ዕንባቆም 1:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱ የሚያስፈሩና የሚያስደነግጡ ናቸው፣ ፍርዳቸውና ክብራቸው ከራሳቸው ይወጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም የሚያስፈሩና የሚያስደነግጡ ናቸው፤ ፍርዳቸውና ክብራቸው፣ ከራሳቸው ይወጣል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱ የሚያስፈሩና የሚያስደነግጡ ናቸው፤ ፍርዳቸውና ክብራቸው ከራሳቸው ይወጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ አስፈሪና አስደንጋጭ ናቸው፥ የራሳቸውን ክብር ማስጠበቂያ ሕግ ያወጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱ የሚያስፈሩና የሚያስደነግጡ ናቸው፥ ፍርዳቸውና ክብራቸው ከራሳቸው ይወጣል። |
መልእክተኞችን በባሕር ላይ፥ ደብዳቤዎችንም በውኃ ላይ ይልካል። ፈጣኖች መልእክተኞች ወደ ረዥምና ወደ ባዕድ፥ ወደ ክፉም ሕዝብ ይሄዳሉና፤ ተስፋ የቈረጡና የተረገጡ ሕዝብ እነማን ናቸው? ዛሬ ግን የምድር ወንዞች ሁሉ፥ ሰዎች እንደሚኖሩባት ሀገር ይኖራሉ።
በዚያ ዘመን ለሠራዊት ጌታ ለእግዚአብሔር፥ ከተዋረደና ከደከመ ሕዝብ፥ ከዛሬ እስከ ዘለዓለም ታላቅ ከሆነ ወገን፥ ተስፋ ከሚያደርግና ከሚረገጥ፥ በሀገሩ ወንዝ ዳር ከሚኖር ሕዝብ ዘንድ የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔር ስም በተጠራበት በደብረ ጽዮን እጅ መንሻ ይቀርባል።
አሁንም አንቺ ቅምጥል ተዘልለሽ የምትቀመጪ፥ በልብሽም፥ “እኔ ነኝ ከእኔም በቀር ሌላ የለም፤ መበለትም ሆኜ አልኖርም፤ የወላድ መካንነትንም አላውቅም” የምትዪ፥ ይህን ስሚ፤
ተዘልላ የተቀመጠች፥ በልብዋም፦ እኔ ነኝ፥ ከእኔም በቀር ሌላ የለም ያለች ደስተኛይቱ ከተማ ይህች ናት፣ አራዊት የሚመሰጉባት ባድማ እንዴት ሆነች! በእርስዋ በኩል የሚያልፈው ሁሉ እጁን እያወዛወዘ ያፍዋጫል።
አንተ ቅረብ፤ አምላካችን እግዚአብሔር የሚለውን ሁሉ ስማ፤ እምላካችን እግዚአብሔርም ለአንተ የሚናገረውን ሁሉ ለእኛ ንገረን፤ እኛም ሰምተን እናደርገዋለን።