ሆሴዕ 2:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምድርም ላይ ለእኔ እዘራታለሁ፤ ይቅርታ የሌላትን ይቅር እላታለሁ፤ ያልተወደደች የነበረችውን እወድዳታለሁ፤ ሕዝቤም ያልሆነውን፥ “አንተ ሕዝቤ ነህ” እለዋለሁ፤ እርሱም፥ “አንተ ጌታዬና አምላኬ ነህ” ይለኛል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ ራሴ ስል በምድሪቱ እተክላታለሁ፤ ‘ምሕረትን ያላገኘ’ ብዬ የጠራሁትንም እምረዋለሁ፤ ‘ሕዝቤ አይደላችሁም’ ተብለው የተጠሩትንም፣ ‘ሕዝቤ’ እላቸዋለሁ፤ እነርሱም፣ ‘አንተ አምላኬ ነህ’ ይላሉ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “እንዲህም ይሆናል፥ በዚያን ቀን እመልሳለሁ ይላል ጌታ፥ ለሰማይ እመልሳለሁ፥ ሰማይም ለምድር ይመልሳል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቤን በምድሪቱ ላይ እመሠርታለሁ፤ እንዲበለጽጉም አደርጋቸዋለሁ፤ ‘ምሕረት አይደረግላችሁም’ የተባሉትን ምሕረት አደርግላቸዋለሁ፤ ‘ሕዝቤ አይደላችሁም’ የተባሉትንም ‘ሕዝቤ ናችሁ’ እላቸዋለሁ፤ እነርሱም ‘አንተ አምላካችን ነህ’ ይሉኛል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያንም ቀን እመልሳለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር ለሰማይ እመልሳለሁ፥ ሰማይም ለምድር ይመልሳል፥ |
ይህ፦ እኔ የእግዚአብሔር ነኝ ይላል፤ ያም በያዕቆብ ስም ይጠራል፤ ይህም፦ እኔ የእግዚአብሔር ነኝ ብሎ በእጁ ይጽፋል፤ በእስራኤልም ስም ይጠራል።”
ጌታ ሆይ! አንተ ኀይሌና ረዳቴ፥ በመከራም ቀን መጠጊያዬ ነህ፤ ከምድር ዳርቻ አሕዛብ ወደ አንተ መጥተው፥ “በእውነት አባቶቻችን ውሸትንና ከንቱን ነገር ለምንም የማይረባቸውን ጣዖትን ሠርተዋል” ይላሉ።
እኔም ደግሞ በአብርሃምና በይስሐቅ በያዕቆብም ዘር ላይ ገዢዎች ይሆኑ ዘንድ ከዘሩ እንዳላስነሣ፥ የያዕቆብንና የባሪያዬን የዳዊትን ዘር እጥላለሁ፤ ምርኮአቸውን እመልሳለሁና፥ እምራቸውማለሁና።”
ደግሞ ፀነሰች፤ ሴት ልጅንም ወለደች። እግዚአብሔርም፥ “መለየትን እለያቸዋለሁ እንጂ ይቅር እላቸው ዘንድ የእስራኤልን ቤት ከእንግዲህ ወዲህ አልምራቸውምና ስምዋን ኢሥህልት ብለህ ጥራት፤
ሦስተኛውንም ክፍል ወደ እሳት አገባለሁ፥ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፥ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፣ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፣ እኔም፦ ይህ ሕዝቤ ነው እላለሁ፣ እርሱም፦ እግዚአብሔር አምላኬ ነው ይላል።
በኢየሩሳሌም ላይ ከመጡት ከአሕዛብ ሁሉ የቀሩት ሁሉ ለንጉሡ ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር ይሰግዱ ዘንድ፥ የዳስ በዓልንም ያከብሩ ዘንድ በየዓመቱ ይወጣሉ።
በዚያም ቀን ብዙ አሕዛብ ወደ እግዚአብሔር ይጠጋሉ፥ ሕዝብም ይሆኑኛል፣ በመካከልሽም እኖራለሁ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ወደ አንቺ እንደ ላከኝ ታውቂአለሽ።
ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያዋ ድረስ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፣ በየስፍራውም ለስሜ ዕጣን ያጥናሉ፥ ንጹሕም ቍርባን ያቀርባሉ፣ ስሜ በአሕዛብ ዘንድ ታላቅ ይሆናልና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።