ኢሳይያስ 3:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 እኔ በእነርሱ ራስ ላይ የቡሃና የቈረቈር በሽታ አመጣለሁ፤ የውስጥ ገላቸውም ይጋለጣል።” Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም17 ስለዚህ፣ ጌታ በጽዮን ሴቶች ዐናት ላይ ቈረቈር ያመጣል፤ እግዚአብሔርም ራሳቸውን ቡሓ ያደርጋል።” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 ስለዚህ፤ ጌታ በጽዮን ሴቶች ዐናት ላይ ቆረቆር ያመጣል፤ ጌታም ራሳቸውን ቡሀ ያደርጋል። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 ስለዚህ ጌታ የጽዮን ታላላቅ ሴቶች ልጆችን ያዋርዳቸዋል። እግዚአብሔርም በዚያ ቀን ልብሳቸውን ይገልጣል። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 ስለዚህ ጌታ የጽዮንን ቆነጃጅት አናት በቡሀነት ይመታል፥ እግዚአብሔርም ኀፍረተ ሥጋችውን ይገልጣል። Ver Capítulo |
በዚያን ቀን ጌታ የኢየሩሳሌምን ሴቶች ጌጣጌጥ ማለት የእግራቸውን አልቦ፥ የጠጒራቸውን መሸፈኛ የአንገታቸውን ጌጣጌጥ፥ የጆሮአቸውን ጒትቻ፥ አምባራቸውን፥ የፊታቸውን መሸፈኛ፥ የጠጒራቸውን መሸፈኛ፥ በክንዳቸው ላይ የሚያደርጉትን ጌጥ፥ በወገባቸው ላይ የሚያስሩትን መቀነት፥ የሽቶ ጠርሙሳቸውን፥ ጥንቈላ የተጻፈበትን አሸንክታብ፥ የጣታቸውንና የአፍንጫቸውን ቀለበት፥ ለዓመት በዓል የሚሆነውን የክት ልብስ፥ መጐናጸፊያቸውንና ካባቸውን፥ የእጅ ቦርሳቸውን፥ መስታዋታቸውን፥ ከሐር የተሠራ የውስጥ ልብሳቸውን፥ ራስ ማሰሪያቸውንና ዐይነ ርግባቸውን ሁሉ ያስወግዳል።