ሆሴዕ 9:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ! ስጣቸው፤ ምን ትሰጣቸዋለህ? መካን ማኅፀንን፥ የደረቁትንም ጡቶች ስጣቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ስጣቸው፤ ምን ትሰጣቸዋለህ? የሚጨነግፉ ማሕፀኖችን፣ የደረቁ ጡቶችን ስጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ሆይ! ስጣቸው፤ ምን ትሰጣቸዋለህ? የሚጨነግፍን ማኅፀን የደረቀውንም ጡት ስጣቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌታ ሆይ! ለዚህ ሕዝብ ምን ትሰጠው፤ የሚጨነግፍ ማሕፀንና ደረቅ ጡት ስጣቸው! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤቱ፥ ስጣቸው፥ ምን ትሰጣቸዋለህ? የሚጨነግፍን ማኅፀን የደረቀውንም ጡት ስጣቸው። |
ኤፍሬም ታመመ፤ ሥሩም ደረቀ፤ ከእንግዲህም ወዲህ ፍሬ አያፈራም፤ ደግሞም ቢወልዱ የተወደደውን የማኅፀናቸውን ፍሬ እገድላለሁ።