Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ራእይ 16:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ፊተኛውም ሄዶ ጽዋውን በምድር ውስጥ አፈሰሰ፤ የአውሬውም ምልክት ባለባቸው ለምስሉም በሚሰግዱ ሰዎች ክፉኛ የሚነዘንዝ ቍስል ሆነባቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 የመጀመሪያው መልአክ ሄዶ ጽዋውን በምድር ላይ አፈሰሰ፤ የአውሬውን ምልክት በተቀበሉትና ለምስሉም በሰገዱት ሰዎች ላይ ክፉኛ የሚያሠቃይ ቍስል ወጣባቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 የመጀመሪያውም መልአክ ሄዶ ጽዋውን በምድር ላይ አፈሰሰ፤ የአውሬውም ምልክት ባለባቸው ለምስሉም በሚሰግዱ ሰዎች ላይ ክፉኛ የሚነዘንዝ ቁስል ሆነባቸው።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 የመጀመሪያው መልአክ ሄደና ጽዋውን በምድር ላይ አፈሰሰ፤ የአውሬው ምልክት ባለባቸውና ለአውሬው ምስል በሚሰግዱ ሰዎች ላይ መጥፎና የሚያሠቃይ ቊስል ወጣባቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ፊተኛውም ሄዶ ጽዋውን በምድር ውስጥ አፈሰሰ፤ የአውሬውም ምልክት ባለባቸው ለምስሉም በሚሰግዱ ሰዎች ክፉኛ የሚነዘንዝ ቍስል ሆነባቸው።

Ver Capítulo Copiar




ራእይ 16:2
22 Referencias Cruzadas  

ፊተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ ደምም የተቀላቀለበት በረዶና እሳት ሆነ፤ ወደ ምድርም ተጣለ፤ የምድርም ሲሶው ተቃጠለ፤ የዛፎችም ሲሶው ተቃጠለ፤ የለመለመም ሣር ሁሉ ተቃጠለ።


ከስቃያቸውና ከቍስላቸውም የተነሣ የሰማይን አምላክ ተሳደቡ፤ ከሥራቸውም ንስሓ አልገቡም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፈውስ በሌ​ለው በግ​ብፅ ቍስል፥ በእ​ባ​ጭም፥ በቋ​ቁ​ቻም፥ በች​ፌም ይመ​ታ​ሃል።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር ስለ አል​ሰጠ ያን​ጊዜ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ ቀሠ​ፈው፤ ተል​ቶም ሞተ።


ስለ​ዚህ ጌታ የጽ​ዮን ታላ​ላቅ ሴቶች ልጆ​ችን ያዋ​ር​ዳ​ቸ​ዋል። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚያ ቀን ልብ​ሳ​ቸ​ውን ይገ​ል​ጣል።


ከዚ​ህም ሁሉ በኋላ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መድ​ኀ​ኒት በማ​ይ​ገ​ኝ​ለት ደዌ አን​ጀ​ቱን ቀሠ​ፈው።


አን​ተም ከደ​ዌው ጽናት የተ​ነሣ አን​ጀ​ትህ በየ​ዕ​ለቱ እስ​ኪ​ወጣ ድረስ በክፉ የአ​ን​ጀት ደዌ ትታ​መ​ማ​ለህ።”


ከሄ​ደ​ችም በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ በከ​ተ​ማ​ዪቱ ላይ መጣች፤ ታላቅ ሁከ​ትም ሆነ፤ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም ሰዎች ታላ​ቁ​ንም ታና​ሹ​ንም መታ፤ የው​ስጥ አካ​ላ​ቸ​ው​ንም በእ​ባጭ መታ​ቸው፤ የጌት ሰዎ​ችም የው​ስጥ አካ​ላ​ቸ​ውን ምስል ሠሩ፥


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ በአ​ዛ​ጦን ሰዎች ላይ ከበ​ደች፤ ክፉም ነገር አመ​ጣ​ች​ባ​ቸው፤ በእ​ነ​ር​ሱም ላይ በመ​ር​ከ​ቦች ውስጥ ወጣ፤ የአ​ዛ​ጦ​ን​ንና የአ​ው​ራ​ጃ​ዎ​ች​ዋ​ንም ሰዎች የው​ስጥ አካ​ላ​ቸ​ውን በዕ​ባጭ መታ፤ በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውም መካ​ከል አይ​ጦች ወጡ፤ በከ​ተ​ማ​ውም ታላቅ መቅ​ሠ​ፍት ሆነ።


በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ላይ ሲመጣ ያየ​ኸ​ውን ክፉ ሕማ​ምና ደዌ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ያር​ቅ​ል​ሃል፤ ያየ​ኸ​ው​ንም መከራ ሁሉ ወደ አንተ አያ​መ​ጣ​ውም፤ ከአ​ን​ተም በሚ​ጠ​ሉህ ሁሉ ላይ ይመ​ል​ሰ​ዋል።


እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ ስለ ሥራሽ ክፋት በሽቱ ፋንታ ትቢያ ይሁ​ን​ብሽ፤ በወ​ርቅ መታ​ጠ​ቂ​ያ​ሽም ፋንታ ገመድ ታጠቂ፤ በራስ ወርቅ ቀጸ​ላ​ሽም ፋንታ ቡሃ​ነት ይው​ጣ​ብሽ፤ በሐር መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያሽ ፋንታ ማቅ ልበሽ።


በደመናውም ላይ የተቀመጠው ማጭዱን ወደ ምድር ጣለው፤ ምድርም ታጨደች።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልት​ድን በማ​ት​ች​ል​በት በክፉ ቍስል ጕል​በ​ት​ህ​ንና ጭን​ህን ከእ​ግ​ርህ ጫማ እስከ አና​ትህ ድረስ ይመ​ታ​ሃል።


በፊተኛውም አውሬ ሥልጣን በእርሱ ፊት ሁሉን ያደርጋል። ለሞቱ የሆነውም ቍስል ተፈወሰለት፤ ለፊተኛው አውሬ ምድርና በእርሱ የሚኖሩት እንዲሰግዱለት ያደርጋል።


ሦስተኛም መልአክ በታላቅ ድምፅ እንዲህ እያለ ተከተላቸው፤ “ለአውሬውና ለምስሉ የሚሰግድ በግምባሩም ወይም በእጁ ምልክቱን የሚቀበል ማንም ቢኖር፥


ለሰባቱም መላእክት “ሄዳችሁ የእግዚአብሔርን ቁጣ ጽዋዎች በምድር ውስጥ አፍስሱ፤” የሚል ታላቅ ድምፅ ከመቅደሱ ሰማሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios