የእስራኤልም ልጆች ከግብፅ ንጉሥ ከፈርዖን እጅ፥ ከግብፅ ምድር ያወጣቸውን አምላካቸውን እግዚአብሔርን በድለው ነበርና፥ ሌሎችንም አማልክት አምልከው ነበርና፤
ሆሴዕ 4:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በተራሮችም ራስና በኮረብታዎች ላይ ይሠዋሉ፤ ጥላውም መልካም ነውና ከኮምበልና ከልብን፥ ከአሆማም ዛፍ በታች ያርዳሉ፤ ስለዚህ ሴቶች ልጆቻችሁ ይሰስናሉ፤ ሙሽሮቻችሁም ያመነዝራሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በተራሮችም ጫፍ ላይ ይሠዋሉ፤ መልካም ጥላ ባለው፣ በወርካ፣ በኮምቦልና በአሆማ ዛፍ ሥር፣ በኰረብቶችም ላይ የሚቃጠል ቍርባን ያቀርባሉ። ስለዚህ ሴቶች ልጆቻችሁ ዘማውያን፣ ምራቶቻችሁም አመንዝራዎች ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በተራሮችም ራስ ላይ ይሠዋሉ፤ ጥላውም መልካም ነውና ከባሉጥና ከልብን ከአሆማም ዛፍ በታች በኮረብቶች ላይ ያጥናሉ፤ ስለዚህ ሴቶች ልጆቻችሁ ዘማውያን ይሆናሉ፥ ምራቶቻችሁም ያመነዝራሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በየተራራው ላይ መሥዋዕት ያቀርባሉ፤ በየኮረብታው ላይ ቊርባን ያቀርባሉ፤ ይህንንም የሚያደርጉት ታላላቅ በሆኑና ቅርንጫፋቸው በተንሰራፋ ጥላቸው መልካም በሆነ ዋርካ፥ በለሳና ጥድ ሥር ነው። በዚህ ምክንያት ሴቶች ልጆቻችሁ ዘማውያን ይሆናሉ። ምራቶቻችሁም ያመነዝራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በተራሮችም ራስ ላይ ይሠዋሉ፥ ጥላውም መልካም ነውና ከኮምበልና ከልብን ከአሆማም ዛፍ በታች በኮረብቶች ላይ ያጥናሉ፥ ስለዚህ ሴቶች ልጆቻችሁ ይገለሙታሉ፥ ሙሽሮቻችሁም ያመነዝራሉ። |
የእስራኤልም ልጆች ከግብፅ ንጉሥ ከፈርዖን እጅ፥ ከግብፅ ምድር ያወጣቸውን አምላካቸውን እግዚአብሔርን በድለው ነበርና፥ ሌሎችንም አማልክት አምልከው ነበርና፤
ሴቶቹም ለማምለኪያ ዐፀድ መጋረጃ ይፈትሉባቸው የነበሩትን በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ያሉትን የሰዶማውያንን ቤቶች አፈረሰ።
እናንተ በለመለመ ዛፍ ሁሉ በታች በጣዖት ደስ የምትሰኙ፥ እናንተም በሸለቆች ውስጥ በዓለትም ስንጣቂዎች በታች ልጆቻችሁን የምትሠዉ፥ እናንተ የጥፋት ልጆችና የዐመፀኞች ዘሮች አይደላችሁምን?
ከጥንት ጀምሬ ቀንበርሽን ሰብሬአለሁ፤ እስራትሽንም ቈርጫለሁ፤ አንቺም፦ አላገለግልም አልሽ፤ ነገር ግን ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ ላይ፤ ከለምለምም ዛፍ ሁሉ በታች ለማመንዘር ተጋደምሽ።
በአምላክሽ በእግዚአብሔር ላይ እንዳመፅሽ፥ መንገድሽንም ከለመለመ ዛፍ ሁሉ በታች ለእንግዶች እንደ ዘረጋሽ፥ ቃሌንም እንዳልሰማሽ ኀጢአትሽን ብቻ ዕወቂ ይላል እግዚአብሔር።
እግዚአብሔርም በንጉሡ በኢዮስያስ ዘመን እንዲህ አለኝ፥ “ከዳተኛዪቱ እስራኤል ያደረገችውን አየህን? ወደ ረዘመው ተራራ ሁሉ፥ ወደ ለመለመ ዛፍም ሁሉ በታች ሄደች፤ በዚያም አመነዘረች።
ሰውነታችሁንም ታጠፉ ዘንድ፥ በምድርም አሕዛብ ሁሉ መካከል መረገሚያና መሰደቢያ ትሆኑ ዘንድ፥ ለመቀመጥ በገባችሁባት በግብፅ ምድር ለሌሎች አማልክት በማጠናችሁ በእጃችሁ ሥራ ለምን ታስቈጡኛላችሁ?
ከልብስሽም ወስደሽ በመርፌ የተጠለፉ ጣዖታትን ሠራሽ፤ አመነዘርሽባቸውም፤ ስለዚህ ፈጽመሽ አልገባሽም፤ ከእንግዲህም ወዲህ እንዲህ ያለ ነገር አይሆንም።
በየመንገዱ ራስ ከፍ ያለውን ቦታሽን ሠራሽ፤ ውበትሽንም አረከስሽ፤ ለመንገድ አላፊም ሁሉ እግርሽን ገለጥሽ፤ ዝሙትሽንም አበዛሽ።
ሬሳዎቻቸው በጣዖቶቻቸው መካከልና በመሠዊያዎቻቸው ዙሪያ በወደቁ ጊዜ በረዣዥም ኮረብታ ሁሉ፥ በተራሮችም ራሶች ሁሉ፥ በዕንጨቱም ጥላ ሥር ለጣዖቶቻቸው ሁሉ፥ መልካም መዓዛን ባጠኑበት ከቅጠሉ ሁሉ በታች ሬሳዎቻቸው በወደቁ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
የእስራኤል ኀጢአት የሆኑት የአዎን የኮረብታው መስገጃዎች ይፈርሳሉ፤ እሾህና አሜከላም በመሠዊያዎቻቸው ላይ ይበቅላሉ፤ ተራሮችንም፥ “ክደኑን፤ ኮረብቶችንም፦ ውደቁብን” ይሉአቸዋል።
እኔን ረስታ ወዳጆችዋን እየተከተለች፥ በጕትቾችዋና በጌጥዋም እያጌጠች ለበኣሊም የሠዋችበትን ወራት እበቀልባታለሁ፥” ይላል እግዚአብሔር።
ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ሚስትህ በከተማይቱ ውስጥ አመንዝራ ትሆናለች፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆችህም በሰይፍ ይወድቃሉ፤ ምድርህም በገመድ ትከፈላለች፤ አንተም በረከሰች ምድር ትሞታለህ፤ እስራኤልም ከምድሩ ተማርኮ ይሄዳል።”