እናንት የጽዮን ቈነጃጅት፥ እናቱ በሠርጉ ቀን በልቡ ደስታ ቀን ያቀዳጀችውን አክሊል ደፍቶ ንጉሥ ሰሎሞንን ታዩ ዘንድ ውጡ።
ኢሳይያስ 3:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ ጌታ የጽዮን ታላላቅ ሴቶች ልጆችን ያዋርዳቸዋል። እግዚአብሔርም በዚያ ቀን ልብሳቸውን ይገልጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ፣ ጌታ በጽዮን ሴቶች ዐናት ላይ ቈረቈር ያመጣል፤ እግዚአብሔርም ራሳቸውን ቡሓ ያደርጋል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ፤ ጌታ በጽዮን ሴቶች ዐናት ላይ ቆረቆር ያመጣል፤ ጌታም ራሳቸውን ቡሀ ያደርጋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ በእነርሱ ራስ ላይ የቡሃና የቈረቈር በሽታ አመጣለሁ፤ የውስጥ ገላቸውም ይጋለጣል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ጌታ የጽዮንን ቆነጃጅት አናት በቡሀነት ይመታል፥ እግዚአብሔርም ኀፍረተ ሥጋችውን ይገልጣል። |
እናንት የጽዮን ቈነጃጅት፥ እናቱ በሠርጉ ቀን በልቡ ደስታ ቀን ያቀዳጀችውን አክሊል ደፍቶ ንጉሥ ሰሎሞንን ታዩ ዘንድ ውጡ።
እንዲሁ የአሦር ንጉሥ የግብፅንና የኢትዮጵያን ምርኮ፥ ጐበዛዝቱንና ሽማግሌዎቹን ራቁታቸውንና ባዶ እግራቸውን አድርጎ፥ ገላቸውንም ገልጦ ለግብፅ ኀፍረት ይነዳቸዋል።
እግዚአብሔር እንዲህ አለ፥ “የጽዮን ቆነጃጅት ኰርተዋልና፥ አንገታቸውን እያሰገጉ በዐይናቸውም እያጣቀሱ፥ በእግራቸውም እያረገዱ፥ ልብሳቸውንም እየጐተቱ፥ በእግራቸውም እያማቱ ይሄዳሉና፤
በልብሽም፦ እንዲህ ያለ ነገር ስለ ምን ደረሰብኝ? ብትዪ፥ ከኀጢአትሽ ብዛት የተነሣ ልብስሽ በስተኋላሽ ተገፎአል፤ ተረከዝሽም ተገልጦአል።
ወይም ጎባጣ፥ ወይም ድንክ፥ ወይም ዐይነ መጭማጫ፥ ወይም ቅንድበ መላጣ፥ ወይም እከካም፥ ወይም ቋቍቻም፥ ወይም የአባለዘሩ ፍሬ አንድ የሆነ ነውረኛ ሁሉ አይቅረብ።
በሻፊር የምትቀመጪ ሆይ፥ በዕራቁትነትሽና በእፍረት እለፊ፥ በጸዓናን የምትቀመጠው አልወጣችም፥ የቤትኤጼል ልቅሶ ከእናንተ ዘንድ መኖሪያውን ይወስዳል።
እነሆ፥ በአንቺ ላይ ነኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ ልብስሽን በፊትሽ እገልጣለሁ፣ ኅፍረተ ሥጋሽንም ለአሕዛብ፥ ነውርሽንም ለመንግሥታት አሳያለሁ።