Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሉቃስ 21:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ነገር ግን በዚያ ወራት ለፀ​ነ​ሱና ለሚ​ያ​ጠቡ ወዮ​ላ​ቸው፤ በም​ድር ላይ ጽኑ መከራ፥ በዚ​ህም ሕዝብ ላይ መቅ​ሠ​ፍት ይሆ​ና​ልና።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 በምድሪቱ ላይ ታላቅ መከራ ይሆናል፤ በዚህም ሕዝብ ላይ ቍጣ ይመጣል፤ ስለዚህ በዚያ ወቅት ለነፍሰ ጡሮችና ለሚያጠቡ እናቶች ወዮላቸው!

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 በነዚያ ቀናት ለነፍሰ ጡሮችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው፤ ታላቅ ችግር በምድር ላይ፥ በዚህም ሕዝብ ላይ ቁጣ ይሆናልና፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 በዚያን ጊዜ ለነፍሰጡሮችና ለሚያጠቡ እመጫቶች ወዮላቸው! በምድር ላይ ታላቅ መከራ ይሆናል፤ በዚህም ሕዝብ ላይ የእግዚአብሔር ቊጣ ይመጣል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 በዚያን ወራት ለእርጕዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው፤ ታላቅ ችግር በምድር ላይ፥ በዚህም ሕዝብ ላይ ቍጣ ይሆናልና፤

Ver Capítulo Copiar




ሉቃስ 21:23
18 Referencias Cruzadas  

መካ​ኖች፥ ያል​ወ​ለዱ ማኅ​ፀ​ኖ​ችና ያላ​ጠቡ ጡቶ​ችም የተ​መ​ሰ​ገኑ ናቸው የሚ​ሉ​በት ወራት ይመ​ጣ​ልና።


በዚያን ወራትም ለርጉዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው።


በዚያችም ወራት ለርጉዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው።


ዮድ። የር​ኅ​ሩ​ኆች ሴቶች እጆች ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ቀቅ​ለ​ዋል፤ የወ​ገኔ ሴት ልጅ በመ​ቀ​ጥ​ቀ​ጥዋ መብል ሆኖ​አ​ቸው።


ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ተነሥቶ የሚጀመርበት ጊዜ ደርሶአልና፤ አስቀድሞም በእኛ የሚጀመር ከሆነ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ መጨረሻቸው ምን ይሆን?


አሁንም እናንተ ባለጠጎች! ስለሚደርስባችሁ ጭንቅ ዋይ ዋይ እያላችሁ አልቅሱ።


ሁልጊዜ ኀጢአታቸውን ይፈጽሙ ዘንድ አሕዛብ እንዲድኑ እንዳንናገራቸው ይከለክሉናልና። ነገር ግን ቍጣው ወደ እነርሱ ፈጽሞ ደርሶአል።


ነገር ግን ለድ​ሆች መራ​ራ​ትን፥ ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር መተ​ባ​በ​ርን አት​ርሱ፤ እን​ዲህ ያለው መሥ​ዋ​ዕት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ ያሰ​ኘ​ዋ​ልና።


ጠላ​ቶ​ችሽ አን​ቺን የሚ​ከ​ቡ​በት ቀን ይመ​ጣል፤ ይከ​ት​ሙ​ብ​ሻል፤ ያስ​ጨ​ን​ቁ​ሻ​ልም፤ በአ​ራቱ ማዕ​ዘ​ንም ከብ​በው ይይ​ዙ​ሻል።


ነገር ግን እነ​ዚ​ያን ልነ​ግ​ሥ​ባ​ቸው ያል​ወ​ደ​ዱ​ትን ጠላ​ቶ​ችን ወደ​ዚህ አም​ጡና በፊቴ ውጉ​አ​ቸው።”


በዚህም ድንጋይ ላይ የሚወድቅ ይቀጠቀጣል፤ ድንጋዩ ግን የሚወድቅበትን ሁሉ ይፈጨዋል።”


እነርሱም “ክፉዎችን በክፉ ያጠፋቸዋል፤ የወይኑንም አትክልት ፍሬውን በየጊዜው ለሚያስረክቡ ለሌሎች ገበሬዎች ይሰጠዋል፤” አሉት።


“እነዚህ የሚሉትን አትሰማምን?” አሉት። ኢየሱስም “እሰማለሁ፤ ‘ከሕፃናትና ከሚጠቡት አፍ ምስጋናን ለራስህ አዘጋጀህ፤’ የሚለውን ቃል ከቶ አላነበባችሁምን?” አላቸው።


ነገር ግን እን​ዲህ ይመ​ስ​ለ​ኛል፤ በግድ ይህ ሊመ​ረጥ ይሻ​ላ​ልና እን​ዲህ ሆኖ ቢኖር ለሰው ይሻ​ለ​ዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios