በገባዖንም ወዳለው ወደ ታላቁ ድንጋይ በደረሱ ጊዜ አሜሳይ በፊታቸው መጣ፤ ኢዮአብም የሰልፍ ልብስ ለብሶ ነበር፤ በላዩም መታጠቂያ ነበረ፤ በወገቡም ላይ ሰገባ ያለው ሰይፍ ታጥቆ ነበር፤ እርሱም ሲራመድ ሰይፉ ወደቀ።
ሆሴዕ 6:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ገለዓድ ከንቱን የምትሠራና በደም የተቀባች ከተማ ናት፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ገለዓድ በደም የተበከለች፣ የክፉዎች ሰዎች ከተማ ናት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ገለዓድ በደም የተቀባች የክፉ አድራጊዎች ከተማ ነች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ገለዓድ ክፉ ሰዎችና በደም የተበከሉ ነፍሰ ገዳዮች የሞሉባት ከተማ ሆናለች! መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ገለዓድ ኃጢአትን የሚሠሩ ሰዎች ከተማ፥ በደምም የተቀባ ነው። |
በገባዖንም ወዳለው ወደ ታላቁ ድንጋይ በደረሱ ጊዜ አሜሳይ በፊታቸው መጣ፤ ኢዮአብም የሰልፍ ልብስ ለብሶ ነበር፤ በላዩም መታጠቂያ ነበረ፤ በወገቡም ላይ ሰገባ ያለው ሰይፍ ታጥቆ ነበር፤ እርሱም ሲራመድ ሰይፉ ወደቀ።
አበኔርም ወደ ኬብሮን በተመለሰ ጊዜ ኢዮአብ በበር ውስጥ በቈይታ ይናገረው ዘንድ ወደ አጠገቡ ወሰደው፤ በዚያም ለወንድሙ ለአሣሄል ደም ተበቅሎ ወገቡን መታው፤ ሞተም።
አንተም ደግሞ የሶርህያ ልጅ ኢዮአብ፥ ሁለቱን የእስራኤል ሠራዊት አለቆች የኔር ልጅ አበኔርን የኢያቴርንም ልጅ አሜሳይን ገድሎ፥ በእኔ ላይ ያደረገውን ታውቃለህ፤ የጦርነትንም ደም በሰላም አፈሰሰ፤ በወገቡም ባለው ድግና በእግሩም ባለው ጫማ ንጹሕ ደም አኖረ።
እኔም ለመታረድ እንደሚነዳ እንደ የዋህ ጠቦት በግ ሆንሁ፤ እነርሱም በእንጀራው ዕንጨት እንጨምር ስሙም ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይታሰብ ከሕያዋን ምድር እናጥፋው ብለው ክፉ ምክርን እንዳሰቡብኝ አላወቅሁም ነበር።
በገለዓድ ባይሆንም እንኳ በጌልጌላ መሥዋዕታቸውን የሚሠዉ አለቆች ስተዋል፤ መሠዊያዎቻቸውም በእርሻ ትልም ላይ እንደ አለ የድንጋይ ክምር ነው።
ካህናት ሆይ! ይህን ስሙ፤ የእስራኤል ቤት ሆይ! አድምጡ፤ የንጉሥ ቤት ሆይ! ልብ አድርጉ፤ ለሚመለከት ወጥመድ፥ በታቦርም ላይ የተዘረጋ አሽክላ ሆናችኋልና ፍርድ በእናንተ ላይ ነው።
ልኮም ወደ ኢየሩሳሌም አደባባይ እንዲያስመጣውና እንዲሰጣቸው ለመኑት፤ እነርሱ ግን ወደዚያ ሄደው በመንገድ ሸምቀው ሊገድሉት ፈልገው ነበር።
ከጋድም ነገድ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን በገለዓድ ውስጥ ራሞትንና መሰማርያዋን፥ ቃሚንንና መሰማርያዋን፤