በዚያ ጊዜም ምናሔም ቴርሳን፥ በእርስዋም ያሉትን ሁሉ፥ ዳርቻዋንም መታ፤ ይከፍቱለትም ዘንድ አልወደዱምና መታት፤ በእርስዋም የነበሩትን እርጉዞች ሁሉ ሰነጠቃቸው።
ሆሴዕ 9:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ እንደ አየሁ የኤፍሬም ልጆች ለወጥመድ ተሰጥተዋል፤ ኤፍሬምም ልጆቹን ወደ ገዳዮች አወጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤፍሬምን እንደ ጢሮስ፣ በመልካም ስፍራ ተተክሎ አየሁት፤ አሁን ግን ኤፍሬም ልጆቹን፣ ለነፍሰ ገዳዮች አሳልፎ ይሰጣል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤፍሬምን እንደ ጢሮስ በለመለመ መስክ ተተክሎ አየሁት፤ አሁን ግን ኤፍሬም ልጆቹን ወደ ገዳዩች ያወጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤልን በመልካም መሬት ላይ እንደ ተተከለች የዘንባባ ዛፍ ሆና አየኋት፤ እስራኤላውያን ግን ልጆቻቸውን ለዕርድ አቀረቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ እንዳየሁ የኤፍሬም ልጆች ለምርኮ ተሰጥተዋል፥ ኤፍሬምም ልጆቹን ወደ ገዳዩች ያወጣል። |
በዚያ ጊዜም ምናሔም ቴርሳን፥ በእርስዋም ያሉትን ሁሉ፥ ዳርቻዋንም መታ፤ ይከፍቱለትም ዘንድ አልወደዱምና መታት፤ በእርስዋም የነበሩትን እርጉዞች ሁሉ ሰነጠቃቸው።
ሕፃናቱንም በመንገድ፤ ጐልማሶቹንም በአደባባዮቻችን ያጠፋ ዘንድ ሞት በመስኮቶቻችን ወደ ሀገራችን ገብቶአልና።
ታው። የሚያሳድዱኝን እንደ በዓል ቀን ከዙሪያዬ ጠራ፥ በእግዚአብሔር ቍጣ ቀንም ያመለጠ ወይም የቀረ አልተገኘም፤ ያቀማጠልኋቸውንና ያሳደግኋቸውን ጠላቴ በላቸው።
በባሕር መግቢያ የምትኖር፥ በብዙም ደሴቶች ላይ ከሚኖሩ አሕዛብ ጋር ንግድን የምታደርግ ጢሮስን እንዲህ በላት፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ጢሮስ ሆይ! አንቺ፦ በውበት ፍጹም ነኝ ብለሻል።
በሕዝብህም መካከል ጥፋት ይነሣል፤ እናትም በልጆችዋ ላይ በተጣለች ጊዜ የሰልማን አለቃ ቤትአርብኤልን በጦርነት ቀን እንዳፈረሰ፥ አምባዎችህ ሁሉ ይፈርሳሉ።
በአሦራውያንም መንገድ አጠገብ እንደ ተራበ ድብ እገጥማቸዋለሁ፤ የልባቸውንም ሥር እቈርጣለሁ፤ በዚያም የዱር አንበሶች ይበሏቸዋል፤ የምድረ በዳም አራዊት ይነጣጠቋቸዋል።
ሰማርያ በአምላክዋ ላይ ዐምፃለችና ፈጽማ ትጠፋለች፤ በሰይፍም ይወድቃሉ፤ ሕፃኖቻቸውንም ይጥሉአቸዋል፤ እርጉዞቻቸውንም ይሰነጥቋቸዋል።
ኤፍሬም ታመመ፤ ሥሩም ደረቀ፤ ከእንግዲህም ወዲህ ፍሬ አያፈራም፤ ደግሞም ቢወልዱ የተወደደውን የማኅፀናቸውን ፍሬ እገድላለሁ።
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሚስትህ በከተማይቱ ውስጥ አመንዝራ ትሆናለች፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህም በሰይፍ ይወድቃሉ፤ ምድርህም በገመድ ትከፈላለች፤ አንተም በረከሰች ምድር ትሞታለህ፤ እስራኤልም ከምድሩ ተማርኮ ይሄዳል።”