ለዮሴፍም በግብፅ ምድር ልጆች ተወለዱለት፤ እነርሱም የሄልዮቱ ከተማ ካህን የጴጤፌራ ልጅ አስኔት የወለደችለት ምናሴና ኤፍሬም ናቸው። ሶርያዊት ዕቅብቱ የወለደችለት የምናሴም ልጅ ማኪር ነው። ማኪርም ገለዓድን ወለደ፤ የምናሴም ወንድም የኤፍሬም ልጆች ሱታላና ጠኀን ናቸው። የሱታላ ልጅም ኤዴን ነው።
ዘፍጥረት 48:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህም ነገር በኋላ እንዲህ ሆነ፤ “እነሆ፥ አባታችን ደከመ” ብለው ለዮሴፍ ነገሩት፤ እርሱም ሁለቱን ልጆቹን ምናሴንና ኤፍሬምን ይዞ ሄደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከጥቂት ጊዜ በኋላም፣ “አባትህ ታሟል” ተብሎ ለዮሴፍ ስለ ተነገረው ሁለቱን ልጆቹን ምናሴንና ኤፍሬምን ይዞ ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጥቂት ጊዜ ካለፈ በኋላ “አባትህ ታሞአል” ተብሎ ለዮሴፍ ተነገረው፤ ስለዚህ ዮሴፍ ሁለቱን ልጆቹን ምናሴንና ኤፍሬምን ይዞ ያዕቆብን ለማየት ሄደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጥቂት ጊዜ ካለፈ በኋላ “አባትህ ታሞአል” ተብሎ ለዮሴፍ ተነገረው፤ ስለዚህ ዮሴፍ ሁለቱን ልጆቹን ምናሴንና ኤፍሬምን ይዞ ያዕቆብን ለማየት ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚህም ነገር በኍላ እንዲህ ሆነ እነሆ አባትህ ታምሞአል ብለው ለዮሴፍ ነገሩት እርሱም ሁለትን ልጆቹን ምናሴንና ኤፍሬምን ይዞ ሄደ። |
ለዮሴፍም በግብፅ ምድር ልጆች ተወለዱለት፤ እነርሱም የሄልዮቱ ከተማ ካህን የጴጤፌራ ልጅ አስኔት የወለደችለት ምናሴና ኤፍሬም ናቸው። ሶርያዊት ዕቅብቱ የወለደችለት የምናሴም ልጅ ማኪር ነው። ማኪርም ገለዓድን ወለደ፤ የምናሴም ወንድም የኤፍሬም ልጆች ሱታላና ጠኀን ናቸው። የሱታላ ልጅም ኤዴን ነው።
ለያዕቆብም፥ “እነሆ፥ ልጅህ ዮሴፍ መጥቶልሃል” ብለው ነገሩት፤ እስራኤልም ተጠነካከረ፤ በአልጋውም ላይ ተቀመጠ።
አሁንም እኔ ወደ አንተ ከመምጣቴ በፊት በግብፅ ምድር የተወለዱልህ ሁለቱ ልጆችህ ለእኔ ይሁኑ፤ ኤፍሬምና ምናሴ ለእኔ እንደ ሮቤልና እንደ ስምዖን ናቸው።
ኤልሳዕም በሚሞትበት በሽታ ታመመ፤ የእስራኤልም ንጉሥ ዮአስ ወደ እርሱ ወርዶ በፊቱ አለቀሰና፥ “አባቴ ሆይ፥ አባቴ ሆይ፥ የእስራኤል ሰረገላቸውና ፈረሰኛቸው” አለ።
ኢዮብም ከደዌው ከዳነ በኋላ መቶ ሰባ ዓመት ኖረ፥ ኢዮብም የኖረበት ዘመን ሁሉ ሁለት መቶ አርባ ነው። ልጆቹንና የልጅ ልጆቹንም እስከ አራት ትውልድ ድረስ አየ።
የዮሴፍ ልጆች ምናሴና ኤፍሬም ሁለት ነገዶች ነበሩ፤ ለሌዋውያንም ከሚቀመጡባቸው ከተሞች ለእንስሶቻቸው ከሚሆን ማሰማሪያቸውና ከእንስሶቻቸውም በቀር በምድሩ ውስጥ ድርሻ አልሰጡአቸውም።