ዘፍጥረት 47:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮሴፍም ለፈርዖን ካልሆነችው ከካህናቱ ምድር በቀር አምስተኛው እጅ ለፈርዖን እንዲሆን በግብፅ ምድር እስከ ዛሬ ሕግ አደረጋት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ዮሴፍ የምርቱ አንድ ዐምስተኛ ለፈርዖን እንዲገባ የሚያዝዝ የመሬት ሕግ በግብጽ አወጣ፤ ይህም ሕግ እስከ ዛሬ ይሠራበታል። በዚያ ጊዜ በፈርዖን እጅ ያልገባው መሬት የካህናቱ ብቻ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮሴፍም ለፈርዖን ካልሆነችው ከካህናቱ ምድር በቀር አምስተኛው እጅ ለፈርዓን እንዲሆን በግብጽ ምድር እስከ ዛሬ ድረስ ሕግ አደረጋት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ዐይነት ዮሴፍ ከመከር ሁሉ አንድ አምስተኛው እጅ ለፈርዖን እንዲሰጥ የግብጽን መሬት ይዞታ በሚመለከት ሕግ አወጣ፤ ይህም ሕግ እስከ ዛሬ ድረስ ይሠራበታል፤ የፈርዖን ንብረት ያልሆነው የካህናት መሬት ብቻ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮሴፍም ለፈርዖን ካልሆነችው ከካህናቱ ምድር በቀር አምስተኛው እጅ ለፈርዓን እንዲሆን በግብፅ ምድር እስከ ዛሬ ድረስ ሕግ አደረጋት። |
ለሐውልት ያቆምኋት ይህችም ድንጋይ የእግዚአብሔር ቤት ትሆንልኛለች፤ ከሰጠኸኝም ሁሉ ለአንተ ከዐሥር እጅ አንዱን እሰጥሃለሁ።”
ፈርዖን በግብፅ ምድር ላይ ሹሞችን ይሹም፤ በሰባቱም የጥጋብ ዓመታት ከሚገኘው ፍሬ በግብፅ ምድር ሁሉ ከአምስት እጅ አንደኛውን ይውሰድ።
ዮሴፍ የካህናትን ምድር ብቻ አልገዛም፤ ፈርዖን ለካህናቱ ድርጎ ይሰጣቸው ነበርና፥ ፈርዖንም የሰጣቸውን ድርጎ ይበሉ ነበር፤ ስለዚህም ምድራቸውን አልሸጡም።
ደግሞም በካህናቱና በሌዋውያኑ፥ በመዘምራኑም፥ በበረኞቹም፥ በናታኒምም በዚህም በእግዚአብሔር ቤት በሚሠሩ አገልጋዮች ላይ ግብርና ቀረጥ እንዳይጣል፥ የምትገዙአቸውም አገዛዝ እንዳይኖር ብለን እናስታውቃችኋለን።
ከአሕዛብ ዘንድ ከሁሉ የሚከፉትን አመጣለሁ፤ ቤታቸውንም ይወርሳሉ፥ የኀያላንንም ትዕቢት አጠፋለሁ፤ መቅደሶቻቸውም ይረክሳሉ።
“የምድርም ዐሥራት፥ ወይም የምድር ዘር፥ ወይም የዛፍ ፍሬ ቢሆን፥ የእግዚአብሔር ነው፤ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ነው።
“ለሌዊም ልጆች እነሆ፥ በምስክሩ ድንኳን አገልግሎት ስለሚያገለግሉ፥ የእስራኤልን ልጆች ዐሥራት ርስት አድርጌ ሰጥቻቸዋለሁ።
“ዐሥራት በምታወጣበት በሦስተኛው ዓመት የምድርህን ፍሬ ሁሉ ዐሥራት አውጥተህ በፈጸምህ ጊዜ፥ ሁለተኛ ዐሥራት አውጥተህ በከተሞችህ ውስጥ ይበሉ ዘንድ፥ ይጠግቡም ዘንድ ለሌዋዊው፥ ለመጻተኛውም፥ ለድሃ-አደጉም፥ ለመበለቲቱም ስጣቸው።