ኢሳይያስ 27:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን እግዚአብሔር በፈጣኑ እባብ ደራጎን ላይ፥ በክፉውም እባብ ደራጎን ላይ ልዩ፥ ታላቅና ብርቱ ሰይፍን ያመጣል። በባሕርም ውስጥ ያለውን ዘንዶ ይገድለዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ቀን እግዚአብሔር፣ ተወርዋሪውን እባብ ሌዋታንን፣ የሚጠቀለለውን ዘንዶ ሌዋታንን በብርቱ፣ በታላቁና በኀይለኛ ሰይፍ ይቀጣዋል፤ የባሕሩንም ግዙፍ አውሬ ይቈራርጠዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም ቀን ጌታ ፈጣኑን እባብ ሌዋታንን፥ የሚጠቀለለውንም እባብ ሌዋታንን፥ በጠንካራ በታላቅ፥ በብርቱም ሰይፍ ይቀጣል፤ በባሕርም ውስጥ ያለውን ዘንዶ ይገድላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ቀን እግዚአብሔር በጽኑ፥ በታላቁና በኀያል ሰይፉ የሚስለከለከውንና የሚጠመጠመውን እባብ ሌዋታንን ይቀጣል፤ የባሕሩንም ዘንዶ ይገድላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን እግዚአብሔር ፈጣኑን እባብ ሌዋታንን ጠማማውንም እባብ ሌዋታንን በጠንካራ በታላቅም በብርቱም ሰይፍ ይቀጣል፥ በባሕርም ውስጥ ያለውን ዘንዶ ይገድላል። |
እነሆ፥ እግዚአብሔር በምድር በሚኖሩት ላይ ከመቅደሱ መቅሠፍቱን ያመጣል፤ ምድርም ደምዋን ትገልጣለች፤ ሙታኖችዋንም ከእንግዲህ ወዲህ አትከድንም።
እኔም ለሰይፍ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ፤ ሁላችሁም በሰይፍ ትገደላላችሁ፤ በፊቴ ክፉ ነገር አደረጋችሁ፤ ያልወደድሁትንም መረጣችሁ እንጂ በጠራኋችሁ ጊዜ አልመለሳችሁልኝምና፥ በተናገርሁም ጊዜ አልሰማችሁኝምና።”
ያንጊዜ ተኵላና በግ በአንድነት ይሰማራሉ፤ አንበሳም እንደ በሬ ገለባ ይበላል፤ የእባብም መብል ትቢያ ይሆናል። በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ አይጐዱም፤ አያጠፉምም፥” ይላል እግዚአብሔር።
ምድርም ሁሉ በእግዚአብሔር እሳት ሰውም ሁሉ በሰይፉ ይፈረድባቸዋል፤ በእግዚአብሔርም ተቀሥፈው የሞቱት ይበዛሉ።
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በላኝ፤ ከፋፈለኝም፤ እንደ ባዶ ዕቃም አደረገኝ፤ እንደ ዘንዶም ዋጠኝ፤ ከሚጣፍጠውም ሥጋዬ ሆዱን ሞላ።
እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በወንዞች መካከል የሚተኛ፥ ወንዙ የእኔ ነው፤ ለራሴም ሠርቼዋለሁ የሚል ታላቅ ዘንዶ የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን ሆይ! እነሆ በአንተ ላይ ነኝ።
በቀርሜሎስ ራስ ውስጥ ቢሸሸጉ ፈልጌ ከዚያ አወጣቸዋለሁ፤ በባሕሩም ጥልቅ ውስጥ ከዐይኔ ቢደበቁ በዚያ እባቡን አዝዛለሁ፤ እርሱም ይነድፋቸዋል፤
ለዘንዶውም ሰገዱለት፤ ለአውሬው ሥልጣንን ሰጥቶታልና፤ ለአውሬውም “አውሬውን ማን ይመስለዋል? እርሱንስ ሊዋጋ ማን ይችላል?” እያሉ ሰገዱለት።