ኢሳይያስ 17:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተክልን በተከልህበት ቀን ትበድላለህ፤ የዘራኸውም በበነጋው በምታወርስበት ቀን ይበቅላል፤ አባትም ለልጁ እንደሚያወርስ አንተም ለልጆችህ ታወርሳለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በተከልህበት ቀን እንዲበቅል፣ በዘራህበትም ማግስት እንዲያብብ ብታደርግ እንኳ፣ መከሩ በደዌና በማይሽር ሕመም ቀን፣ እንዳልነበረ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በተከልክበት ቀን እንዲበቅል፥ በዘራህበት ማግስት እንዲያብብ ብታደርግ እንኳን፥ ነገር ግን በኀዘንና በብርቱ ደዌ ቀን መከሩ እንዳልነበር ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያው በተከላችሁት ቀን አድጎ ቢያብብ እንኳ ከቶ አታመርቱትም፤ በዚህ ፈንታ የምታመርቱት ችግርና የማይፈወስ በሽታ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በተከልህበት ቀን ታበቅለዋለህ፥ በነጋውም ዘርህን እንዲያብብ ታደርገዋለህ፥ ነገር ግን በኀዘንና በትካዜ ቀን መከሩ ይሸሻል። |
አጫጅ የቆመውን እህል ሰብስቦ ዛላውን እንደሚያጭድ ይሆናል፤ በሸለቆ እሸትን እንደሚሰበስብም እንዲሁ ይሆናል።
ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፥ ካህናትም በእጃቸው ያጨበጭባሉ፥ ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ነገር ይወድዳሉ፤ በፍጻሜውስ ምን ታደርጋላችሁ?
ነፋስን ዘርተዋልና ዐውሎ ነፋስን አጨዱ፤ ለነዶአቸውም ኀይል የለውም፤ ከፍሬውም ዱቄት አይገኝም፤ ቢገኝም ጠላት ይበላዋል።
ኤፍሬም ታመመ፤ ሥሩም ደረቀ፤ ከእንግዲህም ወዲህ ፍሬ አያፈራም፤ ደግሞም ቢወልዱ የተወደደውን የማኅፀናቸውን ፍሬ እገድላለሁ።
ነገር ግን ልቡናህን እንደ ማጽናትህ፥ ንስሓም እንደ አለመግባትህ መጠን የእግዚአብሔር እውነተና ፍርድ በሚገለጥበት ቀን መቅሠፍትን ለራስህ ታከማቻለህ።