን መስማትን እንቢ አላችሁ፤
ከታናናሾቹ ከጌታዬ አገልጋዮች የሚያንሰውን የአንዱን ጭፍራ ፊት መመለስ እንዴት ትችላለህ? ስለ ሰረገሎችና ፈረሰኞች በግብፅ የሚታመኑ ለጌታዬ ባሮች ናቸው።
እንዲህም በለው፥ “ተጠበቅ፥ ዝምም በል፤ አትፍራ፤ ከእነዚህ ከሚጤሱ ሁለት የእንጨት ጠለሸቶች፥ የተነሣ ልብህ አይደንግጥ፤ ከተቈጣሁ በኋላ ይቅር እላለሁና።
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ከእኔ ትጠይቁ ዘንድ የላካችሁን የይሁዳን ንጉሥ እንዲህ በሉት፦ እነሆ ሊረዳችሁ የወጣው የፈርዖን ሠራዊት ወደ ሀገሩ ወደ ግብፅ ይመለሳል።
ኤፍሬምም ደዌውን አያት፤ ይሁዳም ሥቃዩን አያት፤ ኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ፤ ወደ ንጉሡም ወደ ኢያሪም መልእክተኛን ላከ፤ እርሱ ግን ፈጽሞ ይፈውሳችሁ ዘንድ አልቻለም፤ ከእናንተም ሕማም አልተወገደም።