ደግሞም አንድ ልብ ይሰጣቸው ዘንድ፥ በእግዚአብሔርም ቃል የሆነውን የንጉሡንና የአለቆቹን ትእዛዝ ያደርጉ ዘንድ የእግዚአብሔር እጅ በእነርሱ ላይ ሆነ።
ዕብራውያን 13:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰላም አምላክ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን በእናንተ እያደረገ ፈቃዱን ታደርጉ ዘንድ በመልካም ሥራ ሁሉ ፍጹማን ያድርጋችሁ፤ ለእርሱ እስከ ዘለዓለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈቃዱን እንድታደርጉ በመልካም ነገር ሁሉ ያስታጥቃችሁ፤ ደስ የሚያሠኘውንም በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእኛ ያድርግ፤ ለርሱ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን። አሜን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን በእናንተ እያደረገ፥ ፈቃዱን ትፈጽሙ ዘንድ በመልካም ሥራ ሁሉ ፍጹማን ያድርጋችሁ፤ ለእርሱ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፈቃዱን ለመፈጸም እንድትበቁ በመልካም ነገር ሁሉ ያስታጥቃችሁ፤ ደስ የሚያሰኘውንም በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእኛ ያድርግ፤ ለኢየሱስ ክርስቶስም ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ክብር ይሁን፤ አሜን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን በእናንተ እያደረገ፥ ፈቃዱን ታደርጉ ዘንድ በመልካም ሥራ ሁሉ ፍጹማን ያድርጋችሁ፤ ለእርሱ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን። |
ደግሞም አንድ ልብ ይሰጣቸው ዘንድ፥ በእግዚአብሔርም ቃል የሆነውን የንጉሡንና የአለቆቹን ትእዛዝ ያደርጉ ዘንድ የእግዚአብሔር እጅ በእነርሱ ላይ ሆነ።
ከሁለቱ የአባቱን ፈቃድ ያደረገ ማን ነው?” “ፊተኛው” አሉት። ኢየሱስ እንዲህ አላቸው “እውነት እላችኋለሁ፥ ቀራጮችና ጋለሞቶች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት በመግባት ይቀድሙአችኋል።
እኔ በእነርሱ እኖራለሁ፤ አንተም በእኔ፤ በአንድ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ፤ አንተም እንደ ላክኸኝና እንደ ወደድኸኝ እኔም እነርሱን እንደ ወደድኋቸው።
ፈቃዱን ሊያደርግ የሚወድድ ግን ትምህርቴ ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ ሆነች፥ የምናገረውም ከራሴ እንዳይደለ እርሱ ያውቃል።
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን፤ አሜን። በቆሮንቶስ ተጽፋ ለክንክራኦስ ማኅበረ ክርስቲያን በምትላላከው በፌቤን እጅ ወደ ሮሜ ሰዎች የተላከችው መልእክት ተፈጸመች። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ለዘለዓለሙ አሜን።
እግዚአብሔር መልካሙን ነገር ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል፤ ፍጹም በረከቱንም ለዘወትር ያበዛላችሁ ዘንድ፥ ለሁሉም ታተርፉታላችሁ፤ በጎ ሥራ መሥራትንም ታበዛላችሁ።
እግዚአብሔር በሥራው እውነተኛ ነው፤ መንገዱም ሁሉ የቀና ነው፤ እግዚአብሔር የታመነ ነው፤ ክፋትም የለበትም፤ እግዚአብሔር ጻድቅና ቸር ነው።
ነገር ግን ሁሉ አለኝ፤ ይበዛልኝማል፤ የመዓዛ ሽታና የተወደደ መሥዋዕት የሚሆነውን፥ ለእግዚአብሔርም ደስ የሚያሰኘውን ስጦታችሁን ከአፍሮዲጡ ተቀብዬ አሟልቻለሁ።
በቃልም ቢሆን፥ ወይም በሥራ የምታደርጉትን ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አድርጉ፤ ስለ እርሱም እግዚአብሔር አብን አመስግኑት።
ከእናንተ ወገን የሚሆን ኤጳፍራስም ሰላም ይላችኋል፥ እርሱ የክርስቶስ አገልጋይ ነው፤ እግዚአብሔር በሚወደው ነገር ሁሉ ምሉኣንና ፍጹማን እንድትሆኑ፥ ስለ እናንተ ዘወትር ይጸልያል፤ ይማልዳልም።
የሰላምም አምላክ ራሱ ሁለንተናችሁን ይቀድስ፤ መንፈሳችሁም ነፍሳችሁም ሥጋችሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ያለ ነቀፋ ፈጽመው ይጠበቁ።
ልጆችን በማሳደግ፥ እንግዶችንም በመቀበል፥ የቅዱሳንንም እግሮች በማጠብ፥ የተጨነቁትንም በመርዳት፥ በጎንም ሥራ ሁሉ በመከተል፥ ይህን መልካም ሥራ በማድረግ የተመሰከረላት ልትሆን ይገባል።
እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤ ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ይኖራል፤ አንድ ሰው እንኳ አላየውም፤ ሊያይም አይቻለውም፤ ለእርሱ ክብርና የዘላለም ኀይል ይሁን፤ አሜን።
ስማቸው በሰማይ ወደ ተጻፈ ወደ ማኅበረ በኵርም፥ ሁሉን ወደሚገዛም ወደ እግዚአብሔር፥ ወደ ፍጹማን ጻድቃንም ነፍሳት፥
ስለዚህ የማይናወጥ መንግሥትን ስለምንቀበል በማክበርና በፍርሀት እግዚአብሔርን ደስ እያሰኘን የምናመልክበትን ጸጋ እንያዝ።
ነገር ግን ለድሆች መራራትን፥ ከእነርሱም ጋር መተባበርን አትርሱ፤ እንዲህ ያለው መሥዋዕት እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋልና።
እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።
ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።
ብቻውን ለሆነ አምላክና መድኃኒታችን ከዘመን ሁሉ በፊት አሁንም እስከ ዘላለምም ድረስ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ክብርና ግርማ ኀይልም ሥልጣንም ይሁን፤ አሜን።
በዙፋኑም ፊት ብርሌ የሚመስል የብርጭቆ ባሕር ነበረ። በዙፋኑም መካከል በዙፋኑም ዙሪያ፥ በፊትና በኋላ ዐይኖች የሞሉአቸው አራት እንስሶች ነበሩ።
በሰማይና በምድርም ከምድርም በታች በባሕርም ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ በእነርሱም ውስጥ ያለ ሁሉ “በረከትና ክብር ምስጋናም ኀይልም ከዘላለም እስከ ዘላለም በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠው፥ ለበጉም ይሁን፤” ሲሉ ሰማሁ።
“መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል ታርደሃልና፤ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ፥ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፤ በምድርም ላይ ይነግሣሉ፤” እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።