ሎጥም ዓይኖቹን አነሣ፤ በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውንም ሀገር ሁሉ ውኃ የሞላበት መሆኑን አየ፤ እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን ከማጥፋቱ አስቀድሞ እስከ ሴጎር ድረስ እንደ እግዚአብሔር ገነትና እንደ ግብፅ ምድር እንደ ነበረ አየ።
ኢሳይያስ 15:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሞዓብ ራሷን ይዛ ትጮኻለች፤ ለልቧም ይረዳታል፤ እስከ ሴጎርም ድረስ ብቻዋን ታለቅሳለች። ሞዓብ እንደ ሦስት ዓመት ጥጃ ናትና በሉሒት ዐቀበት ትጮኻለች። በአሮሜዎን መንገድም ይመለሳሉ፤ ይጮኻሉም፥ ጥፋትና መናወጥም ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልቤ ስለ ሞዓብ አለቀሰ፤ ስደተኞቿም እስከ ዞዓር፣ እስከ ዔግላት ሺሊሺያ ሸሹ፤ እንባቸውን እያፈሰሱ ወደ ሉሒት ወጡ፤ በሖሮናይም መንገድም፣ ስለ ጥፋታቸው ዋይ እያሉ ነጐዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልቤ ስለ ሞዓብ አለቀሰ፤ ከእርሷ የሚሸሹ ወደ ዞዐር ወደ ዔግላት ሺሊሺያ ኮበለሉ፤ በሉሒት አቀበት ላይ እያለቀሱ ወጡ፤ በሖሮናይምም መንገድ የዋይታ ጩኽት አሰሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለ ሞአብ ከልቤ አለቅሳለሁ፤ ሕዝቡ ወደ ጾዓርና ወደ ዔግላት ሸሊሺያ ኰበለሉ፤ ጥቂቶችም ወደ ሉሒት አቀበት ወጡ፤ በሚወጡበትም ጊዜ ያለቅሱ ነበር፤ ሌሎች ደግሞ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ስለ ጥፋታቸው እያለቀሱ ወደ ሖሮናይም ለማምለጥ ይሞክራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልቤ ስለ ሞዓብ ጮኸ፥ ከእርስዋ የሚሸሹ ወደ ዞዐር ወደ ዔግላት ሺሊሺያ ኮበለሉ፥ በሉሒት ዓቀበት ላይ እያለቀሱ ይወጣሉ፥ በሖሮናይምም መንገድ የዋይታ ጩኽት ያነሣሉ። |
ሎጥም ዓይኖቹን አነሣ፤ በዮርዳኖስ ዙሪያ ያለውንም ሀገር ሁሉ ውኃ የሞላበት መሆኑን አየ፤ እግዚአብሔር ሰዶምንና ገሞራን ከማጥፋቱ አስቀድሞ እስከ ሴጎር ድረስ እንደ እግዚአብሔር ገነትና እንደ ግብፅ ምድር እንደ ነበረ አየ።
ከሰዶም ንጉሥ ከባላ፥ ከገሞራ ንጉሥ ከበርሳ፥ ከአዳማ ንጉሥ ከሰናአር፥ ከሲባዮ ንጉሥ ከሲምቦር፤ ሴጎር ከተባለች ከባላ ንጉሥም ጋር ጦርነት አደረጉ።
እንግዲህ ፍጠንና በዚያ ራስህን አድን፤ ወደዚያ እስክትደርስ ድረስ ምንም አደርግ ዘንድ አልችልምና።” ስለዚህም የዚያች ከተማ ስም ሴጎር ተባለ።
ሀገሪቱም ሁላ በታላቅ ድምፅ አለቀሰች። ሕዝቡም ሁሉ በቄድሮን ወንዝ ተሻገሩ፤ ንጉሡም ደግሞ የቄድሮንን ወንዝ ተሻገረ፤ ንጉሡና ሕዝቡም ሁሉ ወደ ምድረ በዳ በሚወስደው መንገድ ተሻገሩ።
ዳዊትም ወደ ደብረ ዘይት ዐቀበት ወጣ፤ ሲወጣም ያለቅስ ነበር፤ ራሱንም ተከናንቦ ነበር፤ ያለጫማም ይሄድ ነበር፤ ከእርሱም ጋር የነበሩት ሕዝብ ሁሉ ተከናንበው ነበር፤ እያለቀሱም ይወጡ ነበር።
አሁንም እንዲህ እላለሁ፤ በሦስት ዓመት ውስጥ እንደ ምንደኛ ዓመት የሞዓብ ክብር ከብዙ ሀብትዋ ጋር ይዋረዳል፤ በቍጥርም ጥቂት ይቀራል፤ ክብርዋም አይገኝም።
ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሁከትና የጥፋት፥ የመረገጥና የስብራትም ቀን በጽዮን ሸለቆ ውስጥ ሆኖአል። ታናሹና ታላቁም ሸሽተው በተራራ ላይ ይቅበዘበዛሉ።
እግሮቻቸውም ለተንኮል ይሮጣሉ፤ ደምን ለማፍሰስም ይፈጥናሉ፤ ሰውን ለመግደል ይመክራሉ፤ ጕስቍልናና ቅጥቃጤ በመንገዳቸው አለ።
ይህን ባትሰሙ ነፍሴ ስለ ትዕቢታችሁ በስውር ታለቅሳለች፤ የእግዚአብሔርም መንጋ ተሰብሮአልና ዐይኔ ታነባለች፤ እንባንም ታፈስሳለች።
እኔም አንተን ተከትዬ አልደከምሁም፥ የሰውንም ቀን አልተመኘሁም፤ አንተ ታውቃለህ፤ ከከንፈሬ የወጣውም በፊትህ ነው።
አንጀቴ! አንጀቴ! ልቤ በጣም ታምሞአል፤ ነፍሴም አእምሮዋን አጥታለች፤ በውስጤም ልቤ ታውኮብኛል፤ ነፍሴም የመለከትን ድምፅና የሰልፍን ውካታ ሰምታለችና ዝም እል ዘንድ አልችልም።
በተራሮቹ ላይ አልቅሱ፤ በምድረ በዳም ጎዳና ላይ እዘኑ፤ ሰው ጠፍትዋልና፤ የሚመላለስም የለምና ሙሾውንም አሙሹ፤ የሰማይ ወፍ ድምፅንም እስከ ከብት ድምፅ ድረስ አይሰሙም፤ ደንግጠውም ተማርከው ሄዱ።
ሞዓብ ሆይ፥ ወዮልህ! የካሞስ ሕዝብ ሆይ፥ ጠፋህ፤ ወንዶች ልጆቻቸውን ለማደን፥ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለምርኮ፤ ለአሞራውያን ንጉሥ ለሴዎን ሰጠ።