Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 18:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን በባ​ሕር ላይ፥ ደብ​ዳ​ቤ​ዎ​ች​ንም በውኃ ላይ ይል​ካል። ፈጣ​ኖች መል​እ​ክ​ተ​ኞች ወደ ረዥ​ምና ወደ ባዕድ፥ ወደ ክፉም ሕዝብ ይሄ​ዳ​ሉና፤ ተስፋ የቈ​ረ​ጡና የተ​ረ​ገጡ ሕዝብ እነ​ማን ናቸው? ዛሬ ግን የም​ድር ወን​ዞች ሁሉ፥ ሰዎች እን​ደ​ሚ​ኖ​ሩ​ባት ሀገር ይኖ​ራሉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ይህችውም መልእክተኞችን በባሕር፣ ከወንዞች ማዶ በደንገል ጀልባ የምትልክ ናት። እናንተ ፈጣን መልእክተኞች ረዣዥምና ቈዳው ወደ ለሰለሰ፣ ከቅርብም ከሩቅም ወደሚፈራ ሕዝብ፣ ኀያልና ቋንቋው ወደማይገባ፣ ወንዞች ምድሩን ወደሚከፍሉት መንግሥት፣ ሂዱ!

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 መልእክተኞችን በባሕር ላይ፥ የደንገል መርከቦችንም በውኃ ላይ ለምትልክ ምድር ወዮላት! እናንተ ፈጣን መልእክተኞች ሆይ፥ ወደ ረጅምና ወደ ለስላሳ ሕዝብ፥ ከቅርብም ከሩቅም አስፈሪ ወደ ሆነ ሕዝብ፥ ኀያል ወደሆነና ወደሚገዛ፥ ወንዞችም ምድራቸውን ወደሚከፍሉት ሕዝብ ሂዱ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ያቺ አገር መልእክተኞችን ከደንገል በተሠራ ጀልባ በአባይ ወንዝ ላይ ትልካለች፤ ሕዝብዋ ረጃጅሞችና ቆዳቸው ለስላሳ፥ አገራቸው በወንዞች የተከፋፈለች፥ ጠንካሮችና ኀያላን በመሆናቸው በዓለም ሁሉ ወደሚፈሩት ሕዝቦች እናንት ፈጣን መልእክተኞች ሂዱ!

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 መልእክተኞችን በባሕር ላይ የደንገል መርከቦችንም በውኃ ላይ ለምትልክ ምድር ወዮላት! እናንተ ፈጣኖች መልእክተኞች ሆይ፥ ወደ ረጅምና ወደ ለስላሳ ሕዝብ፥ ከመጀመሪያው አስደንጋጭ ወደ ሆነው ወገን፥ ወደሚሰፍርና ወደሚረግጥ፥ ወንዞችም ምድራቸውን ወደሚከፍሉት ሕዝብ ሂዱ።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 18:2
14 Referencias Cruzadas  

በዚያ ዘመን ለሠ​ራ​ዊት ጌታ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ ከተ​ዋ​ረ​ደና ከደ​ከመ ሕዝብ፥ ከዛሬ እስከ ዘለ​ዓ​ለም ታላቅ ከሆነ ወገን፥ ተስፋ ከሚ​ያ​ደ​ር​ግና ከሚ​ረ​ገጥ፥ በሀ​ገሩ ወንዝ ዳር ከሚ​ኖር ሕዝብ ዘንድ የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም በተ​ጠ​ራ​በት በደ​ብረ ጽዮን እጅ መንሻ ይቀ​ር​ባል።


ኢት​ዮ​ጵ​ያ​ው​ያ​ንና የል​ብያ ሰዎች እጅግ ብዙ ሰረ​ገ​ሎ​ችና ፈረ​ሰ​ኞች የነ​በ​ሩ​አ​ቸው እጅግ ታላቅ ጭፍራ አል​ነ​በ​ሩ​ምን? በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ታመ​ንህ በእ​ጅህ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው።


የኢ​ት​ዮ​ጵ​ያም ንጉሥ ዝሪ አንድ ሚሊ​ዮን ሰዎ​ችና ሦስት መቶ ሰረ​ገ​ሎች ይዞ ወጣ​ባ​ቸው፤ ወደ መሪ​ሳም መጣ።


በዚያ ቀን መል​እ​ክ​ተ​ኞች ተዘ​ል​ለው የሚ​ኖ​ሩ​ትን ኢት​ዮ​ጵ​ያ​ው​ያ​ንን ለማ​ጥ​ፋት ከፊቴ በመ​ር​ከብ ይወ​ጣሉ፤ በግ​ብ​ፅም ቀን ሁከት ይሆ​ን​ባ​ቸ​ዋል፤ እነሆ፥ ይመ​ጣ​ልና።


ደግ​ሞም ሊሸ​ሽ​ጉት በአ​ል​ቻሉ ጊዜ እናቱ የደ​ን​ገል ሣጥን ለእ​ርሱ ወስዳ ዝፍ​ትና ቅጥ​ራን ለቀ​ለ​ቀ​ችው፤ ሕፃ​ኑ​ንም አኖ​ረ​ች​በት፤ በወ​ን​ዝም ዳር ባለ በቄ​ጠማ ውስጥ አስ​ቀ​መ​ጠ​ችው።


እነሆ፥ ጊን​ጦ​ች​ንና እባ​ቦ​ችን፥ የጠ​ላ​ት​ንም ኀይል ሁሉ ትረ​ግጡ ዘንድ ሥል​ጣ​ንን ሰጠ​ኋ​ችሁ፤ የሚ​ጐ​ዳ​ች​ሁም ነገር የለም።


የመ​ር​ከብ መን​ገድ ፍለጋ፥ ወይም የሚ​በ​ርና የሚ​በ​ላ​ውን የሚ​ፈ​ልግ የን​ስር ፍለጋ እን​ደ​ማ​ይ​ታ​ወቅ ሕይ​ወቴ እን​ዲሁ ሆነ።


“ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ መስ​ማ​ትን ሰም​ቻ​ለሁ፤ በአ​ሕ​ዛብ ሀገ​ሮች ተሰ​ብ​ሰቡ፤ በእ​ር​ስ​ዋም ላይ ኑ፤ እር​ስ​ዋ​ንም ውጓት፥ የሚል መል​እ​ክ​ተኛ ተል​ኳል።


የአ​ብ​ድዩ ራእይ። ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ ኤዶ​ም​ያስ እን​ዲህ ይላል፦ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ መስ​ማ​ትን ሰማሁ፤ ከባ​ቢን ወደ አሕ​ዛብ ልኮ፥ “ተነሡ፤ በላ​ይ​ዋም እን​ነ​ሣና እን​ው​ጋት።


እነርሱ የሚያስፈሩና የሚያስደነግጡ ናቸው፣ ፍርዳቸውና ክብራቸው ከራሳቸው ይወጣል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios