ሰባት ቀንና ሰባት ሌሊትም በአጠገቡ ተቀመጡ፤ ሕማሙ እጅግ አስፈሪና ታላቅ እንደ ነበረ አይተዋልና ከእነርሱ አንድ ቃል የሚናገረው አልነበረም።
ኢሳይያስ 3:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጌጦችሽም ሣጥኖች ያለቅሳሉ፤ ይዋረዳሉም፤ ብቻሽንም ትቀሪያለሽ፤ ከምድርም ጋር ትቀላቀያለሽ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጽዮን ደጆች ያዝናሉ፣ ያለቅሳሉም፤ እርሷም ተረስታ በመሬት ላይ ትቀመጣለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጽዮን ደጆች ያዝናሉ፤ ያለቅሳሉም፤ እርሷም ተረስታ በመሬት ላይ ትቀመጣለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኢየሩሳሌም በሮች እርቃንዋን ሆና በልቅሶና በሐዘን እንደ ተቀመጠች ሴት ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሮችዋ ያዝናሉ ያለቅሱማል፥ እርስዋም ብቻዋን በምድር ላይ ትቀመጣለች። |
ሰባት ቀንና ሰባት ሌሊትም በአጠገቡ ተቀመጡ፤ ሕማሙ እጅግ አስፈሪና ታላቅ እንደ ነበረ አይተዋልና ከእነርሱ አንድ ቃል የሚናገረው አልነበረም።
እናንተ የከተሞች በሮች ሆይ፥ ወዮ በሉ፤ እናንተም ከተሞች ሆይ፥ ደንግጡ፥ ጩኹም፤ ፍልስጥኤማውያን ሆይ፥ ሁላችሁም ቀልጣችኋል፤ ጢስ ከሰሜን ይወጣልና፥ እንግዲህም አትኖሩምና።
የበለጸገች ከተማና ቤቶችዋ ምድረ በዳ ይሆናሉ። የከተማውን ሀብትና ያማሩ ቤቶችን ይተዋሉ፤ አንባዎችም ለዘለዓለም ዋሻ፥ የምድረ በዳም አህያ ደስታ፥ የመንጎችም ማሰማሪያ ይሆናሉ።
አንቺ ድንግል የባቢሎን ልጅ ሆይ፥ ውረጂ፤ በትቢያም ላይ ተቀመጪ፤ የከለዳውያን ሴት ልጅ ሆይ፥ ከዚህ በኋላ ለስላሳና ቅምጥል አትባዪምና ያለ ዙፋን በመሬት ላይ ተቀመጪ።
እኔም፥ “ጌታዬ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ ነው?” አልሁ። እርሱም መልሶ እንዲህ አለኝ፥ “ከተሞች የሚኖርባቸውን አጥተው እስኪፈርሱ ድረስ፥ ቤቶችም ሰው አልቦ እስኪሆኑ፥ ምድርም ፈጽሞ ባድማ ሆና እስክትቀር ድረስ ነው፤”
መበለቶቻቸውም ከባሕር አሸዋ ይልቅ በዝተዋል፤ በብላቴኖች እናት ላይ በቀትር ጊዜ አጥፊውን አምጥቻለሁ፤ ጭንቀትንና ድንጋጤን በድንገት አምጥቼባታለሁ።
አሌፍ። ሕዝብ ሞልቶባት የነበረች ከተማ ብቻዋን እንዴት ተቀመጠች! በአሕዛብ ተመልታ የነበረች እንደ መበለት ሆናለች፤ አሕዛብን ትገዛ የነበረች፥ አውራጃዎችንም ትገዛ የነበረች ገባር ሆናለች።
ዳሌጥ። ወደ ዓመት በዓል የሚመጣ የለምና የጽዮን መንገዶች አለቀሱ፤ በሮችዋ ሁሉ ፈርሰዋል፤ ካህናቷም ያለቅሳሉ፤ ደናግሎችዋም ተማረኩ፤ እርስዋም በምሬት አለች።
ዮድ። የጽዮን ሴት ልጅ ሽማግሌዎች ዝም ብለው በመሬት ላይ ተቀምጠዋል፤ ትቢያን በራሳቸው ላይ ነሰነሱ፤ ማቅም ታጠቁ፤ በኢየሩሳሌም መሳፍንቱንና ደናግሉን ወደ ምድር አወረዷቸው።
ሔት። እግዚአብሔር የጽዮንን ሴት ልጅ ቅጥር ያፈርስ ዘንድ ዐሰበ፤ የመለኪያውንም ገመድ ዘረጋ፤ እርስዋን ከማጥፋት እጁን አልመለሰም፤ ምሽጉና ቅጥሩ አለቀሱ፤ በአንድነትም ደከሙ።
ሰዎች የሚኖሩባቸው ከተሞች ይጠፋሉ፤ ምድሪቱም ውድማ ትሆናለች፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ በላቸው።”
የባሕርም አለቆች ሁሉ ከዙፋኖቻቸው ይወርዳሉ፤ ዘውዳቸውን ከራሳቸው ያወርዳሉ፤ ወርቀ ዘቦ ልብሳቸውን ያወልቃሉ፤ በመሬትም ላይ ተቀምጠው ይደነግጣሉ፤ ሞታቸውንም ይፈራሉ፤ ስለ አንቺም ያለቅሳሉ።
አንቺን ይጥሉሻል፤ ልጆችሽንም ከአንቺ ጋር ይጥሉአቸዋል፤ ድንጋይንም በደንጋይ ላይ አይተዉልሽም፤ የይቅርታሽን ዘመን አላወቅሽምና።”