የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ወይን ቦታ እርሱ የእስራኤል ቤት ነው፤ ተወዳጁ አዲስ ተክልም የይሁዳ ሰዎች ናቸው፤ ፍርድን ያደርጋል ብየ እጠብቅ ነበር፤ እነሆም፥ ዐመፅን አደረገ፤ ጽድቅንም አይደለም፥ ጩኸትን እንጂ።
ሆሴዕ 10:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የማይረባውን የሐሰት ቃል ይናገራሉ፤ ቃል ኪዳንም ያደርጋሉ፤ ስለዚህ መርዛም ሣር በእርሻ ትልም ላይ እንደሚበቅል ፍርድ ይበቅልባቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከንቱ ተስፋ ይሰጣሉ፤ በሐሰት በመማል፣ ቃል ኪዳን ያደርጋሉ፤ ስለዚህም ፍርድ፣ በዕርሻ ውስጥ እንደሚገኝ መርዛማ ዐረም ይበቅላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የማይረባውን ቃላት ተናገሩ፤ በሐሰት መሐላ ቃል ኪዳን አደረጉ፤ ስለዚህ መርዛም አረም በእርሻ ትልሞች ላይ እንደሚበቅል መቅሠፍት በቀለባቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሐሰት መሐላ ቃል ኪዳን በመግባት ከንቱ ንግግር ይናገራሉ፤ ስለዚህ በእርሻ መሬት ውስጥ መርዘኛ አረም እንደሚበቅል በእነርሱም መካከል ክርክር ይስፋፋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የማይረባውን ቃል ይናገራሉ፥ ቃል ኪዳን በገቡ ጊዜ በሐሰት ይምላሉ፥ ስለዚህ መርዛም ሣር በእርሻ ትልም ላይ እንደሚበቅል መቅሠፍት ይበቅልባቸዋል። |
የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ወይን ቦታ እርሱ የእስራኤል ቤት ነው፤ ተወዳጁ አዲስ ተክልም የይሁዳ ሰዎች ናቸው፤ ፍርድን ያደርጋል ብየ እጠብቅ ነበር፤ እነሆም፥ ዐመፅን አደረገ፤ ጽድቅንም አይደለም፥ ጩኸትን እንጂ።
ፍርድን ወደ ቍጣ፥ የእውነትንም ፍሬ ወደ እሬት ለውጣችኋልና፥ በውኑ ፈረሶች በጭንጫ ላይ ይሮጣሉን? ወይስ በሬዎች በዚያ ላይ ያርሳሉን?
ሄዶ የእነዚያን አሕዛብ አማልክት ያመልክ ዘንድ ከአምላካችሁ ከእግዚአብሔር ልቡን ዛሬ የሚያስት ወንድ ወይም ሴት ወይም ወገን ወይም ነገድ አይኑርባችሁ፤ ሐሞትና እሬትም የሚያበቅል ሥር አይሁንባችሁ።
እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፥ “እነሆ፥ ከአባቶችህ ጋር ታንቀላፋለህ፤ ይህም ሕዝብ ይነሣል፤ ይቀመጥባትም ዘንድ በሚሄድባት ምድር መካከል ያሉትን ሌሎችን አማልክት ተከትሎ ያመነዝራል፤ እኔንም ይተወኛል፤ ከእነርሱም ጋር ያደረግሁትን ቃል ኪዳን ያፈርሳሉ።
በዚያም ቀን ቍጣዬ ይነድድባቸዋል፤ እተዋቸውማለሁ፤ ፊቴንም ከእነርሱ እመልሳለሁ፤ ለጠላቶቻቸውም መብል ይሆናሉ፤ በዚያም ቀን፦ በእውነት አምላካችን እግዚአብሔር ትቶናልና፥ በእኛም መካከል የለምና ይህ ክፉ ነገር ሁሉ አገኘን እስኪሉ ድረስ ብዙ ክፉ ነገርና ጭንቀት ይደርስባቸዋል።
አስተውሉ፤ የእግዚአብሔርንም ጸጋ የሚያቃልል አይኑር፤ ሕማምን የምታመጣ፥ ብዙዎችንም የምታስታቸውና የምታረክሳቸው መራራ ሥር የምትገኝበትም አይኑር።