ሆሴዕ 13:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቍጣዬ ንጉሥን ሰጠሁህ፤ በመዓቴም ሻርሁት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በቍጣዬ ንጉሥን ሰጠሁህ፤ በመዓቴም ሻርሁት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቁጣዬ ንጉሥን ሰጠሁህ፥ በመዓቴም ሻርሁት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቊጣዬ ነገሥታትን ሰጥቻችሁ ነበር፤ ነገር ግን በከፍተኛ ቊጣዬ አጠፋኋቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቁጣዬ ንጉሥን ሰጠሁህ፥ በመዓቴም ሻርሁት። |
የእስራኤል ልጆች ያለ ንጉሥና ያለ አለቃ፥ ያለ መሥዋዕትና ያለ ምሥዋዕ፤ ያለ ካህንና ያለ ራእይ፤ ያለ ኤፉድና ያለ ተራፊም ብዙ ወራት ይቀመጣሉና፤
ራሳቸውን አነገሡ፤ ከእኔም ዘንድ አይደለም፤ አለቆችንም አደረጉ፤ እኔም አላወቅሁም፤ ለጥፋታቸውም ከብራቸውና ከወርቃቸው ጣዖታትን ለራሳቸው አደረጉ።
ዛሬ ግን ከመከራችሁና ከጭንቃችሁ ሁሉ ያዳናችሁን እግዚአብሔርን ንቃችሁ፦ ‘እንዲህ አይሁን፤ ነገር ግን ንጉሥ አንግሥልን’ አላችሁት። አሁንም በየነገዳችሁና በየወገናችሁ በእግዚአብሔር ፊት ቁሙ” አላቸው።
ሳሙኤልም ሳኦልን፥ “የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና፥ እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ንጉሥ እንዳትሆን ንቆሃልና ከአንተ ጋር አልመለስም” አለው።
እግዚአብሔርም ሳሙኤልን፥ “በእስራኤል ላይ እንዳይነግሥ ለናቅሁት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ነው? የዘይቱን ቀንድ ሞልተህ ና፤ በልጆቹ መካከል ለእኔ ንጉሥ አዘጋጅቼአለሁና ወደ እሴይ ወደ ቤተ ልሔም እልክሃለሁ” አለው።