Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሆሴዕ 9:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እኔ እንደ አየሁ የኤ​ፍ​ሬም ልጆች ለወ​ጥ​መድ ተሰ​ጥ​ተ​ዋል፤ ኤፍ​ሬ​ምም ልጆ​ቹን ወደ ገዳ​ዮች አወጣ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ኤፍሬምን እንደ ጢሮስ፣ በመልካም ስፍራ ተተክሎ አየሁት፤ አሁን ግን ኤፍሬም ልጆቹን፣ ለነፍሰ ገዳዮች አሳልፎ ይሰጣል።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ኤፍሬምን እንደ ጢሮስ በለመለመ መስክ ተተክሎ አየሁት፤ አሁን ግን ኤፍሬም ልጆቹን ወደ ገዳዩች ያወጣል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እስራኤልን በመልካም መሬት ላይ እንደ ተተከለች የዘንባባ ዛፍ ሆና አየኋት፤ እስራኤላውያን ግን ልጆቻቸውን ለዕርድ አቀረቡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 እኔ እንዳየሁ የኤፍሬም ልጆች ለምርኮ ተሰጥተዋል፥ ኤፍሬምም ልጆቹን ወደ ገዳዩች ያወጣል።

Ver Capítulo Copiar




ሆሴዕ 9:13
13 Referencias Cruzadas  

በባ​ሕር መግ​ቢያ የም​ት​ኖር፥ በብ​ዙም ደሴ​ቶች ላይ ከሚ​ኖሩ አሕ​ዛብ ጋር ንግ​ድን የም​ታ​ደ​ርግ ጢሮ​ስን እን​ዲህ በላት፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ጢሮስ ሆይ! አንቺ፦ በው​በት ፍጹም ነኝ ብለ​ሻል።


ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሚስ​ትህ በከ​ተ​ማ​ይቱ ውስጥ አመ​ን​ዝራ ትሆ​ና​ለች፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ች​ህም በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃሉ፤ ምድ​ር​ህም በገ​መድ ትከ​ፈ​ላ​ለች፤ አን​ተም በረ​ከ​ሰች ምድር ትሞ​ታ​ለህ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ከም​ድሩ ተማ​ርኮ ይሄ​ዳል።”


በአ​ሦ​ራ​ው​ያ​ንም መን​ገድ አጠ​ገብ እንደ ተራበ ድብ እገ​ጥ​ማ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የል​ባ​ቸ​ው​ንም ሥር እቈ​ር​ጣ​ለሁ፤ በዚ​ያም የዱር አን​በ​ሶች ይበ​ሏ​ቸ​ዋል፤ የም​ድረ በዳም አራ​ዊት ይነ​ጣ​ጠ​ቋ​ቸ​ዋል።


በሕ​ዝ​ብ​ህም መካ​ከል ጥፋት ይነ​ሣል፤ እና​ትም በል​ጆ​ችዋ ላይ በተ​ጣ​ለች ጊዜ የሰ​ል​ማን አለቃ ቤት​አ​ር​ብ​ኤ​ልን በጦ​ር​ነት ቀን እን​ዳ​ፈ​ረሰ፥ አም​ባ​ዎ​ችህ ሁሉ ይፈ​ር​ሳሉ።


ኤፍ​ሬም ታመመ፤ ሥሩም ደረቀ፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ ፍሬ አያ​ፈ​ራም፤ ደግ​ሞም ቢወ​ልዱ የተ​ወ​ደ​ደ​ውን የማ​ኅ​ፀ​ና​ቸ​ውን ፍሬ እገ​ድ​ላ​ለሁ።


ሕፃ​ና​ቱ​ንም በመ​ን​ገድ፤ ጐል​ማ​ሶ​ቹ​ንም በአ​ደ​ባ​ባ​ዮ​ቻ​ችን ያጠፋ ዘንድ ሞት በመ​ስ​ኮ​ቶ​ቻ​ችን ወደ ሀገ​ራ​ችን ገብ​ቶ​አ​ልና።


በዚያ ጊዜም ምና​ሔም ቴር​ሳን፥ በእ​ር​ስ​ዋም ያሉ​ትን ሁሉ፥ ዳር​ቻ​ዋ​ንም መታ፤ ይከ​ፍ​ቱ​ለ​ትም ዘንድ አል​ወ​ደ​ዱ​ምና መታት፤ በእ​ር​ስ​ዋም የነ​በ​ሩ​ትን እር​ጉ​ዞች ሁሉ ሰነ​ጠ​ቃ​ቸው።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን የኤ​ፍ​ሬ​ምን ዘር ሁሉ፥ እንደ ጣልሁ፥ እን​ዲሁ ከፊቴ እጥ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።”


ልጆቹ ቢበዙ ለጥ​ፋት ይሆ​ናሉ፤ ቢያ​ድ​ጉም ለማ​ኞች ይሆ​ናሉ።


ታው። የሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​ኝን እንደ በዓል ቀን ከዙ​ሪ​ያዬ ጠራ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ ቀንም ያመ​ለጠ ወይም የቀረ አል​ተ​ገ​ኘም፤ ያቀ​ማ​ጠ​ል​ኋ​ቸ​ው​ንና ያሳ​ደ​ግ​ኋ​ቸ​ውን ጠላቴ በላ​ቸው።


ሰማ​ርያ በአ​ም​ላ​ክዋ ላይ ዐም​ፃ​ለ​ችና ፈጽማ ትጠ​ፋ​ለች፤ በሰ​ይ​ፍም ይወ​ድ​ቃሉ፤ ሕፃ​ኖ​ቻ​ቸ​ው​ንም ይጥ​ሉ​አ​ቸ​ዋል፤ እር​ጉ​ዞ​ቻ​ቸ​ው​ንም ይሰ​ነ​ጥ​ቋ​ቸ​ዋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios